❗#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ አባታችን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ::
🔷👉 እነርሱም ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል :: ታዲያ አንድ ቀን አቅሌያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን #ንስኢ_ወልደ_ዘይትሌአል_ቀርኑ_እምኑኀ_ሰማይ " ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ የሚል ድምጽ ሰማች ::
❗ በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ ❗
🔴👉 ፃዲቁ አባታችን አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው " ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን " ብለው በማመስገናቸውና ኋላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላእክትን ይመስላሉ ።
🔵👉 ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመደ ብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ #ፍሱሐ_ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአርገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።
🔷👉 በገድለህ በትሩፋትህ ከሞት ነፍስ ከርደተ ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? #ዘኬድከ_ጸበለ_እግረከ_ይልህሱ_ወበ_ውእቱ_ይጽግቡ ።" የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ ::
🔵👉 ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር ።
🔷👉 ከዚህ በኋላ ሑር ምድረ ኢትዮጵያ " ወበህየኒ ሐልውከ ነፍሳተ ወታወጽኦሙ" ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ #ምድረ_ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ #ዝቋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር ::
🔴👉 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ #ዘገብረ_ተዝካርከ_ወዘጸውአ_ስመከ_እምህር_ለከ " ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከአልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ " #ተንስእ_ወጻእ_መሀርኩ_ለከ_ኵሎ_ኢትዮጵያ ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል ::
✅👉 ከዚህ በኋላ #ምድረ_ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትክል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል :: ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል ::
🔴👉 ለ100 ዓመት ሕዝበ ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለው በዝቋላ ተራራ በሚገኘው ሐይቅ ተዘቅዝቀው ለምነው የምሕረት ቃልኪዳንን የተቀበሉበት እንዲሁም እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው።
❗የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት አይለየን ❗
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 5/2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16