እንደ ቀልድ ፈገግ
(በላይ በቀለ ወያ)
አንቺ እንደምን አለሽ? እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ሳቄ ይቀድመኛል
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው
እየሳቁ ውሎ እየሳቁ ማደር
ውሸት ነው አትመኝ
እዚህ ሀዘን የለም ሳቅ ነው የተረፈን
ህመም ለቆ ይሔዳል
"አመመኝ አመመኝ" ፣ በሚል አንድ ዘፈን።
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ምኔ እንደታመመ?
አያስቅም ታዲያ?!
#belaybekeleweya
#kemetsihaftmender
@kemetsihaf
@kemetsihaf
(በላይ በቀለ ወያ)
አንቺ እንደምን አለሽ? እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ሳቄ ይቀድመኛል
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው
እየሳቁ ውሎ እየሳቁ ማደር
ውሸት ነው አትመኝ
እዚህ ሀዘን የለም ሳቅ ነው የተረፈን
ህመም ለቆ ይሔዳል
"አመመኝ አመመኝ" ፣ በሚል አንድ ዘፈን።
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ምኔ እንደታመመ?
አያስቅም ታዲያ?!
#belaybekeleweya
#kemetsihaftmender
@kemetsihaf
@kemetsihaf