👆👆👆👆👆
📚ተከታታይ የሙሐደራ ግብዣ ቁ.1⃣4⃣📚
📋ርእስ ፦ #የአሽዓሪያ_ዓቂዳ_በጥቅሉ
👤አቅራቢ ፦ ኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ
🔶በሙሐደራው ውስጥ የተካተቱ ነጥቦች ▶️
🔷ባሳለፍነው ሙሐደራ ላይ በአለማችን ሰፊ ስርጭት ያላቸውን አሽዓሪያዎች አጠነሳሰስ እና አነሳስ ምን እንደሚመስል ተመልክተናል። ዛሬ ስለእምነታቸው የተወሰነ እናያለን።
♦️አሽዓሪያዎች ከታሪክ ሂደታቸው አንፃር ወጥ የሆነ አቋም የላቸውም። በዚህም መሰረት የመጀመሪያዎቹ አሽዓሪያዎች ከመጨረሻዎቹ የሚሻሉ ነበሩ። እንደምሳሌ ስናይ አቡልሐሰን አልአሽዓሪይ የሙዕተዚላነትን አቋም ከተወ በኋላ እና ወደ አህሉስ-ሱንና ሳይገባ በፊት ከአቡበከር አልባቂላኒ ይሻል ነበር አቡበከር አልባቂላኒም ከኢብኑ ፉረክ ይሻል ነበር ... እንዲህ እንዲህ እያለ የአሽዓሪያ መዝሀብ በተለያዩ መሪዎቹ እጅ ወደ ሙዕተዚላነት እንዲቀየር ያደረጉት በርካታ ተፅእኖዎች ነበሩ። ስለዚህ ጥቅል በሆነ መልኩ ከፍትህ አንፃር እና እውነታውን ከመረዳት አንፃር የመጀመሪያዎቹ እና የመጨረሻዎቹ እያሉ ከፋፍሎ ማየት አስፈላጊ ይሆናል።
°
♦️የመጀመሪያዎቹ አሽዓሪያዎች ከትክክለኛው አህሉስ-ሱንና ወልጀመዓህ የወጡበት ጉዳይ ከአላህ ስሞች እና ባህሪያት ጋር በተያያዙ ርእሶች ላይ ነው። የአላህን - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ባህሪያትን እንደ አህሉስ-ሱንና ቢቀበሉም ከፍላጎቱ ጋር የተያያዙ ባህሪያትን እንዳሉ መቀበል ተስኗቸው ነበር። በመሆኑም "ኢስቲዋእን" ፣ "ኑዙልን"/(በፈለገው ጊዜ መውረዱን) እና የመሳሰሉትን ባህሪያት አይቀበሉም።
°
♦️እንደምሳሌ የ"ኢስቲዋእ" ጉዳይ ላይ ስንመጣ አላህ ከፍጥረታቱ በላይ መሆኑን ያረጋግጡ ነበር። ነገር ግን "ኢስቲዋእን" ማለትም አላህ ከሱ ልቅና ጋር በሚገጥም መልኩ ከዐርሹ ላይ ከፍ ማለቱን ያስተባብሉ ነበር። የሚያስተባብሉበትም ምክንያት ይህ ባህሪይ ከጊዜ በኋላ የተፈፀመ ተግባር ስለሆነ ለአላህ ተገቢ አይደለም ብለው ስለሚያስቡ ነው።
°
♦️ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ስንገባ ደግሞ በርካታ ስሕተቶችን እናስተውላለን። ለምሳሌ አሽዓሪያዎች የአላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ንግግርን አስመልክቶ የሚከተሉት አቋም የኢብኑ ኩላብ አባባል ላይ ትንሽ ማሻሻያ በማድረግ ነው። ኢብኑ ኩላብ ቁርአን በትክክል የአላህ ቃል መሆኑን አላረጋገጠም። ቁርአን ከአላህ ቃል የተወራ ነው ብሎ ተናገረ። አሽዓሪያቹም ቁርአን በትክክል አላህ የተናገረበት ንግግር ሳይሆን መልእክቱ ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው ግን ይህን መልእክት የገለፀው እና በዐረበኛ ያስተላለፈው ጅብሪል ነው በማለት ያምናሉ። እናም ይህንን "ዒባራህ ዐን ከላሚ-ሏህ"/(ከአላህ ቃል የተገለፀ) በማለት ይጠሩታል።
°
♦️በኢማን ዙሪያ ላይ ያላቸው አቋም ኢማን በልብ ብቻ ማመን እንጂ ተግባርን እና ንግግርን አያካትትም የሚለውን የሙርጂአዎች አቋም ነው። በቀደር በኩል ደግሞ አቋማቸው የ"ጀብሪያ" ነው። ማለትም ባሪያዎች የራሳቸው ምርጫ የላቸውም ፤ አንድን ተግባር የሚተገብሩት አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - አስገድዷቸው ነው የሚል እምነት አላቸው ምንም እንኳን ይሄን እምነታቸው በግልጽ በዝርዝር ባይናገሩትም ጥቅል በሆነ መልኩ ይህን አቋማቸውን ኪታባቸው ላይ አስፈረውታል።
°
♦️ከአላህ ውሳኔዎች እና ፍርዶች በስተጀርባ ጥበብ ወይም "ሒክማህ" የለም ብለውም ያምናሉ። ማለትም አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - የሆነን ነገር ሲፈፅም ከበስተኋላው "ሒክማህ"/(ጥበብ) እና "ዒለህ"/(ምክንያት) የለም ብለው ያምናሉ። ከአላህ ዘንድ የሚደነገግ መለኮታዊ ትእዛዝ ከመተላለፉ በፊት ነገሮች በመጥፎነትም በጥሩነትም አይታወቁም ብለው ያስባሉ። የሆነ ነገር መጥፎ እና ጥሩ የሚሆነው ሸሪዓ ሲወርድ ብቻ ነው እንጂ ከዛ በፊት አንድ ነገር መጥፎም ጥሩም አይሆንም በማለት ድንበር ያልፋሉ። ሙዕተዚላዎች ደግሞ አንድ ሰው መልእክተኛ ሳይመጣለት በፊት ራሱ የሆነ ነገር ጥሩ መሆኑን አውቆ ካልሰራው እና ሌላ ነገርን ደግሞ መጥፎ መሆኑን አውቆ ከሰራው አላህ ዘንድ ይቀጣበታል ይላሉ። በዚህ ርእስ ላይ ትክክለኛው አቋም በሙዕተዚላዎች እና በአሽዓሪያዎች መካከል ላይ ያለው የአህሉስ-ሱንናዎች ነው።
°
♦️የመጨረሻዎቹ ከመጀመሪያዎቹ ከወረሷቸው ጥመቶች ባሻገር በየጊዜው አዳዲስ የራሳቸው ጥመትን ይጨምራሉ። የመጀመሪያዎቹ ቅድም እንዳየነው የአላህን ከተግባሩ ጋር የሚያያዙ ባህሪያትን ብቻ ነው የማይቀበሉት እነዚህ ግን ከማይቀበሏቸው የሚቀበሏቸውን መቁጠር ይቀላል። እነርሱም ሰባት ባህሪያት ብቻ ሲሆኑ እነዚህንም ባህሪያት የሚገነዘቡት በራሳቸው አረዳድ ነው እንጂ አህሉስ-ሱንና ወልጀመዓህ በሚያፀድቁበት መንገድ አይደለም። ሰባቱ ባህሪያትም "አልሐያት"/(ህይወት) ፣ "አልኢልም"/(እውቀት) ፣ "አልኢራዳህ"/(ፍላጎት) ፣ "አልቁድራህ" ፣ "አስ-ሠምዕ"/(መስማት) ፣ "አልበሰር"/(መመልከት) እና "አልከላም"/(ንግግር) ናቸው። እነዚህንም "ሲፈተል መዓኒ" ይሏቸዋል። ሌሎቹን በቁርአን እና በሐዲስ የተረጋገጡ የአላህን ባህሪያት ለምን አትቀበሉም? ሲባሉ ፦ እነዚህ ባህሪያት በአእምሯችን ስንመዝነው ትክክል ስለሆነ እና ስለገጠመ እና ሌሎቹ ደግሞ ከአእምሯችን ጋር ስለማይገጥሙ በማለት ውሃ የማያነሳ ምክንያት ያቀርባሉ። አንዳንዶቹ እነዚህን ባህሪያት ላይ የተወሰነ ጨማምረው ወደ20 ያደርሷቸዋል።
°
♦️የመጨረሻዎቹ አሽዓሪያዎች ምንም እንኳን ሙዕተዚላዎች ላይ ምላሾችን ቢሰጡም ፣ አንዳንድ ንግግራቸው ላይ እውነቶች ቢኖሩም በጥቅሉ ሲታዩ ከሙዕተዚላቸው ጋር የሚያቀራርባቸው ነገሮች በዝተው ከነሱ ጋር መመሳሰል ችለዋል። እንደውም በአንዳንድ ርእሶች ላይ ከነሱ የወሰዷቸው ነገሮች እንዳሉ መሪዎቻቸው ሳይቀር ያምናሉ። ለምሳሌ በሰው ልጅ ላይ መጀመሪያ ማወቅ ግዴታ የሚሆንበት ተግባር ተውሒድ ምናምን ሳይሉ "ነዘር" ነው ይላሉ። ይህም ማለት ፍጥረተ-ዓለሙን በማስተዋል መልኩ መመልከት ነው ይላሉ። ይህንንም ሊሉበት የቻሉበት ምክንያት ቁርአዊ እና ሓዲሳዊ መረጃዎች በቂ አይደለም ብለው ስለሚያምኑ ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው እምነቱን ሊመሰረት የሚገባው ምንም በማያጠራጥር ነገር ነው እናም ይህንንም የሚያስገኘው "ነዘር" ነው ብለው የፍልስፍና አካሄድ ይሄዳሉ። ሌሎቹ ደግሞ ድንበር አልፈው መጀመሪያ አንድ ሰው ላይ ግዴታ የሚሆነው ነገር "ሸክ"/(መጠራጠር) ነው ይላሉ።
°
♦️የአሽዓሪያዎች ችግር በጣም ብዙ ነው። ዓቂዳቸውን ከብዙ በጥቂቱ ከላይ ያየነውን ይመስላል። ይህን አቋማቸውንም የተለያዩ ኪታባቸው ላይ ተጠቅሶ ይገኛል። እያንዳንዱን ችግር ለየብቻ ነጥለን ሰፋ አድርገን ብንመለከት አንዱ ርእስ ብቻ ከአህሉስ-ሱንና ወልጀመዓህ ለማስወጣት ያለምንም ማመንታት በቂ ነው። በታሪክ ዘመንም የነበሩ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንት የነሱ አካሄድ ከእህሉስ-ሱንና ወልጀመዓህ መንሃጅ የወጣ መሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም ግን የተለያዩ ጥቅል የሆኑ የዑለማዎች ንግግሮችን እንደምሳሌ በማምጣት ህዝቡ ላይ ማምታቻ ለመጣል እና ራሳቸው አህሉስ-ሱንና ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ይጥራሉ። ይዘቱ ግን በተቃራኒው ነው።
____________
📕ምንጭ ፦ ከኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ "የአሽዓሪያዎች ዓቂዳ በጥቅሉ" ከሚለው ሙሐደራ ላይ የተወሰደ
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
📆ዙልቀዕዳህ 02/1439ሂ. #ሐምሌ 08/2010
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📜ሙሉውን ከኦዲዮው ያዳምጡ። እርሶ ጋር ብቻ እንዲቀር ካልፈለጉ ለወዳጅ ዘመድም ያስተላልፉ።
🔊ዳውንሎድ ሊንክ
⏬⏬⏬⏬⏬