አተርፍ ባይ
(በላይ በቀለ ወያ)
የሀገሬ ገበሬ
ንቃቃት መሬት ላይ ስንዴውን ይዘራል
ወፍ እዳይበላበት
ከማማ ላይ ወቶ ሲጠብቅ ይኖራል
ማልደው የተነሱ
የተራቡ ወፎች ሰብሉ ላይ ሲያርፉ
መወርወሩን እንጂ
መምታቱን የማያይ
ከገበሬ ጋራ እውር ነው ወንጨፉ
ለወፍ ባሉት ጠጠር
ወፍ ይመግባሉ
ወፍ በሳተ ጠጠር ስንዴ እያረገፉ
#belaybekeleweya
#kemetsihaftmender
@kemetsihaf
@kemetsihaf
(በላይ በቀለ ወያ)
የሀገሬ ገበሬ
ንቃቃት መሬት ላይ ስንዴውን ይዘራል
ወፍ እዳይበላበት
ከማማ ላይ ወቶ ሲጠብቅ ይኖራል
ማልደው የተነሱ
የተራቡ ወፎች ሰብሉ ላይ ሲያርፉ
መወርወሩን እንጂ
መምታቱን የማያይ
ከገበሬ ጋራ እውር ነው ወንጨፉ
ለወፍ ባሉት ጠጠር
ወፍ ይመግባሉ
ወፍ በሳተ ጠጠር ስንዴ እያረገፉ
#belaybekeleweya
#kemetsihaftmender
@kemetsihaf
@kemetsihaf