እኔና አንቺ
(በረከት በላይነህ)
በጥምር ነፍሳችን አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል
ፍራፍሬው ይከበናል
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ
ኮከቦቹ!
"ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ
ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት የምድር የሰማይ በር
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር
ሁሉን ይሸምታል ፍቅር ሲዘረዘር
#bereketbelayneh
#kemetsihaftmender
@kemetsihaf
@kemetsihaf
(በረከት በላይነህ)
በጥምር ነፍሳችን አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል
ፍራፍሬው ይከበናል
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ
ኮከቦቹ!
"ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ
ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት የምድር የሰማይ በር
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር
ሁሉን ይሸምታል ፍቅር ሲዘረዘር
#bereketbelayneh
#kemetsihaftmender
@kemetsihaf
@kemetsihaf