በአፈር አሲዳማነት እና በመስኖ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ለግብርና ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ።
መጋቢት 29/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የአፈር አሲዳነትና ለምነትን ማሻሻል፤ እንዲሁም በመስኖ አጠቃቀምና አስተዳር ዙሪያ ለጓንጓ ወረዳ የግብርና ባለሙያዎች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና በግብርና ኮሌጅ አስተባባሪነት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ዲን ሀብታሙ አድማስ (ዶ/ር) በስልጠናው ማጠቃለያ በሰጡት ማብራሪያ ሰልጣኞች ሲመለሱ የአፈር ለምነትን የሚቀንሱ ነገሮችን ለአርሶ አደሩ በማሰልጠን ምርታማነት እንዲሻሻል የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የአፈር ለምነትን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ የሆነውን የአፈር አሲዳማነትን በማከም የአፈር ለምነትን መመለስ እንደሚቻል በሳይንሳዊ በስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንደተፈጠረ ጠቀሰው በተጨማሪም የአፈር ለምነትን የሚቀንሰው የአፈር መሸርሸር ሲሆን፣ በአፈር መሸርሸር የተነሳ የአፈር ለምነት እንዳይቀነስ የእርከን ሥራ (የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ሥራ) በማጠናከር የአፈር ለምነት መመለስ እንደሚቻልም አብራርተዋል። በስልጠናው የአፈር አሲዳማነት፣ የአፈር ጨዋማነት፣ የአፈር መሸርሸር፣ የመስኖ አጠቃቀም ችግሮችና መፍትሄዎቹ የመሳሰሉት ጉዳዮች የተዳሰሱ ሲሆን ሰልጣኞች ያገኙትን ግንዛቤ ተግባራዊ እንዲያደርጉም ተገልጿል።
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02xWWR6dBDyBJWFeDFsnYpSmuyqCttundQAo7MSu8Pe7FH47WrsuZUtfFoNTzBfX1Al/?app=fbl