እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ታሪካዊ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አሜሪካን ሀገር ኬንታኪ ስቴት (Kentucky State) ከሚገኙ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ዓለምአቀፋዊ ትስስር በመፍጠር የትምህርት እና የምርምር ጥራት ለማስጠበቅ፣ የመምህራን እና የተመራማሪዎችን አቅም ለማሳደግ እና ዓለምአቀፋዊ ገጽታዉን ለማሳደግ በያዘው እቅድ መሠረት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ እና የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አእምሮ ታደሰ በአሜሪካን ሀገር ከሚገኙ ኬንታኪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ( Kentucky State University) እና ከኬንታኪ ዩኒቨርሲቲ ( University of Kentucky) ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሜሪካ ከሚገኙ ዩኒቨርሲሰዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሲፈራረም የመጀመሪያው ሲሆን ስምምነቱም ታሪካዊ ሊባል የሚያስችለው ነው።
ስምምነቱ በኬንታኪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኮፊ አካክፓ፣ በኬንታኪ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ም/ዲን ፕ/ር ሱሬንድራናት ሱማን እና በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ የተፈረመ ሲሆን የመግባቢያ ስምምነቱ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመምህራን እና የተማሪዎች ልውውጥ( Faculty and students exchange)፣በጋራ ምርምር ማካሄድ እና የምርምር ፈንድ ማፈላለግ፣ ኮንፈረንስ እና ወርክሾፕ በጋራ ማከናወን እና የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን የሚያካትት ነው።
https://www.facebook.com/share/r/19xG5tQo93/