ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉና ያዝናናሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ ቦታዎች እየለቀምኩ አቀርባለሁ። ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለክ። እዚህ የሚለቀቁ ፅሁፎች እኔ የተናገርኳቸው እና የፃፍኳቸው ብቻ አይደሉም። ከመፃፍ፣ከሶሻል ሚዲያ እና ከተለያዩ ሰዎች የሰበሰብኳቸው ጭምር ናቸው።
Any comment @jer21

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

"በተቻለኝ መጠን ሁሌ የምሰብካት ስብከት አለችኝ፣ የምሬን! ጠዋት ስትነቃ ተመስገን በል! በረከቶችህን ቁጠር፣ ርዕሷ ነች ይህቺ!!"

"ጧት ስትነሳ ተመስገን በል፣ ምክንያቱም ሞተህ ልታድር ትችል ነበራ! ከአልጋ ወርደህ ስትቆም ተመስገን በል፣ በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበር!!"

"ከዛ ደግሞ ተነስተህ ስትንጠራራ ተመስገን በል! መንጠራራት ደስ አይልም፣ ተንጠራርተህ ድብርትህን ስታስለቅቅ? ድብርትን እንዲህ ማስለቀቅ እንድትችል አድርጎ የፈጠረህን፣ ይኼን የሰጠህን ተመስገን አትልም?"

"ቀጥለህ የፊኛና የጎረቤቱን ጥያቄ ታስተናግዳለህ ተመስገን በል! አንዱ ወይም ሌላው እንቢ ሊልህ ይችል ነበራ። ሽንትህን ወጥሮህ ስትሸና የሚኖርህን ጤንነትና ዕረፍት ያላቸውን ዋጋስ?"

"መሽናት ባትችል የሚያስከትልብህ ጭንቀትና ህመምስ? የጠጣኸው ውሃ ሽንት ሆኖ መውጣቱ ይሄ የማናውቀው ተዓምር ውስጣችን በመስራቱ ተመስገን አትልም?"

"ከዛ በሗላ ወጥተህ ስትሄድ መንገዱ ሁሉ ጤና ነው፤ ታክሲው፣ ሰዉ፣ ምኑ፣ ለማኙ፣ መነኩሴው... ስታይ ተመስገን በል! ምክኒያቱም ሰጥ አርጋቸው የሚባሉ ጄኔራል ጨለማን ተገን አድርገው በታንክ ገብተው ሀገሩ ፀጥ ብሎ ቢቆይህስ? ምን ታደርግ ነበር?"

"የምግብ ጉዳይስ፣ ተመስገን! እያልክ ብላ። ዊልያም ሼክስፒር እንደሚለው 'እግዜር ምግብ ይሰጥና ሆድ ይከለክላል፤ ወይ ሆድ ይሰጥና ምግብ ይከለክላል' ሊሆንብህ ይችል ነበራ። ለአንተ ግን ጤነኛ ሆድም የሚጥም ምግብም ሰጥቶሃል፤ ተመስገን አትልም?"

"ከዚህ በኋላ ስራ ለመሄድ ትነሳለህ። ሌላ በረከት! ስራ ለመሄድ ሳይሆን ስራ ፍለጋ ለመሄድ ልትወጣ ትችል ነበራ። በረከቶችህን አንድ በአንድ ቁጠር ማለቂያ የለውም። ያለህ ከሌለህ ይበልጣልና ተመስገን በል!"

✍️ ጋሽ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን🙌

@kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ እንዴት ናችሁ🙏

የኦቶማን ንጉስ አህመድ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን (ቆንጆዋን ንግሥት) በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈት እና ሚስቴን አግባት”ብሎት ፈረሱ ላይ ወጥቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ።

ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው አቧራማ ንፋስ እንዳለ አየ። ቆም ብሎ ሲቃኝ ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየሮጠ ሲመጣ ተመለከተ።

"ምነዉ ምን ሆንክ?" ብሎ ንጉሱ ጠየቀ።

በጣም ከመሮጡ የተነሳ ትንፋሹ እየተቆራረጠ ጓደኛው ሙሳ “የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ” ሲል መለሰ።

ምንድን??? ብሎ አይቶት በድንጋጤ እና በመገረም አየዉ።

ቁልፎቹን ለመሞከር ለ4 ቀናት ይቅርና ለ1ሰአት እንኳን አልጠበቀም።

✍️ አንዳንዴ ጠላትን ስንፈራና ስንሰጋ ገዳያችን እዛ ከጉያችን የጓደኛነትን የወዳጅነትን ጭንብል ለብሱ እናገኘዋለን።

እናም "ጠርጥር እንዳትመነጠር" ነው ጨዋታው።

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን🙌

@kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ🙏

በዓለም ታዋቂዋ የፋሽን ዲዛይነር እና ደራሲ "ክሪስዳ ሮድሪጌዝ" በካንሰር ህመም ተሰቃይታ ከመሞቷ በፊት ይህን ጽሁፍ ጽፋ ነበር...

1. በአለማችን ውዱ ብራንድ መኪና ጋራዥ ውስጥ አለኝ፤ አሁን ግን በዊልቸር ነው የምጓዘው።

2. ቤቴ በሁሉም ዓይነት ብራንድ ልብሶች ፣ ጫማዎች እና ውድ እቃዎች የተሞላ ነው። ነገር ግን ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ አንሶላ ተጠቅልሏል።

3. በባንኬ ውስጥ በቂ ገንዘብ አለ፤ አሁን ግን ከዚህ ገንዘብ ምንም ጥቅም እያገኘሁ አይደለም።

4. ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነው ግን በሆስፒታል ውስጥ ባለ አልጋ ላይ ተኝቻለሁ።

5. ከአንድ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ሌላ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሄድ እችላለሁ።

አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከላቦራቶሪ ወደ ላብራቶሪ እየተዘዋወርኩ ነው።

6. በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ፈርሜያለሁ፤ አሁን ግን የዶክተሩ ማስታወሻ ነው የኔ አውቶግራፍ።

7. ፀጉሬን ለማስጌጥ ሰባት የውበት ባለሙያዎች ነበሩኝ፤ ዛሬ በራሴ ላይ ፀጉር የሚባል ነገር የለም።

8. በግል ጀት ወደፈለግኩበት ቦታ መብረር እችል ነበር፤ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በረንዳ ለመድረስ የሁለት ሰዎች እርዳታ እፈልጋለሁ።

9. ብዙ ምግብ ቢኖርም፥ የእኔ አመጋገብ ግን በቀን ሁለት ክኒን እና ማታ ደግሞ ጥቂት ጨዋማ ውሃ ነው።

ይህ ቤት ፣ ይህ መኪና ፣ ይህ ጀት ፣ ይህ የቤት ዕቃ ፣ ብዙ የባንክ አካውንቶች እንዲሁም ታዋቂነት ምንም አልጠቀሙኝም። ከእነዚህ ውስጥ ምንም እፎይታ ሊሰጠኝ አልቻለም።

እውነተኛ ህይወት፥ ብዙ ሰዎችን ማጽናናት እና ፊታቸው ላይ ፈገግታ እንዲሰፍን ማደረግ ማስቻል ነው።

"ከሞት በስተቀር ምንም እውነታ የለም!!"

🙌መልካም ምሽት! የነገ ሰው ይበለን🙌

@kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

"በመታነጽ ላይ ሳለህ የቦዘንክ ቢመስላቸው አትደነቅ!"

ድሮ እኛ ሃይ ስኩል ስንማር 'ከመማር ይልቅ ፋብሪካ መሥራት ይሻላል' ብለው ትምህርት አቋርጠው ሥራ የገቡ ጓደኞቻችን ነበሩ።

እነዚህ ጓደኞቻችን ወድያው በወሩ ደመወዝ አገኙ፤ ልብስ ቀየሩ። ሲቆዩ ቤት ተከራዩ፤ አልጋና ፍራሽ ፣ ቁምሳጥን ፣ ወንበርና ጠረጴዛ ገዙ። ጓደኛ ያዙ፤ ኬክ ጋበዙ። ኋላም አንዳንዶቹ አግብተው ሌሎቹም በውጭ ወለዱ።

ያኔ ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ በኋላ አንዱ ወዳጄ አገኘኝና "አሁንም እየተማርክ ነው?" አለኝ። አዎ! ነበር መልሴ። "አይደክምህም? አይሰለችህም?" አለኝ። "አሁን እኮ ልጨርስ ነው" አልኩና ተለየሁት።

ከዓመት በኋላ እኔ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ይዤ ሥራ ስጀምር የወዳጄ ደመወዝ የእኔን ሩብ ያህል ነበር። ከብዙ ዓመታት በኋላ አንድ ምሽት ላይ ወዳጄን አገኘሁት። "ከየት ነው?" ስለው "ከትምህርት" አለኝ። የማታ ትምህርት ጀምሮ ነበር። በቀን "አይሰለችህም?" ያለኝን እሱ በማታ መትጋት ጀምሮበት ኖሯል። "ህምምም..." ብዬ "ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?" ስለው እኔ ቀን የተማርሁትን እጥፍ ጊዜ ጠራልኝ።

አንዳንዱ እንዲህ ነው። መጀመሪያ ሳይታየው ኋላ ከረፈደ እጥፍ ዋጋ ሊከፍል ይገደዳል። ስኬት ቀድሞ በመራ አይደለም። ከእውቀት ሥራን ባስቀደመም አይደለም። ሥራ በዕውቀት ካልሆነ ልፋት ነው።

6ተኛ ፎቅ ላይ በፓምፕ እየተገፋ ኮንክሪት ሲሞላ አይተሃል? ያ በእውቀት የሚሠራ ነው። ያለእውቀት የሚሠራው ግን በባሬላ እያጋዘ ይደክማል።

ትጋት እና ልፋት ይለያያሉ። ትጋት የእውቀት ሥራ፤ ልፋት ደግሞ ተቃራኒው ነው። ትጋ እንጂ አትልፋ!

በልፋት የትም አትደርስም። ይልቅ ጭንቅላትህን አጎልምስ።

💎አየህ አንተ ስትታነጽ ፣ ስትተጋ ማንም ልብ አይልህም። ያንተ ራስን ማነጽ አርቀው ለማያስቡት ቦዘኔነት ነው። ሲያዩህ መሬት አትቆፍርም ፣ እንጨት አትልግም ፣ ምስማር አትመታም ፣ ልብስ አትሰፋም ፣ ዳቦ አትጋግርም ፣ መርፌ አትወጋም። ለእነርሱ አንተ እየቦዘንክ ነው።

መጨረሻ ተሳክቶልህ ፣ በኑሮ ከፍ ብለህ ሲያዩህ ግን "እድለኛ ነህ" ይሉሃል። እውነት ነው እድል ማለት ስትተጋ ሳትታይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻል ነው።

ስንዴዋ አፈር ውስጥ ገብታ ስትበሰብስ ውጤቱን ለሚያውቀው ለገበሬው እንጂ ለሌላው ብክነት ነው። ሌሎች ውጤቱን የሚያዩት ስንዴዋ ስታፈራ ነው።

ዘሩን የሚያናንቁ በፍሬው ቢደነቁ አትገረም።

አንተ ግን ለሌሎች ታይታ ሳይሆን በገባህ መንገድ አቅጣጫህን መርጠህ ትጋ!

አንድ ቀን ውጤቱን ሲያዩ "እድለኛ ነህ" ይሉሃል።

✍ጌታቸው ከበደ

ከእዚሁ ከቴሌግራም መንደር የተወሰደ!

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

"ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ? ከሆነ በውሃው ላይ ተያይዘው ተያይዘው ይቆማሉ። ጉንዳኖቹ ተያይዘው በወንዝ ላይ በሚሰሩት መንገድ ሌሎች ብዙ ጉንዳኖች ይሻገራሉ፤ ተያይዘዉ ይሻገራሉ። ተደጋግፈው አስፈሪውን ወንዝ ይሻገሩታል። ባይያያዙና ባይደጋገፉ ግን አይቻላቸውም። አንዲት ጠብታ ዝናብ ለአንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።" ✍️ዴርቶጋዳ

ፍቅር የበጎ ነገሮች መክፈቻ ነው፡፡ በፍቅር ያልተዘጋ ሴራ የለም፡፡ በፍቅር ያላበቃለት ጦርነት የለም፡፡ በፍቅር አደብ ያልገዛ ጦረኛ የለም፡፡ ፍቅር የነገሮች መጠቅለያ ፣ የበጎ ነገሮች መሠረት ነው፡፡ የሠው ልጅ ጭንቅላቱን በፍቅር ከሞላ ክፉ ሃሳቦችና ተልካሻ ሴራዎች ወደእሱ ድርሽ አይሉም፡፡ በፍቅር የተሞላ ጭንቅላት ትርፉ በፍቅር መኖር ነው፡፡

"ጦርነት በሕይወትና በቁስ ላይ ከሚያስከትለው ጥፋት የበለጠ የሚያስጠላ ነገር በዚህ ዓለም ያለ አይመስለኝም። የሰው ልጅ በመካከሉ የሚፈጠሩትን ልዩነቶች በውይይትና በሠላም የሚፈታበት ቀን መች ይመጣ ይሆን? ያ ቀን ናፈቀኝ።" ✍️በዓሉ ግርማ

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አረፈዳጅሁ🙏

"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም።

የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም።

የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።

እናም አንድን ነገር ለታይታ ማድረግ ሞኞች የፈለሠፉት የመከበር ሙከራ መሆኑን ተረድተህ በቀጥተኛው መንገድ ለመጓዝ ሞክር።"

✍ Bruce Lee

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

ሰውን ከክፋት ፣ ከስስት ፣ ከዕብሪት ፣ ከትዕቢት ጋር የሚያፋቅረው የመጀመሪያው ምክንያት "ዝንጋዔ ሞት" ነው። ሞትን ያህል ዕዳ መቃብርን ያህል እንግዳ መዘንጋት ሰው በሀብቱ ና በጉልበቱ እንዲመካ ይገፋፋዋል፤ ማን አህሎኝነት ይወርሰዋል።

ይህንን ከመሰረቱ የተረዱ ጥንታዊ ሮማውያን ለገዥዎቻቸው አንድ አዛውንት ይመድቡ ነበር።

ገዥው ማለዳ ተነስቶ ቁርስ ሲጎርስ ያ አዛውንት ድንገት ዘው ብሎ በመግባት አንዲት ቃል ተናግሮ ይወጣል:-
'
'
'

"ትሞታለህ!"

ሮማዊ ጀኔራል ከድል መልስ በሰረገላ ሆኖ ወደ ከተማው ሲመለስ ህዝቡ ዘንባባ ይዞ በክብር ይቀበለዋል። ምርኮውንም እያግተለተለ ሲያልፍ በዚህ ደስታ መካከል ያ አዛውንት ከጄኔራሉ ጀርባ መጥቶ:- " ትሞታለህ!" ብሎት ያልፋል።

ሞትን ማሰብ የመታበይ መድኅን ነው የመታበይ ብቻ ሳይሆን የማግበስበስ ፍቱን መድሃኒት ነውና።

✍ዓለማየሁ ገላጋይ
📖መለያየት ሞት ነው

🙌መልካም አዳር የነገ ሰው ይበለን🙌

@kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

በቀናችን ውስጥ የሚገጥሙንን ማናቸውም የሕይወት ሁኔታዎች ወደድንም ጠላንም ማስቀረት አንችልም፡፡ አንዳንድ ቀኖች በጣም ደስተኛ ያረጉናል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ይበልጥ ፈታኝ ይሆኑብናል።

የተፈጠረውን ማንኛውንም ነገር መቀበል እና ከሁኔታው ጋር እርቅ መፈጠር ግን ብልሀት ነው፡፡ በዚህ ታላቅ የሕይወት ሚስጥር ለመቆየት ከትላንት ጭንቀቶች መላቀቅ አለብን፤ ትኩረታችንን ወደ አሁን መልሰን ማደረግ ምንችለውን ማስተዋል ይገባናል፤ በነበር እና በይሆናል መጨነቅ ችግራችንን አንድ እርምጃ አይፈታልንም፡።

እራስህን ለሚመጣው አዲስ እድል ክፈት፤ በዚህ ውድ ጊዜ እራስህን ሁን፤ ትናንት ቀድሞውኑ አልፏልና ያለፈውን ተወው። በእያንዳንዱ አዲስ ቀን ድንቅ ነገር እንደሚፈጠር አስተውል። በቀንህ የሚገጥምህን ምንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ሁን።

ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይቻላል። ግን የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል፤ የሕይወት እውነተኛ ክስተት አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ ሰላም ፍጠር፤ ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ትናንትህን መልቀቅ ይኖርብሀል።

ቀንህን የደስታህ ምንጭ አድርጋት።
አንተ አሁን ላይ ሙሉ ሰው ነህ፤ አንቺም ነሽ፤ ዘና በል፤ ዘና በይ።

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

@kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

ከሌለን፤ ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለን ነገር ይበልጣል። ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ መልካም ነገሮች አሉ።

ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል። ይሁን እንጂ አዲስ ቀን ሲሰጥህ ከብዙዎች በላይ እድለኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን። በሰላም ውሎ በሰላም ማደር እጅግ ትልቅ ነገር ነው። አዲስ ቀን አዲስ ህይወት ነው።

አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፤ የራስህንም አታቃል።

ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን በመኖርህ ብቻ ደስታን ምርጫህ አድርግ። አዲስ ቀን እንድታይ ስለተፈቀደልህ ብቻ ለፈጣሪ ምስጋና ልታቀርብ ይገባል።

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው!

የአስተሳሰብ ለውጥ ልክ እንደ አውሮፕላን ሁለት ክንፍ አለው፡፡ አንዱ ክንፍ እውቀት ነው፡፡ ሌላኛው ተግባር ነው፡፡ ሰዎች ለመለወጥ የሚቸገሩበት አንደኛው ምክንያት ከእውቀት እጦት የተነሳ ነው፡፡ ምክንያቱም በማታውቀው ነገር ዙሪያ እንዴት ትለወጣለህ? ይሄ ቦታ አልተመቸንም ብንል የት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንሄደው? ሄደን ምን ያጋጥመናል? ካላልን አስቸጋሪ ነው፡፡

ሁሉ እውቀት ኖሮን ደግሞ ባለንበት ቁጭ ብንል ተለወጥን ማለት አይደለም። አሁን እንደውም ትልቁ ሽወዳ ያለው አንዳንዴ ብዙ ስለለውጥ ስናውቅ የተለወጥን ይመስለናል፡፡ ከእሱ ደግሞ አለማወቅ ሁሉ ይሻላል፡፡

እውቀት ብርሀን ነው፡፡ ካወክ በራልህ ማለት ነው ፡፡ ቤት ውስጥ መብራት ባይኖር ምንም ማድረግ አትችል ይሆናል፡፡ ግን ቤት ውስጥ መብራት ቢኖር ስቶቩን ለኩሶ ፣ እቃውን አውጥቶ ፣ ድስቱን ጥዶ ምግብ አብስሎ አያበላህም፡፡ ነገር ግን አንተ እንድትሰራ በር ይከፍትልሀል፡፡

ስለዚህ እውቀትን እና ተግባርን ማቀናጀት ነው ለውጥ የሚፈጥረው! ምንድን ነው መለወጥ የምንፈልገው? እሱን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? እሱንም መለየት እና ማድረግ ነው፡፡ ጓሮህን ከሆነ መለወጥ የምትፈልገው እንዴት መለወጥ እንደምትችል ማወቅ አለብህ፡፡ ከዛ እጅህን ሰብስበህ መነሳት አለብህ፡፡ ጓሮህ ተቀየረ ማለት ነው፡፡

✍ዶ/ር ምህረት ደበበ

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

@Kezimkezia


🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ አሳብ አይበላም፤ አልጋ ተመቸ ተብሎ ያለ ሀሳብ አይተኛም፡፡ ጨዋታ ደራ ተብሎ ያለ ልክ አይወራም፤ ገንዘብ አለ ተብሎ ያለ መጠን አይወጣም፤ እግር አለ ተብሎ ያለ ምዕራፍ አይኬድም፡፡ ይህ ኅሊናን ማቦዘን ነው፡፡

ዝግ ኅሊና እንጂ ዝግ መንገድ የለም፡፡ መንገድ የሚከፈተው ኅሊናህ ውስጥ ነው፡፡ አስቀድመው በኅሊና መንገድ ወደ ጨረቃ የሄዱ ሰዎች በኋላ በመንኮራኩር መንገድ ለመሄድ አልቸገራቸውም፡፡

✍️ዳንኤል ክብረት
"ኅሊና እና መንገድ"

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

"የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መውደድ የለበትም!"

📖መነሻ ሃሳብ :- " ማታ ማታ - ገጽ 110

"ማሰብ ተፈጥሯዊ ባህሪህ ቢሆንም በማሰብ ላይ ያለህ ብስለት ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ካንተ የተለየ ሀሳብ ሲያጋጥምህ ለሃሳቡ በምትሰጠው ምላሽ(ግብር) ነው።

እምትወደው ሰው የግድ ባንተ ሃሳብ የሚስማማ ወይም አንተ የምትወደውን ብቻ የሚወድ መሆን የለበትም። እንደዛ አይነት ሰው ከፈለግክ ያንተን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል የሀሳብና የፍላጎት ወዛደር እንጂ አሳቢን አታገኝም።

የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር በመውደድ አይደለም መዋደዱ የሚገለጸው። ካንተ ለተለየ ነገር ሁሉ ጥላቻ ከሆነ ምላሽህ በትክክል ማሰብ መቻልህም ጥያቄ ውስጥ ይገባል። በሃሳብ መፋለስ የልዩነት እንጂ የጥላቻም ያለመዋደድ መንስኤም ሆነ ምልክት አይደለም። አንተ ራስህ በየቀንና በየሰአቱ የምታስባቸው ሃሳቦች ልዩነት አላቸው፤ ግን አቻችለሀቸው እየኖርህ ነው። ታድያ የሰውን ልዩነት ማቻቻልስ እንዴት ያቅትሀል...…?

ለራሳችን ጥያቄ ሰተነው እንጨርስ!

የሀሳብ ልዩነቶችን ለምን በስድብ እናጣጣቸዋለን።

ሰዎች እኛ ያልደገፍነውን ስለደገፉ ለምን እንዲያፍሩ እናደርጋቸዋለን?"

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

@kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

ሁለት ሱፊዎች በመንገድ ላይ ሲሄዱ ይገናኙና በመተቃቀፍ ተሳስመው አንዱ የቋጠረውን ስንቅ በጋራ ሊመገቡ ተቀመጡ። ይኸንን ትዕይንት ለአፍታ የተመለከተው የክርስቲያን ልዑል ወደ ሁለቱ ሰዎች ተጠግቶ ስለትውውቃቸው ጠየቃቸው።

መመገባቸውን ሳያቋርጡ አንዱ ቀና ብሎ ፦

"ካለዛሬ አይቼው አላውቅም ..." አለው።

"ምናልባት የአንድ ሀገር ልጆች ትሆኑ ...?" ሲል ጠየቀ ልዑሉ።

"ሀገሩንም አላውቅም ..." አለ ሰውየው አሁንም መመገቡን ሳያቋርጥ።

"ታዲያ ለምንድ ነው እንዲህ ዓይነት ፍቅር ያሳየኸው...?" አለ ልዑሉ በፍፁም ግርምት ተሞልቶ።

"በእኔ መንገድ ላይ ሲጓዝ ስላገኘሁት ነው" አለው።

ልዑሉም ተደንቆ ዝም ብሎ አልሄደም። በዚያ ቦታ ለሱፊዎች ማረፊያ የሚሆን ትልቅ አዳራሽ ሰራ። ዛሬ አዳራሹ ዘመናዊ መልክ ተገንብቶ የሱፊዎች መፍለቂያ "ዩኒቨርስቲ" ሆኗል።

📖ጥበብ ከጲላጦስ

ሰው መሆን እኮ እንዲህ ነው፤ በሀይማኖት ተለያይቶ ፣ በደም ሳይተሳሰሩ ፣ በባህል ሳይገናኙ ፣ ነገር ግን መረዳዳት ፣ አብሮ መብላት ፣ እንደሰው ተያይቶ አብሮ ችግርን መካፈል ማለት ነው። ባጠቃላይ በፍቅር ለመኖር ሰው መሆንና እንደ ሰው ማስተዋል ብቻ በቂ ነው።

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ ጫማ ስለሌለህ እግርህ አይታይም፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያክ ይተምኑሀል፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩት ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ።

እኔ ትንሽነቴን አልረሳም፤ ማወቄም አያመፃድቀኝም። ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው። ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።

ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ፤ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።

✍️Unknown

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

@kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

✍️ታገሱ!

የሰዎች ሁኔታና የነገሮች እልህ አስጨራሽነት እጅግ ፈታኝ የሆነበት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጸለዬ፤ “ፈጣሪ ሆይ እባክህን ትእግስትን ስጠኝ፤ ይህንን የለመንኩህን ትእግስት ደግሞ አሁኑኑ እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” ይህ ሰው ፈጣሪ ትእግስትን እስከሚሰጠውም መታገስ አልቻለም፡፡

ትእግስትን እንማረዋለን እንጂ አንቀበለውም፡፡ ትእግስትን የመማሪያው ብቸኛ መንገድ ደግሞ እልህ አስጨራሽ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ በማለፍና አስቸጋሪ ሰዎችን ችሎ መንገድን በመቀጠል ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ስንጀምር የሚፈታተነን ነገር ቀስ በቀስ እየደከመ ይሄዳል፡፡

አያችሁ እኛ አመለካከታችንን በመለወጥ በልጠንና ተሽለን እንገኛለን እንጂ ትእግስት አስጨራሽ ሁኔታዎችና ሰዎች እስከወዲያኛው ድረስ ከአካባቢያችን አይጠፉም፡፡ ትእግስት ባጣንና እልኸኛ በሆንን ቁጥር ውስጣችን ያለውን የትእግስት መጠን አለአግባብ ስለምናቃጥለው ቀስ በቀስ በጥቃቅን ሁኔታዎችና አመላከከታቸው እጅግ አናሳ በሆኑ ሰዎችም ሳይቀር መፈተን እንጀምራለን፡፡ ሁሌም መታገስን ምረጡ!

✍ዶ/ር እዮብ ማሞ

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

@Kezimkezia


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏

✍️ሕይወት እንደ ማዕበል ሲሆን!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ ማዕበል ነው፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፤ ድንገተኛ ወጪዎች፤ የገንዘብ እጥረት፤ የጉዳዮች መጥመም፤ የሰዎች ክህደት፤ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፤ የጤንነት መቃወስን የሚጠቁሙ ምልክቶች . . . ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡

ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡ ማዕበል ይመጣል፤ ልክ እንደመጣ ደግሞ ይሄዳል፡፡ ነፋስ ከየት እንደመጣ ሳናውቀው ወደ እኛ ይነፍሳል፤ ወደየት እንደሚሄድ ሳናውቀው ደግሞ ወደሌላ ቦታ ይነፍሳል፡፡

አይዟችሁ! ጽኑ! አትናወጡ! ተንጋግቶ የመጣው ተንጋግቶ ይሄዳል!

🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌

✍ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Kezimkezia


የጎዳና ተዳዳሪው ቢል ሬይ ለሳራ የዳይመንድ ቀለበቱን ሲመልስላት።


🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ🙏

አሜሪካን ካንሳስ ሲቲ ነዋሪ የሆነችው ሳራ ዳርሊንግ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያዋ በማቅናት ላይ ሳለች አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ ሽማግሌ ከመንገድ ዳር ቁጭ ብለው ሲለምኑ ትመለከታለች።

ሳራ ወደ ሽማግሌው በመጠጋት ቦርሳዋን ከፍታ የተወሰኑ ዶላሮችን ሽማግሌው ከጎናቸው ባስቀመጡት የፕላስቲክ ኩባያ ውስጥ አኑራ ጉዞዋን ትቀጥላለች።

ሳራ ከምንግዜውም በላይ በህይወቷ ደስተኛ ነበረች፤ ከምትወደውና ከምታፈቅረው ጓደኛዋ ጋር በትዳር ለመጣመር የቀናት ዕድሜ ቀርቷቸዋል።

ለእሷ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር ያለው ፍቅረኛዋ እጅግ ውድ የሆነ 💍ዳይመንድ💍 የቃል ኪዳን ቀለበት ገዝቶ በጉልበቱ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ካቀረበላት እና በደስታ እሺ ካለችው ጊዜ አንስቶ ህይወቷ በሀሴት ተሞልቷል።

ምሽት ላይ እንደተለመደው በስስት የምታየውን የዳይመንድ ቀለበት ስማ ለመተኛት ቦርሳዋን ከፈተችው፤ በድንጋጤ ደርቃ ቀረች፤ ቀለበቱ በቦታው አልነበረም።

ቦርሳዋን የከፈተችው መንገድ ዳር ቁጭ ብለው ለሚለምኑት ሽማግሌ ገንዘብ ለመስጠት ብቻ እንደነበር አስታውሳ የሽማግሌው ገንዘብ መሰብሰቢያ ኩባያ ውስጥ ቀለበቱን አብሮ እንደገባባት ጠረጠረች።

ለእጮኛዋ ስልክ በመደወል ሁኔታውን አጫወተችው፤ እጮኛዋም ሲከንፈ መጣ።
ተያይዘው በልመና ወደ ሚተዳደረው ሽማግሌ ቦታ ሄዱ፤ ሽማግሌው ግን በቦታው አልነበሩም።

"በእርግጥ ውድ የሆነ ቀለበት አግኝቶ እንዴት ተመልሶ በቦታው ሊቀመጥ ይችላል" የእጮኛዋ ግምት ነበር።

በቀጣዩ ቀንም በተመሳሳይ ከእጮኛዋ ጋር ሽማግሌው ተቀምጠው ወደ ሚለምኑበት ቦታ ሄዱ፤ አሁንም አልነበሩም። "በቃ ጦስሽን ይውሰድ ከእንግዲህ እርምሽን አውጪ" ነበር የእጮኛዋ መልስ።

በሦስተኛው ቀንም ሳራ ለእጮኛዋ ደውላ ወደ ሽማግሌው ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀችው። እጮኛዋ በመገረም "6 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ቀለበት ችግረኛ እና በረንዳ የሚያድር ሰው እጅ ገብቶ አገኘዋለሁ ብለሽ እንዴት ታስቢያለሽ?" ነበር ያላት። ሳራም "በቃ የዛሬን ብቻ እንየው፤ ሰውየው ከሌለ እርሜን አወጣለሁ" አለችው።

እጮኛዋም የሳራን ፍላጎት ለመሙላት ተስማምቶ ጉዞዋቸውን አቀ፤ ሽማግሌው በቦታው ተቀምጦ ሲለምን አገኙት።
ሳራ በደስታ ተዋጠ፤ አላውቅሽም ብሎ እንዳይሸመጥጠኝ የሚል ስጋት እንደዋጣት ወደ ሽማግሌው ተጠጋች።

አባት ያስታውሱኛል? በማለት ጠየቀች። ሽማግሌው ቢል ሬይ ሀሪስ ይባላ፤ ቀና ብሎ ተመልክቷት "አላወቅኩሽም ልጄ" ሲል መለሰላት።

ሳራም "ከ3 ቀን በፊት ከቦርሳዬ ገንዘብ አውጥቼ ሳስቀምጥ ሌላ ዕቃ አብሬ አኑሬ ነበር ?" ስትል ጠየቀቻቸው?

"የጣት ቀለበት ነው?" አሉ ሽማግሌው።

"አዎን አባት!" አለች ሳራ።

ቢል ቀለበቱን ጠቅልሎ ካስቀመጠበት ኪሱ በማውጣት "አንድ ቀን እንደምትመለሺ አውቅ ነበር" በማለት ከሰጣት ብኋላ "ቀለበቱን ያገኘሁት ዕለት ትክክለኛ ወይም አርቴፊሻል ቀለበት መሆኑን ለማወቅ ወደ ጌጣጌጥ ሱቅ ወስጄው ነበር፤ እነሱም ትክክለኛ መሆኑን ነግረው $4,000 ዶላር ሊገዙኝ ጠይቀውኝ ነበር። በእርግጥ ኑሮውን በበረንዳ ለሚያሳልፍና በልመና ለሚተዳደር 4ሺህ ዶላር ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ነገር ግን እኔን ለመርዳት ብላ በስህተት ቀለበት የጣለችን ሴት ንብረት መንካት አልፈለግኩም። በመሆኑም በጥንቃቄ አኑሬው የአንቺን መምጣት ስጠባበቅ ነበር።" ሲል መለሰላት።

ሳራ ዳርሊንግ እና እጮኛዋ የመልካሙን ቢል ሬይ ሀሪስ ታሪክ ከታች ቀለበቷን ሲሰጣት ከሚታየው ምስል ጋር በማያያዝ በሶሻል ሚዲያ (Facebook) ለጠፉት፤ ከታሪኩም ጎን ለጎን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ አካውንት ከፈቱ። በቢል ሬይ ቀናነት እጅጉን የተደሰቱ አያሌ ግለሶቦች የዕርዳታ እጃቸውን ይዘረጉ ጀመ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ 260,000$ ዶላር ተሰበሰበለት።

በአሁን ሰዓት ቢል ከበረንዳ አዳሪነት ወጥቶ የቤት ባለቤት ነው፤ ተጨማሪ የመጦሪያ ገንዘብም አገኘ።

✍️ ወድቆ የተገኘ ሁሉ አይወሰድም። በተለይ በኢትዮጵያን ባህል ነውር ነው። ባለቤቱ ጠፋብኝ ብሎ ሊመጣ ይችላልና ልክ እንደ አደራ እቃ በጥንቃቄ አስቀምጦ ፈላጊው እስኪመጣ መጠበቅ ያስፈልጋል። በትንሹ ስትታመን፤ ፈጣሪ ደሞ በብዙ ይሰጥሀል።

ምንጭ :- ከፌስቡክ

🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌

@Kezimkezia

Показано 20 последних публикаций.