H̲a̲l̲a̲l̲ ̲l̲i̲v̲i̲n̲g̲ ̲ᶠᵒʰᵃᵐ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Психология


...................꧁﷽꧂.....................

ኢስላማዊ_መረጃዎች
ኢስላማዊ_ታሪኮች
አጫጭር_ዳዕዋዎች እና
የተለያዩ_ሀዲሶችን_ያገኛሉ
አዝናኝ ቀልዶች ☺️
owner 👉 #HAMZA (FOHAM)
ለማንኛውም አስታየት @foham2 አናግሩኝ
ከተሳሳትኩም አርሙኝ✌️ @foham2

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Психология
Статистика
Фильтр публикаций


ከተላመዳቸው ኃጢያቶች በሸዕባን ወር ላይ መቆጠብ ያልቻለ ሙስሊም ረመዳን ሲገባ በአንድ ጊዜ ማቆሙ እንዴት ይቻለዋል?

ሸዕባን የቅድመ ዝግጅትና የመለማመጃ ወር መሆኑን እናስታውስ።


.
ያኔ በልጅነት መስጅድ ቁጭ ብለን በቂርአት እና በጨዋታ ያሳለፍናቸው ጊዜያት ምነኛ ያማሩ ነበሩ 🥰
Foham
@Islamisthis


☕️
     ፉት እያላችሁ……………


ጡፈይሊ የሆነ ቤት ሲገባ የሆኑት ተሰብስበው 🌮ምግብ እየበሉ ያገኛቸዋል።

  "ምንድን ነው ምትበሉት?" አላቸው።
መጃጃሉን ይጠሉት ስለነበር እንዳይበላባቸው ፈልገው "መርዝ ነው" አሉት።

  "እናንተ የሌላችሁበት ሕይወት ዕርም ይሁንብኝ" ብሎ እጁን ሰንዝሮ መብላት ጀመረ።


ቀብር ዚያራ ስትሄዱ ያለው ስሜት🥺 ዱንያ ሙሉ ለሙሉ ታስጠላችኋለች ሀብታም ነው ብላችሁ ያከበራችሁት ባለስልጣን ነው ብላችሁ የፈራችሁት ደሃ ነው ብላችሁ የናቃችሁት ሁሉም ተራ አፈር መሆኑ ይገባችኋል 😔😔 የሚያስጠላው ግን ያ ስሜት ብዙ አይቆይም ከዛ ቦታ ትንሽ ራቅ ስትሉ ለዱንያ መጋጋጥ መጥቶ አይናችን ላይ ድቅን ይላል😔

አላህ የማስተንተን አቅም ይስጠን
@Islamisthis




«ማነው የሚያገባሽ»
-----------------------------
ይህን ሁሉ ቀለም እየተቀባባሽ፡
ተወግዶ ካንች የሴትነት ሀይባሽ፡
ፆታሽ አጠራጥሮ ግራ እየተጋባሽ፡
በቀለሙ ብዛት ሲጠነዛ አበባሽ፡
በቻይና ተሰርቆ ማዕረግና ካባሽ!?
በይ እስኪ ንገሪኝ ማን ነው የሚያገባሽ!?
----------------------------------


⚡️⚡️
ለ ወንዶች ደግሞ👀  .....

ቢክራ (ድንግል) ያልሆነች ሴት ባጠቃላይ ባህሪዋ የተበላሸና " ሴሰኛ " ነች ማለት አይደለም ፡
እንደውም ከተቃራኒ ፆታ ጋር ግንኙነት ሳታደርግ ቢክራነቷ ሊወገድ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ ፡፡
ከነዚህ ውስጥ
➡️የተለያዩ ስፖርቶችን መስራትና
➡️ከባባድ እቃዎችን ማንሳት ይገኙበታል ፡፡

ደግሞም ከዚህ ቀደም ሀራም ግንኙነት የፈፀመች ብትሆንና ዛሬ ላይ ከወንጀሎቿ ሁሉ ፍፁም ተፀፅታ የተመለሰች ከሆነ ምንድነው ችግሩ ፡፡
⚡️ ደም ካላየህ አይሆንልህም እንዴ ?
....አዎ ነው ያልከው ( ? ) .... እንግዲያውስ ደም ከሆነ የምትፈልገው ዶሮ እረድ !😀😁

©reposted

@Islamisthis


   🔖 ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ:-

አንድ ሰው ልጃኣገረድ አግብቶ ቢክራ (ድንግል) ሆና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት??

የሸይኽ መልስ፦ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል፡ ቢክራዋ (ድንግሏ) ያለ ዝሙትም ሊፈርስ ይችላል፡፡ የልጅቷ ውጫዊ ስብዕናዋ መልካም ከሆነ እናም በዲኗ የተስተካከለች ከሆነች በሷ ላይ ጥሩ ግምትና መልካም ጥርጣሬን ማሳደር የግድ ነው፡፡

✔ወይንም አፀያፊውን ዝሙት ሰርታ ከዚያ አላህ መርቷት ከሰራችው መጥፎ ተግባር ተፀፅታና ቶብታም ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያም ወደጥሩነትና መልካምነት ከተቀየረች(ቢክራ)ድንግል አለመሆኗ እሱን አይጎዳውም፡፡

✔ምናልባትም ድንግሏ በወር አበባ ብርታት ምክንያት ፈርሶ ሊሆን ይችላል፡፡ ጠንካራ (ሀይድ)የወር አበባ (ቢክራ)ድንግልን ያፈርሳል፡፡ይህንንም ብዙ ዑለሞች አውስተዋል፡፡

✔ልክ እንደዚሁም በአንዳንድ ዝላዮች ድንግል ሊፈርስ ይችላል፡፡ ከሆነ ቦታ ወደ ሆነ ቦታ ስትዘል ወይም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ዝቅተኛ ቦታ በምትወርድበት ጊዜ በዚህ አጋጣሚ ድንግል ሊፈርስ ይችላል፡፡

✔ስለዚህ የድንግል መፍረስ የግድ በአፀያፊው ዝሙት ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ በጭራሽ ከዝሙት ውጪ በሆነ ክስተት ነው ድንግሌ የፈረሰው ካለች ወይንም በዝሙት ነው ድንግሌ የፈረሰው ግን ተገድጄ እና ተደፍሬ ነው ካለች ይሄ እሱን አይጎዳውም፡፡

✔ወይም በፍላጎቷ ዝሙት ሰርታ ከሆነ ድንግሏ የፈረሰው ግን ያንን ያደረገችው በማታውቅበትና በመሀይምነቷ እንደሆነም እና አሁን ከዚህ ቶብታና ተፀፅታ ከሆነ ይሄም እሱን አይጎዳውም፡፡

✔ይህን የሷን ሚስጥር ሊበትንባትና ሊያሰራጭባ አይገባም ይልቁንስ ሊደብቅላት ይገባል፡፡ በእርሱ ግምት እውነተኛነቷንና ቅንነቷን እናም ማስተካከሏን ካመነበት ከእርሱ ጋር ያቆያታል፡፡ ካሎነ ግን በሷ ላይ ያደረበት ግምት ጥሩ ካልሆነ ይፈታታል ይህም የሚሆነው ግን የሷን ሚስጥር ከመደበቅና ከመጠበቅ ጋር ነው፡፡

    📚ምንጭ መጅሙዕ አል ፈታዋ ሊብኒ ባዝ
                   (287/286-30)


︎ ︎︎⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
              ⚡️ቢክራ (ድንግል)⚡️

ሚስት ለማግባት ስፈልግ ልጃገረድ / ድንግል አግባ ወይም
አግብታ የተፈታች አግባ…… እንዴት? ለምን?


👉👉ምሳሌ1"🎙


አንድ የተፈታ ፔፕሲና ያልተፈታ ፔፕሲ ብታገኝ የትኛውዠን ትመርጣለህ?
ክፍቱን ወይስ እሽጉን? በእርግጠኝነት እሽጉን ፔፕሲ ተሽ አድርገህ ከፍተህ
ያለምንም መወሳወስና ጥርጣሬ ትጠጣዋለህ……… #
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
ድንግል አልባ 😏ምሳሌ 2"=🎙


ክፍት ሆኖ ያገኘኽው ፔፕሲ ትጠጣዋለህ? በሽተኛ ወይም እብድ የከፈተው ይሆን ውስጡ ምን እንዳለብት ምን ገብቶበት እንደሆነ
ሳታውቅ አንስተህ ብጠጣው ውስጥህ ደስተኛ አይሆንም ይቀፍሃል
በእርግጠኝነት ያ ተከፍቶ ያገኘህውን ፔፕሲ ብጠጣው ትዝ ባለህ ቁጥር ውስጥህ ደስተኛ አይሆንም ምክንያቱም ያ ክፍቱ ፔፕሲ ዘልዛላነትን ስለሚገልፅ…… 🙌

አግብታ የተፈታች ምሳሌ 3"


የተከፈተው ፔፕሲ ብምታውቀው ጓደኛህ
በህጋዊ ተከፍቶ ያገኘኸውንና በሜዳ ላይ ተከፍቶ የከረመ ፔፕሲ ቢሰጡህ
የትኛውን ትመርጣለህ?

👍በእርግጠኝነት የምትመርጠው በህጋዊl የተፈታውን ነው ምክንያቱም ያለምንም ጥርጥር ጉዳዩንም ስለምታውቅ ውስጥህ ምንም ሳይቀፍህ ትጠቀማለህ
ስለዚህ ደስተኛ ለመሆን ምርጫህ አንደኛው እና 3 ይሁን ባይ ነኝ 🙌

✍️FOHAM☑️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

@Islamisthis


✨አንድ ወጣት አንድ ሸይኽ ዘንድ ደውሎ አንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦

ያ ሸይኽ ጥያቄ ነበረኝ?
ሸይኹ፦ መርሃባ መጠየቅ ትችላለህ።
ወጣቱ፦ሰለፎቻችን ከቁርዐን ጋር የነበራቸው ሁኔታ እንዴት ነበር? አብራሩልኝ
ሸይኹ፦በአሁን ዘመን ወጣቱ ከስልኩ ጋር እንደማይላቀቀው እነሱም ከቁርዐን ጋር አይላቀቁም ነበር። 


ያለንበት ዘመን እንግዳ ሁኗል!! አንዳንዶች
የተቀደደውን ልብስ ራሳቸውን ለመሸፈን ሲሉ ሰፍተው ይለብሳሉ!!
ሌሎች ደግሞ ራሳቸውን ለማሳየት ሲሉ የተሰፋውን ቀደው ይለብሳሉ!!


እንደ ምዕራባውያን
እየኖርን እንደ ሰሀቦች አይነት
ሞትን የምንሻ ከንቱዎች ነን😭


ትናንት አንተ ማለት…! ሚሉ ሁላ ዛሬ ላይ የልባቸውን ያወሩብሃል። ንግግርህ፣ ሃሳብህ ሁለመናህ ይዘገንናቸዋል። በቃ ይቺ ነች ዱንያ፣ ደህና ወዳጅነት ጀመርኩ ስትል ረጅም የምሬት ጊዜ ታወርስሃለች።ሲጀምርስ ለሷ የተባለ ነገር መች ያምርና!

ከሰው ጋር የሚኖረን ወዳጅነት መሰረቱ ለ አሏህ እስካልሆነ ድረስ መጨረሻው አያምርም። ተጀምሮ የሚቆም ወዳጅነት ከጅምሩም ስሜትን፣ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ለ አሏህ የተባለ አልነበረም። ለ አሏህ በነበረማ ባልቆመ ነበር።

ደስ የሚለው ነገር ያ የተቋረጠው ወዳጅነት የቆመው የ አሏህን ትእዛዝ ከማስከበር ጋር ተያይዞ ከሆነ፤ ብቻ ወደሱ ትእዛዝ እንመለስ እንጂ ያ የቀድሞ ፍቅራችንን እንደሚመልስልን ይህን በማድረግ ላይ ደግሞ ቻይ እንደሆነ በግልፅ ነገሮናል።

﴿عَسَى اللَّهُ أَن يَجْعَلَ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَ الَّذِينَ عَادَيْتُم مِّنْهُم مَّوَدَّةً ۚ وَاللَّهُ قَدِيرٌ﴾ الممتحنة 7

ባይሆን ስላለፈው ማሰቡን ትተን ለሱ ብለን ያጣነውን ነገር እስኪመልስልን በጉጉት መጠበቅ ነው ያለብን!


⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
📦በጣም መፈለግ መለመንን ያስከትላለ➕
📦በጣም መለመን ደግሞ ክብርን ያሳጣል➕
📊ክብርን ስታጣ ደግሞ በወደድከው ነገር ትናቃለክ 🙌
✍️fσнαм

@Islamisthis

204 0 2 21 16

አላውቅም ማለትም መልስ ነው እሺ🥀👆👌


🥀ውዶቼ 🥰
ዛሬ የሸእባን ወር እንደገባ አውቃችኋላ
🥺🥹
እስቲ ይህን ወር ለየት የሚያደርጉት ነገራቶች ጥቀሱ👇


✍ አንድ ቀን ውዱ ነቢያችን ሙሐመድ  ﷺ  አለቀሱ !
ሶሀቦችም ለምን ያለቅሳሉ ያረሱለላህ?

ነብያችንም ﷺ ወዳጆቼ ናፍቀውኝ
ሶሀቦች እኛ ወዳጆቾ አይደለንም እንዴ ያረሱለላህ?

ነብያችን ﷺ  አይ እናንተማ ጓደኞቼ ናችሁ !

ወዳጆቼ ግን ከእኔ በኃላ የሚመጡ እኔን ሳያዩ በእኔ የሚያምኑ ህዝቦቼ ናቸው።

ናፍቀናቸው ባለቀሱት ነብይ ላይ ሰለዋት አውርዱ።

﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ».


اللَّه يرزقني وإياكم الفردوس الأعلىٰ من الجنة.


⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
በአሳነባረ ሆድ ውስጥ ተስፋ ነበር
በእሳት ነበልባል ውስጥም ተስፋ ነበር
በጉድጓድ ውስጥም ተስፋ ነበር
በአላህ ላይ ተስፋ ያረገች ነፍስ አትጎዳም በአላህ ላይ ያለን ተስፋ የማይናድ ይሁን አድራጊው የማይሰስት ጌታ ነውና🩷
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️


ባለ ትዳሮች ተኝተዋል😢

የቀረዉ እኔና አንዳንድ ደጋጎች ናቸዉ
እዚህ አንድ ደግ ይኖር ይሆን ወይስ እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት...😁

ደህና ደሩ🤓

Показано 20 последних публикаций.