©Legal details center© :የህግ ማብራሪያ ማዕከል©


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ይህ channel ለማንኛውም የፌደራል ና የክልል ህጎችን ማወቅ ና ማሳወቅ ለሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አገልግሎት ይሰጣል ።በዚህ ቻናል ውስ የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኙበታል። ለበለጠ መረጃ የ ዩቲዩብ ገጻችንን ይቀላቀላሉ 👇👇
youtube:https://www.youtube.com/@legaledetailscenter
Tik Tok:tiktok.com/@user2867965117502

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: 🏆
𝐆𝐚𝐚𝐟𝐟𝐢𝐢 𝐁𝐚𝐝𝐡𝐚𝐚𝐬𝐚 𝐐𝐚𝐫𝐬𝐡𝐢𝐢 5000 𝐐𝐚𝐛𝐮 𝐈𝐫𝐫𝐚𝐭𝐭𝐢 𝐇𝐢𝐫𝐦𝐚𝐚𝐝𝐡𝐚𝐚.

𝐀𝐥𝐚𝐚𝐛𝐚𝐚𝐧 𝐒𝐮𝐮𝐫𝐚𝐚 𝐢𝐫𝐫𝐚𝐭𝐭𝐢 𝐀𝐫𝐠𝐢𝐭𝐚𝐧 𝐊𝐮𝐧 𝐊𝐚𝐧 𝐁𝐢𝐲𝐲𝐚 𝐊𝐚𝐦𝐢𝐢𝐝𝐡𝐚?












የቻናል view በቅናሽ ዋጋ እንሰራለን
ለማንኛውም ቻናል ቢሆንም በራሳችን post እርስዎ ወደፈለጉት ነገር edit አድርገው መጠቀም ይችላሉ ደግሞ በነፃ በሚባል ዋጋ
👉1k view በ 25 birr ብቻ

ለማሰራት ከፈልጉ
@gofx19 አናግሩን








የፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በእስራት ተቀጣ
---------------------------------------------
ስልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም እና የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወንጀል በፈጸመ የፍርድ ቤት  ፕሬዝዳንት ላይ የ6 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ቅጣት ማስተላለፉን የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለጸ።

በወንጀሉ ተባባሪ የነበረች ሌላ ግለሰብም የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ማስተላለፉን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ባቡ እንደተናገሩት አንደኛ ተከሳሽ  አቶ ሙሉጌታ መሰረት እና 2ኛ ተከሳሽ ወይዘሮ ፈጠነች በዛብህ በፈጸሙት የሙስና ወንጀል የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን ገልጸዋል።

አንደኛ ተከሳሽ አቶ ሙሉጌታ መሰረት የደቡብ ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛና ፕሬዝዳንት ሆነው እየሰሩ በነበሩበት ወቅት ከሁለተኛ ተከሳሽ በፍርድ ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪና ቼክ ፈራሚ ሆና ከምትሰራው ከወይዘሮ ፈጠነች በዛብህ ጋር ለራሳቸውና ለሌሎች ሰዎች ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ለፍርድ ቤቱ ከተመደበው በጀት ውስጥ ከተቋሙ ስራ ጋር ለማይገናኝ አላማ የተቋሙ ሰራተኛ ላልሆኑ ነጋዴዎች በ2013 ዓ.ም  163ሺ ብር አበል ክፍያ ፈጽመዋል ብለዋል።

በዚሁ መዝገብ ግለሰቧ በ2014  ዓ.ም ለሌላ ነጋዴ 197ሺ 706 እንዲሁም በ2015 ዓ.ም 721ሺ 442 ብር ፣ በ2016 ዓ.ም 309ሺ 822 ብር ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ በድምሩ 1 ሚሊየን 361ሺ 768 ብር በአበል ክፍያ እንዲፈጸም  አድርገዋል ብለዋል።

በዚህም ያለአግባብ ስልጠናቸውን በመጠቀም ወንጀሉ በሚሰጠው  ሙሉ ፍሬ  ተካፋይ ለተቆሙ የተመደበውን በጀት ለታለመለት አላማ እንዳይውል ማድረጋቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

በዚህም የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዐቃቤ ህግ በቀረበለት መዝገብ ላይ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ በትላንትናው ዕለት የቅጣት ውሳኔና ፍርድ ሰጥቷል ብለዋል። በዚህም አንደኛ ተከሳሽ እጃቸው ከተያዘበት ከቀን 27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚታሰብ የ6 ዓመት ጽኑ እስራትና የ7ሺ 500 ብር መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል ብለዋል።

2ኛ ተከሳሽ እጃቸው ከተያዘበት ከቀን 27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚቆጠር በ5 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ5ሺ 500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ፍርድ የተሰጠ ሲሆን አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በጋራ ያጎደሉትን 1ሚሊየን 345ሺ 320 ብር በጋራ እንዲከፍሉ የተወሰነ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ በግል በኦዲት የተገኘባቸውን ተጨማሪ 16ሺ ብር 448 ብር እንድትመልስ ውሳኔ መሰጠቱን ገልጸዋል።

አቶ ቢኒያም በመጨረሻም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የሙስና ወንጀሎች አይነትና የመፈጸሚያ ስልቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መምጣታቸውን ገልጸው ህዝቡ ሙስናን በመፀየፍና ተፈጽሞ ሲገኝ ጥቆማ በምስጠት የዜግነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።


የሠ/መ/ቁጥር 205068 ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ/ም
ስራ መሪ ትርጓሜ ስያሜ ስራን መሪን በመወሰን ረገድ ያለው አግባብነት
የአንድ የሥራ መደብ መጠሪያ ሥራ አሥኪያጅ የሚል መጠሪያ መያዙ ብቻዉን በመደቡ ላይ ተመድቦ የሚሰራዉን ሰዉ የሥራ መሪ ስለማያሰኘዉ የሥራ መዘርዝሩ ላይ የተሰጠዉን ተግባርና ኃላፊነት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2/10 ስር ለሥራ መሪ ከተሰጠዉ ትርጓሜ ጋር አገናዝቦ መመርመር ያስፈልጋል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሥራ መሪ የሚባለዉ በሕግ ወይም እንደ ድርጅቱ የሥራ ጠባይ በአሠሪዉ በተሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን መሰረት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማዉጣትና የማስፈጸም ሥልጣን ያለዉ ወይም ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዛወር፣ የማገድ፣የማሰናበት ወይም የመመደብ ተግባሮችን የመወሰን ሥልጣን ያለዉ ግለሰብ ሲሆን እነዚህን የሥራ አመራር ጉዳዮች አስመልክቶ የአሠሪዉን ጥቅም ለመጠበቅ አሠሪዉ ሊወስደዉ ስለሚገባዉ እርምጃ በማንም ሳይመራ የራሱን የዉሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ የሕግ አገልግሎት ኃላፊ ጭምር እንደሆነ ተደንግጓል፡፡በዚህ ድንጋጌ ላይ “…በአሠሪዉ በተሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን…”የሚለዉ አገላለጽ ድርጅቱ ግኡዝ እንደመሆኑ ድርጅቱን ወክሎ የመሪነት ሥራን የሚሰራ ሰዉ ለማለት እንጂ ለአጭር ጊዜ በድርጅቱ ሥራ መሪ ተወክሎ የሚሰራ ሰዉ ለማለት አይደለም፡፡ምክንያቱም በድርጅቱ ሥራ መሪ ጊዜያዊ ዉክልና የሚሰጠዉ ሰዉ ከመነሻዉ ከድርጅቱ ጋር ያለዉ የቅጥር ግንኙነት በአዋጁ አንቀጽ 2/10 ስር የተዘረዘሩትን ተግባርና ኃላነቶች እንዲፈጽም ሥልጣን የሚሰጠዉ ላይሆን ስለሚችል ነዉ፡፡በያዝነዉ ጉዳይ በድርጅቱ ለተጠሪ በተሰጣቸዉ የሥራ መዘርዝር ላይ ተጠሪ እንዲሰሩ የተሰጣቸዉ ተግባርና ኃላፊነት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማዉጣትና የማስፈጸም ወይም ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዛወር፣ የማገድ፣የማሰናበት ወይም የመመደብ እንዳልሆነ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ተረድተናል፡፡የአመልካች ኃላፊ ለአጭር ጊዜ ለተጠሪ በሰጧቸዉ ዉክልና የፈጸሙት ተግባር ተጠሪን የሥራ መሪ የሚያሰኛቸዉ አይደለም፡፡በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የተጠሪን የሥራ መዘርዝር መሰረት በማድረግ ተጠሪ የሥራ መሪ አይደሉም በማለት በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም ብለናል፡፡






#እንድታውቁት

ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፦

➡ ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

➡ አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

➡  የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

➡ ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

➡ ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

➡ አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

➡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

➡ ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።


1. ሕፃናት በፍ/ቤት ለማስረጃነት የሚውል የዘረ መል (DNA) ምርመራ ለማድረግ አይገደዱም፤ ምርመራውን ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ብቻውንም እንደ በቂ ማስረጃ ተቆጥሮ "ሕፃኑን DNA ለማስመርመር ፈቃደኛ ያልተሆነው ልጁ የባልዬው ባይሆን ነው" የሚል  የሕግ ግምት [የፍ/ሕ/ቁ. 22ን ልብ ይሏል] በመያዝ ባልዬው የልጁ አባት አይደለም ብሎ መወሰን ሕገ መንግሥቱን የሚቃረን ነው::
2. በጋብቻ ውስጥ የተወለደን ልጅ ልጄ አይደለም በማለት (አባትነትን ለመካድ) የሚቀርብ ክስ በጠባቡ ሊታይ የሚገባና የክስ ማቅረቢያ ጊዜውም ባልዬው የልጁን መወለደ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ ባሉት 180 ቀናት ውስጥ የመሆኑ ይርጋ የሕፃናትን ሕገ መንግሥታዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከሌሎች ይርጋዎች የተለየ ስለሆነ በአንድነት ሊታይ የማይገባ እና ተከራካሪ ወገኖች ባያነሡትም እንኳን ፍ/ቤቶች በራሳቸው አንሥተው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ ነው::
ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 94/13
ግንቦት 30/2013 ዓ.ም
=================
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
https://t.me/judgeoffed


በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ተጠየቀ

***

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥር 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅን ፍላጎት ለማስከበር ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞው አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች ጠይቀዋል።

የአሜሪካ ፌደራል ዓቃቤ ሕጎች፣ ከግብጽ መንግሥት ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብና የወርቅ ሥጦታ በመቀበል የግብጽን ጥቅም ለማስጠበቅ በሞከር ጥፋተኛ በተባሉት የቀድሞው የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ ቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስራት ቅጣት እንዲጣልባቸው ጠይቀዋል።

ሜኔንዴዝ ጥፋተኛ ከተባሉባቸው ክሶች መካከል፣ የኢትዮጵያና ግብጽ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለመፍታት በሚደረገው ድርድር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሚና እንዲጫወት በመጠየቅ ያልተገባ ተጽዕኖ ለመፍጠር ሞክረዋል የሚል ይገኝበታል።

ክሱን ተከትሎ ሜኔንዴዝ የምክር ቤቱን መቀመጫቸውን መልቀቃቸው አስታውሶ ሲኤንኤን ዘግቧል። የፌደራሉ ፍርድ ቤት በሜኔንዴዝ ላይ የእስር ብይኑን ጥር 21 ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞው የኒው ጀርሲው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የውጭ መንግሥት ፍላጎትን ለመፈጸም ሥልጣናቸውን መጠቀም፣ ጉቦ መቀበል፣ ማጭበርበር፣ ፍትሕን ማደናቀፍን ጨምሮ በ16 የወንጀል ድርጊቶች ተከሰው በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!
#Federalerhicsand anticorroption
================
=




ዛሬ የፀደቀው የንብረት ማስመለስ አዋጅ
ያካተታቸው አንኳር ነጥቦች።

~>  ይህ አዋጅ ተፈፃሚ ከመሆኑ በፊት ባሉት አስር ዓመት ውስጥ ወይም
ተፈፃሚ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የተገኘ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን
ለማስመለስ በዚህ አዋጅ መሰረት ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ክስ ሊቀርብ
ይችላል፤
~>  የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ
ለማስረዳት የወንጀል ሃላፊነት የሚያመጣበት ማስረጃ ቢሰጥም በወንጀል
ችሎት በራሱ ላይ ማስረጃ ሆኖ አይቀርብም፤

~>  ዐቃቤ ሕግ ምንጩ ያልታወቀ ነው ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ንብረት ዝርዝር
እና የተገኘበትን አግባብ የሚያሳይ መግለጫ እንዲያቀርብ በፅሁፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል
~>  የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ ለማስረዳት
የሚያቀርበው ማስረጃ ህጋዊ መሆን አለበት፤
~>  ማንኛውም ሰው ጥያቄው በደረሰው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለዐቃቤ ህግ ዝርዝር
ማስረጃዎችን በማያያዝ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል፤
~>  ዐቃቤ ሕግ ወይም መርማሪ ንብረቱ እንዲታገድ ወይም እንዲያዝ ለፍርድ ቤት
ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል፤
~>  በንብረቱ ላይ የእግድ ወይም የመያዝ
ትዕዛዝ የተሰጠ እንደሆነ፥ ትዕዛዙ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ሶስት ዓመት
ጊዜ ውስጥ በተጠርጣሪው ላይ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረበት የወንጀል ክስ
ወይም ንብረቱን የማስወረስ ክስ ካልቀረበ የተሰጠው የመያዝ ወይም የእግድ ትዕዛዝ
ቀሪ እንዲሆን ባለንብረቱ ወይም ተጠርጣሪው ለፍርድ ቤት ሊያመለክት ይችላል፥
~>  በዚህ አዋጅ ስለንብረት ማገድና መያዝ የተደነገገው ድንጋጌ ቢኖርም፡-
ሀ/ የተጠርጣሪው፣ የተከሳሹ፤ የፍርደኛው ወይም በስሩ ለሚተዳደሩ የቤተሰብ
አባላት የእለት መተዳደሪያ ወይም ሙያዊ ስራ ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ
ቁሳቁሶች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች፤
~>  ለ/ ለተጠርጣሪው፣ ለተከሳሹ፥ ለፍርደኛው ወይም በስሩ ለሚተዳደሩ
የቤተሰብ አባላት የዕለት ኑሮ ጠቃሚ የሚሆኑ እና ከስድስት ወር ላልበለጠ
ጊዜ ወይም ፍርድ ቤቱ በልዩ ሁኔታ ለሚወስነው ጊዜ የሚሆን ስንቅ፤
እንዳይታገድ ወይም እንዳይያዝ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፤
~>   በሌሎች ሕጎች በሚወጡ ድንጋጌዎች መሰረት ከክስ ነጻ የሚደረግ እና
በወንጀል ክርክር ሂደቱ ወደ ምስክር የዞረ የወንጀል ተካፋይ የሆነ ሰው
በወንጀል ድርጊቱ ያገኘው ንብረት እንዲመልስ ወይም ያደረሰው ጉዳት
እንዲክስ ይደረጋል፤

ተጨማሪ መረዳት ለማግኘት ከላይ በ pdf የተያያዘውን የአዋጁን ሙሉ ክፍል ያንብቡ



Показано 20 последних публикаций.