IN christ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


****************
(👉 ኢየሱስ የሆነላችሁን እና እናንተን ያደረጋችሁን በማሰብ በምስጋና ዋሉ......ተባረኩበት)
ያ የተረገመ ፣ የተባረከ ቀን
ለኛ የነፃነት ፣ ለሱ የሰቀቀን
ለኛ የደስታ ፣ ለሱ የጭንቅ ቀን
የፍስሀ ፣ የምጥ ሰአት
የእርካታ ፣ የመጠማት
የእስራት ፣ የአርነት
የህማም ቀን ፣ የድህነት
ቀን ሊሆነን.......
በህመሙ ፣ ሊፈውሰን
ኃጢአት ሆኖ ፣ ሊቀድሰን

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ሰው ሁሉ የተፈጠረበትን ክቡር ዐላማ፣ ፈጣሪው ያየለትን ድንቅ ሕይወትና ያንንም ከመኖር ከልክሎት ያለውን ጕድለቱን፣ እንዲሁም ከጕድለቱ ሊያወጣው የሚችለውን ብቸኛ መፍትሔ አውቆ በዚያ ቢጠቀም እጅግ መልካም ነው። ከዚህ አማራጭ ውጭ ያለው በኀጢአት በተገዛ የዓለም ውሸት ውስጥ ለዘላለም መጥፋት ነው። ከሞት ሕይወት እጅግ የተሻለና ሊወዳደር የማይችል ነው። ሕይወትም እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

በኢየሱስ የሆንን እኛ በሕይወት ነን፤ ማንም እርሱን በሕይወትነቱ ቢያውቀው በሕይወት ይኖራል። ሊያውቀው ባይወድድ ግን በሞት ይቀራል፤ መጨረሻውም ለዘላለም ከእግዚአብሔር የመለየት ቅጣት ይሆናል።

“ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት አንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ …” (ዮሐንስ 11፥25-26)።

#ኢየሱስወይስሞት #ሕይወትኢየሱስነው

https://t.me/inchrist_life




“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”
— ሮሜ 3፥23


ከማንም ጋር አላወዳድርህም
ከማንም ጋር እኩያ አላደርግህም (2x)

ለጌታዎቹ ጌታ ነህ
ለነገሥታቱም ንጉሥ ነህ
ለኃያላኑም ኃያል ነህ
እግዚአብሔር ልዩ ነህ

ከዘለዓለም ዘለዓለም በፊት ብቻህን የነበርከው
ከዘለዓለም ዘለዓለም በኋላ ብቻህን የምትኖረው
ፍጥረት ቢያመልክ ባያመልክህ ቢሰግድ ባይሰግድልህ
ከክብርህ ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጐድልብህ
ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጐድልብህ (2x)

እውነት ነው እኔ ዝም ብል ድንጋዮች ይናገሩልሃል
እጅ እግሬን አጥፌ ብቀመጥ ኮረብቶች ይዘሉልሃል
ወንዞች ያጨበጭቡልሃል አእዋፋት ይዘምሩልሃል
ስለጐደለህ አይደለም እኔ የምጨምረው
ስላነሰህም አይደለም እኔ የማበዛው
ስለሚገባህና ስለተገባህ ነው (2x)

የተለየ ነው አምላክነት ንግስናህ
የተለየ ነው ገናናነትህ ዝናህ
የተለየ ነው መቀመጫህ ዙፋንህ
የተለየ ነው ማስፈራቱ የክብርህ

አልፋ ነህ ኦሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ
አልፋ ነህ (አልፋ ነህ) ኦሜጋ (ኦሜጋ)
መጀመሪያ (መጀመሪያ) መጨረሻ (መጨረሻ)

አልፋ ነህ ኦሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ
አልፋ ነህ (አልፋ ነህ አልፋ ነህ) ኦሜጋ (ኦሜጋ ኦሜጋ)
መጀመሪያ (መጀመሪያ መጀመሪያ) መጨረሻ (መጨረሻ)

አልፋ ኦሜጋ
ኦሜጋ ነህ መጨረሻ
ሁሉን የምትገዛ ጌታ

https://t.me/inchrist_life


1ማወቅ
2መቁጠር
3ራሳችንን ለእግዚአብሔር መቅረብ
4በመንፈስ መመላለስ

።።።።።።።።።። ከክርስቶስ ጋር መሞታችን።።።።።።።። ።
ሮሜ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?
³ ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?
⁴ እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
⁵ ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤
⁶ ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።
⁷-⁸ ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤
⁹ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና።
¹⁰ መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል።
¹¹ እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።
✝️✝️✝️✝️ ሮም 6:6

https://t.me/inchrist_life


በልሳን የሚጸልዩ ሰዎች መንፈሳቸው ሬማን (የጌታን ድምፅ) ለመያዝ በጣም ክፍት እና እጅግ ቅርብ ነው። አንድን ልጅ በመንፈስ መጸለይ ምን ማለት ነው? ብዬ ስጠይቀው “ዓይን ጨፍኖ መጸለይ” አለኝ፡፡ በመንፈስ መመላለስስ ምን ማለት ነው ብዬ ብጠይቀውስ ምን ይል ይሆን? ብዬ አስቤ ፈገግ አልኩ፤ ዓይን ጨፍኖ መሄድ? ዓይን ጨፍኖ መንዳት…? ወይስ ምን ሊሆን ይችላል?

..በመንፈስ መጸለይ ማለት በልሳን መጸለይ ወይም ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ሆኖ መጸለይ ማለት ነው፡፡ በልሳን መጸለይ በአእምሮ ከምንጸልየው በላይ እንዴት ውስጠኛውን ሰውነታችንን እንደሚያጠነክር ልነግራችሁ አልችልም! በልሳን አብዝተን መጸለይ አለብን፡፡ በልሳን የሚጸልይ ራሱን ይገነባል፣ ያንጻል (ቻርጅ ያደርጋል)፣ ያነሳሳል፣ ያሳድጋል፣ ያበረታታል ይላል፡፡

1ቆሮ 14:4 (ምናልባት በልሳን የማትናገሩ ከሆነ በዚህ ሰአት በእምነት መቀበል ትችላላችሁ)

ሐዋሪያው ጳውሎስ ከሁላችሁ ይልቅ አብዝቼ በልሳን እናገራለሁ ያለን ለዚህ ነው፡፡

“ከሁላችሁ የበለጠ በልሳን ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥18

በልሳን የሚጸልዩ ሰዎች መንፈሳቸው ሬማን ለመያዝ በጣም ክፍት እና ቅርብ ነው፤ ልሳን ሰማያዊ ቋንቋ ነው፡፡ በልሳን መናገር ውስጣችሁን ይገነባል፡፡ ለዚህ ነው በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ የሚለን፡፡

“በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥”
— ኤፌሶን 3፥16-17

ሎጎስ የሆነው ቃል ውስጣችሁ ካለ በልሳን ስትጸልዩ ሬማ የሆነው የጊዜው ቃል ከመንፈሳችሁ ውስጥ ይወጣል፡፡ ቃሉ ለዚህ ነው ሳናቋርጥ በመንፈስ እንድንጸልይ የነገረን፡፡

“በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤”
— ኤፌሶን 6፥18


join @inchrist_life
@inchrist_life


New worship live
አንተ ትልቅ ነህ
👉share and share
https://t.me/inchrist_life




#ተሐድሶ (Reformation)

ተሐድሶ ግን ምንድን ነው?

ተሐድሶ ማለት ማደስ፣ መለወጥ፣ ማበረታታት፣ አዲስ ነገር ማውጣት፣ ... ማለት ነው። (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ .435)

ተሐድሶ ማለት ያረጀን፣ የተበላሸን፣ የቀድሞ ይዘቱን የለቀቀን ነገር ቀድሞ ወደነበረበት ይዘት መመለስ ወይም አዲስ ማድረግ ማለት ነው። (ጌታቸው ኃይሌ)

ተሐድሶ የሚለውን ቃል የሚተኩት የእንግሊዝኛ አቻዎቹ #Reformation, #Renewal & #Restoration ናቸው።

Reformation _ ማለት እንደገና መለወጥ፣ የተበላሸውን እና የተመሰቃቀለውን ቦታ ስርዓት አስይዞ ማስቀመጥ፣ ፈር የለቀቀውን አዲስ ሥርዓት ማስያዝ ማለት ነው።

Renewal _ ማደስ፣ የቀድሞ መልክና ውበትን መመለስ ማለት ነው።

Restoration _ ወደ ቀድሞ ስፍራው መመለስ ማለት ነው።

"ተሐድሶ ማለት የነገረ መለኮታዊ፣ የአስተሳሰብ፣ የድርጅታዊ እና የፕሮግራም አወቃቀሮችን ዳግም ማደስ ማለት ነው።" ቦቢ ግሊያም

(ተሐድሶ _ #በጸጋአብ #በቀለ)

ተሐድሶ የሃይማኖት ድርጅት ወይም ተቋም አይደለም!. ተሐድሶ ሰዋዊ አስተሳሰብ አይደለም!. ተሐድሶ የማይጨበጥ ሕልም አይደለም!. ተሐድሶ የግለሰብ መጠሪያ ስም አይደለም!. ተሐድሶ ወቅታዊ እንቅስቃሴ አይደለም!. ተሐድሶ በሰው የሚለኮስ ችቦ አይደለም!.

ተሐድሶ ንጹሕ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል የሚያስነሳው አብዮት ነው!. ተሐድሶ ከራሱ ከእግዚአብሔር የሚነሳ አብርሆት ነው!. የተሐድሶ አቀጣጣይ ራሱ እግዚአብሔር ነው!. ተሐድሶ ወቅታዊ ሳይሆን ሂደታዊ ነው!. ተሐድሶ በአማኞች ኑሮ ቀጣይነት ያለው ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋል!.

ተሐድሶ ... በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሳሳን የሰው አሳብ ያመክናል!. ተሐድሶ ዘመን ያስቆጠሩ ቢሆኑ እንኳን እንደ ቃሉ ያልሆኑ ትምህርቶችን፣ ትንቢቶችን፣ ሥርዓቶችን፣ ልምዶችን፣ ልምምዶችን፣ አካሂያዶችን እና አደራረጎችን ይነቅላል።

The Way Reformation Ministry, Ethiopia.

ለሌሎች አካፍሉ፦
#Grace #Commission
https://t.me/inchrist_life




Репост из: Ethio-luxury
Cargo Tuta
Available on hand
Best Quality
Size 29 30 31 32 33 34
Price #1500 birr
Contact me @EthioLuxuryMarketingManager




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram

Показано 13 последних публикаций.

167

подписчиков
Статистика канала