Репост из: 🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹
✓ ተፍሲር ሱረቱ ኒሳዕ ...
ሱረቱ አለ ኢምራን የጨረሰው «ያአዩሃለዚነ አመኑ ኢስቢሩ ወሷቢሩ ወራቢጡ “ወተቁሏህ” » በማለት "አማኞችን" በማናገር ነበር ፣ ሱረቱ ኒሳዕ ደግሞ ሲጀምር ይህንኑ የተቅዋ ትዕዛዝ "ለመላ የሰው ዘሮች" በማስተላለፍ ነው «ያአዩሃናሱ ኢተቁ-ረበኩም..»
ቁጥሩ ይርቃል እንጂ ዞሮ ዞሮ የሰው ልጅ ሁላ ዘመዳም መሆኑን "ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁ" በማለት ነገረን ፡ በመቀጠል "ዝምድናን ጠብቁ" ይለንና ዘመድ የሌለው እንዳይረሳ ደግሞ ስለ የቲሞች ይነግረናል። ዘመድ ነኝ በሚል የየቲም ብር እንዳይበዘበዝ "ኢነሁ ካነ ሁበን ከቢራ" በማለት የየቲም ገንዘብ መብላት ከሰባቱ ትላልቅ ሀጢአት አንዱ መሆኑን ያስታውሰናል።
وَإِنْ خِفْتُمْ أَلاَّ تُقْسِطُواْ فِي الْيَتَامَى
ይህን አያ ለመረዳት ለምሳሌ የሚያሳድጋት የቲም ልጅ ለጋብቻ ሀላል የሆነች የአጎትን ልጅ ምናምን ሊያሳድግ ይችላል ፣ መጨረሻ ግን እድሜዋ ሲደርስ ቆንጆ ከሆነች ወይም ለብሯ ብሎ ሌላ ሰው ከሚያገባት እኔ ላግባት ይልና መህሯን ቀነስ አድርጎ ለራሱ ያገባታል ፣ ይሄ አድሎ ነው! ካገባሃት ከሌላ ሚስትህ ጋር እኩል አድርገህ ወይም ደግሞ እሷን የሚመጥን ኑሮ ላይ ማኖር ግዴታ ነው። ይህን ማድረግ አልችልም ካልክ ግን ለገንዘቧ ፣ ለውበቷ ፣ ለዲኗ የሚፈልጋት ይኖራል .. እድሏን ትጠብቅ ፣ ገንዘቧን አስረክብ ! አንተ ማስቀረት አይፈቀድልክም ነው ። "ፈንኪሁ" ሲል ሌላ የተፈቀደላችሁን አግቡ ሁለት ፣ ሶስት ፣ አራት ተፈቅዶላችኋል ። ሺዓዎች "መስና" የሚለውን 2×2 ፡ ሩባዕ የሚለውን 4 ሲባዛ በ4 በማለት ነው የሚፈስሩት ፤ ይህ ግን በቋንቋ ደረጃም ስህተት ነው ። ለምሳሌ ስለ መላኢኮች ክንፍ ሲነግረን "መስና" ሲል እያንዳንዳቸው ሁለት ክንፍ ያላቸው ፣ "ወሱላስ" ሲል አንዱ ሶስት ሌላኛውም ሶስት ያላቸው እንጂ 3 ሲባዛ በ3 ማለት አይደለም ።
እስከ 4 ተፈቅዷል ሲባል ታዲያ ፍትህ ሊኖር ግድ ነው ። ፍትህ ሲባል ...በልብሳቸው፣ በመኖሪያቸው ፣ በቀለባቸው፣ በሚደረገው ነገር ሁሉ እኩል ማድረግ አለበት! እዚች ሁለት ቀን ካደረ እዛች ሁለት ቀን ማደር ግዴታው ነው ። ወደ መንገድ ሲሄድም መጀመሪያ እጣ መጣል አለበት ፣ ሁለተኛው ግን የሌላይቱ ይመጣል በዚህ መልኩ ነው የተደነገገው ። በቁሳዊ ነገር እኩል ማድረግ ግድ ነው በተቻለ መጠን ..
ነገር ግን ፍቅርን እኩል መክፈል አይቻልም ። አንዷ ዘንድ የሚያገኘውን ሌላዋ ዘንድ ካላገኘ (በባህሪዋ ፣ በውበቷ ፣ በኺድማዋ ...በተለያየ ነገር) ወደ አንዷ ልቡ ሊዘነብል ይችላል፤ ይሄ ከአቅም በላይ የሆነው አፍው ይደረጋል ። ይህን ሲያመለክት እዚሁ ሱራ 129 ላይ «በሴቶች መካከል 100% እኩል ልታደርጉ አትችሉም ጉጉት እንኳ ቢኖራችሁ ታዲያ ሙሉ ለሙሉ እንዳታዘንብሉ ተጠንቀቁ» ብሎናል ። ረሱልም ሁሉንም ነገር ያከፋፍሉና «ሀዛ ቀስሚ ፊማአምሊክ፡ፈላቱአሂዝኒ ፊማ ላአምሊክ/እኔ በምችለው ይሄ ነው የኔ አከፋፈል ፤ በማልችለው አትያዘኝ ፣ አትውቀሰኝ ጌታዬ» ይሉ ነበር ። ይህን ያህል ጥንቃቄ ካደረገ ከዛ ውጭ ያለውን አሏህ አፍው ይላል ማለት ነው ።
فَإِنْ خِفْتُمْ أَلاَّ تَعْدِلُواْ فَوَاحِدَةً
❝አለማስተካከልን ብትፈሩ አንዲትን ብቻ አግቡ!❞
ሊኩሊ ሳቂጠቲን ላቂጥ / የወደቀ ሁሉ አንሺ አያጣም እንደሚባለው ..ሁሉም ሰው ቢጤውን ፈልጎ እራሱን ኢዕፋፍ ማድረግ ያስፈልጋል። መጀመሪያ "መስና " በማለት በሁለት ነው የጀመረው .. ሸሪዓው የሰው ዘር እንዲበዛ ይፈልጋል፣ ነብዩም ﷺ ወላድና ወዳድ አግቡ "ፈኢኒ ኡካሲሩ ቢኩሙል ኡመም" ብለዋል ።
ذَلِكَ أَدْنَى أَلاَّ تَعُولُواْ
የሚለው ሁለት ትርጉም አለው፦ አንደኛው - ግፍ አንዳትሰሩ ፣ አድሎ ውስጥ አንዳትገቡ በአንድ ተብቃቁ እንደማለት ሲሆን ሁለተኛው ፍች ደግሞ እንዳትደኸዩ ማለትም ይሆናል ፥ ቤተሰብ ሲበዛ ከገቢህ ጋር የማይመጣጠን ከሆነ አቅምህን ያንገዳግዳልና በአንድ ተብቃቃ ተብሎም ይፈሰራል።
وَاتُواْ النَّسَاء صَدُقَاتِهِنَّ نِحْلَةً
"ሶዱቃ" የሚለው ቃል ሲድቅ ከሚለው ይመሰሰላል ፡ ትዳሩን ሷዲቅ የሚያደርገው መህሩ ነው በማለትም ይፈስሩታል ፣
“ኒህላ” የሚለው ግዴታ ወይም ካንተ በጎ ፈቃደኝነት ማለት ነው። ደስ እያለክ out of love ስጥ እንጂ ምን ይሄን ሸክም ቶሎ ሰጥቼ ልገላገል¡ በሚል መንፈስ አይሁን! ብዙ ሰው መጀመሪያ ላይ መህር ቃል ሲገባ አይፈራም ። ደግሞ መህርን ሙሉ ለሙሉ ዱቤ አድርገነዋል ማህበራችን ውስጥ :) አላያችሁም ለሰርጉ ብዙ ሺዎችን ያወጣና መህር ላይ ሲመጣ ወደፊት የሚከፈል ይላል፣ ወደፊት ስለሆነ ቀላል ይመስለዋል .. አንድ ቀን አብሮ ካደረ ጀምሮ በእርሱ ላይ ዋጂብ ነው። ቢሞት እንኳ ሰው ዞልሞ ነው የሚሞተው ማለት ነው። ደስ እያለው መስጠት ተገቢ ነው ፣ ሀዲያ አንደሚሰጥ ሰው (romantic gift) ያድርገው ነው ሀሳቡ ። እዳ ነው ፣ ሸክም ነው በሚል መሆን የለበትም ። ህይዎቷን ሰጥታካለች ፤ አንተም ህይወትክን ሰጥተካታል ..ገንዘብ ሊያጨቃጭቅ አይገባም ።
ባይሆን ሴቷም ይቅርብኝ ካለች ወይም ከሰጣት በኋላ ይህችን ለእንዲህ አድርግባት ብላ ከሰጠችው በፍቃደኝነት ከሆነ ችግር የለውም።
فَإِن طِبْنَ لَكُمْ عَن شَيْءٍ مِّنْهُ نَفْسًا فَكُلُوهُ هَنِييًا مَّرِييًا
በፈቃደኝነቷ ከሰጠችህ እኔው ሰጥቼ እኔው ልጠቀምበት? ብለህ አትሳቀቅ ፥ ተጠቀምበት take it, and enjoy it ! በመሰረቱ የሰዎቹ መፈቃቀር ነው እንጂ የሚፈለገው ገንዘቡ አይደለም .. ገንዘቡ ይመጣል ይሄዳል « አልማሉ ዚሉን ዛኢል» ይላሉ .. ብር እንደ ጥላ ነው አሁን ያንዣብባል አሁን ይጠፋል!
ይቀጥላል ..!
መልካም መስሎ ከታያችሁ ሸር አድርጉት ፣ በጋራ ምንዳ እናግኝ
خيركم من تعلم القرآن وعلمه
https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0