##የሰው ዘር
#መቼ ተፈጠረ።
የዓለም ሊቃውንት እንደሚሉት ሰው የተፈጠረው ከሰባ ሚሊዮን ዓመታት በፊት ነው። ሰው ኑሮውን ለማሻሻል የጀመረበት ጊዜ ሊቃውንቶች ሲናገሩ ከ12 ሚሊዮን አሥር ሺህ ዓመታት በፊት ጀምሮ ነው።
ሊቃውንት የሰው ዘር ከብዙ ዓመታት በፊት መኖሩን ያወቁበትን ማስረጃዎች ያቀርባሉ። በ1959 ዓ.ም ሐምሌ 17 ቀን የሰው ዘር አጥኒ ጓድ የሆኑት ወይዘሮ ሜሪ ሊኪ በታንጋኒካ ውስጥ ኦልድባይ ጐርጌ የተባለ ቀበሌ አንድ የሰው ጭንቅላት ከነጥርሶቹ አግኝተዋል። ያ የተገኘው የሰው ጭንቅላት ከአንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ዓመታት በፊት በሕይወት የነበረ ሰው መሆኑ ተረጋግጧል።
በ1961 ዓ.ም በኬንያ ውስጥ ዶክተር ሎይስ ያገኙት የሰው ጭንቅላት ተመርምሮ አሥራ አራት ሚሊዮን ዓመታት ዕድሜ እንዳለው ታውቋል። በቻይና ውስጥ የተገኘው የሰው አፅም ስምንት ክንድ ወይም 12 ጫማ ርዝመት ስላለው ከ500.000 ዓመታት በፊት የነበሩት ሰዎች ረጃጅሞችና ግዙፎች መሆናቸውን ተረጋግጧል።
መጽሐፊቱ ጠቅላላ የሳይን ዕውቀትን የምትገልጽ ባለመሆንዋ ባጭሩ ለማወቅ ያህል የሰው አፈጣጠርና ታሪክ በዚህ ያበቃል። አሁን ወደ ቅርቡ ዘመን እንመለስ።
ከእውቀት በጳውሎስ ኞኞ