Ethiopian Lottery Service/የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት/


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Букмекерство


To have alternative communication channel

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Букмекерство
Статистика
Фильтр публикаций


በየወሩ የሚወጣው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ29ኛው ዙር የዕጣ መውጫው ቀን እየደረሰ ነው አሁኑኑ 605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌ ብር ይቁረጡ እና ዕድልዎን ይሞክሩ ፡፡
መልካም ዕድል !


መደበኛ ሎተሪ 1725ኛ ዕጣ ዛሬ  ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ  አገልግሎት በዕድል አዳራሽ የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል።




29ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የመውጫው ቀን እየተቃረበ ነው፣ አሁኑኑ 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌ ብር በ10 ብር የ4 ሚሊዮን ብር እና የሌሎችም ዕድሎች አሸናፊ ይሁኑ
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር


አድማስ ዲጂታል ሎተሪን ይቁረጡ ሚሊየነር ይሁኑ አሁኑኑ የእጅ ስልክዎን በማንሳት 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር በ10 ብር ይቁረጡ፡፡የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ https://t.me/lottery_service1


የአዋሽ መልካሳው ነዋሪ የ700ሺህ ብር ቼካቸውን ተረከቡ!
በንግድ ስራ የተሰማሩትና የአዋሽ መልካሳው ነዋሪ አቶ ተስፋዬ በቀለ በ28ኛው አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ4ኛው ዕጣ የ700 ሺህ ብር ቼካቸውን ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተረክበዋል ፡፡ አቶ ተስፋዬ በቀለ የረጅም ጊዜ የሎተሪ ደንበኛ ሲሆኑ በደረሳቸውም ገንዘብ ቤት የመግዛት ዕቅድ እንዳላቸው ገልጸውልናል ፡፡


የእስካባተር ኦፕሬተሩ 1 ሚሊየን ብር ተሸለሙ!
በአዲስ አበባ ዙሪያ የቃሊቲ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፍሮምሳ ሰንበቶ ጉደታ በ28ኛው ዙር አድማስ ድጂታል ሎተሪ በ3ኛው ዕጣ የ1ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል ፡፡ አቶ ፍሮምሳ ሰንበቶ በመዝናኛ መልክ በየጊዜው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ይሞክራሉ ነገር ግን ደርሷቸው አያውቅም ተስፋ መቁረጥ የለም የሚሉት አቶ ፍሮምሳ “ የማታ ማታ እውነት ይረታ“ እንዲሉ ያለ መሰልቸት በመሞከራቸው በ3ኛው ዕጣ የ1ሚሊየን ብር ዕድለኛ ለመሆን በቅተዋል ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ የመኖርያ ቤት ለመግዛት እንዳሰቡ አጫውተውናል ፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


መምህሩ የ2 ሚሊየን ቼካቸውን ተረከቡ
መምህር አዳነ ደሴ ይባላሉ የመምህርነቱን ሙያ በቅርብ ነው የተቀላቀሉት ፡፡ መምህር አዳነ የቀብሪደሀር ነዋሪ ሲሆኑ ከልጅነታቸው ጀምሮ ሁለገብ የሚባል ዓይነት ሰው ናቸው ያገኙትን ይሰራሉ ሥራ አይመርጡም ለዚህም ይመስላል ከመምህርነት ሙያቸው በተጓዳኝ አልፎ አልፎ የዲጂታል ሎተሪ የመሞከር ልማድ አላቸው ፡፡ መቸም “ ደግሞ ደጋግሞ የሞከረ ከዕድል ጋር ተማከረ “ እንዲሉ በ28ኛው አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛው ዕጣ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል ፡፤ በደረሳቸውም ገንዘብ መኖርያ ቤት እንደሚገዙበት ገልጸውልናል ፡፡


የ2017ልዩ-ዕድል ሎተሪ ዕጣ ዛሬ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ  አገልግሎት በዕድል አዳራሽ የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል።


አቶ አብዲ ሙዲን ይባላሉ የነቀምት ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ በአነስተኛ ንግድ ስራ ይተዳደራሉ ፡፡ ከስራቸው ጎን ለጎን አልፎ አልፎ ሎተሪን የመቁረጥ ልምድ ያለቸው ሲሆን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አድማስ ዲጂታል ሎተሪን አዘውትረው ይቆርጣሉ ፡፡ ሎተሪውን ከመውደዴና አንድ ቀን ይመጣል በሚል ተስፋ በ28ኛው ዙር አድማስ ሎተሪ ላይ 31 ጊዜ ቆርጫለሁ ይላሉ አቶ አብዲ ፡፡ ከ31 የዕድል ቁጥሮችም አንዷ የዕድል ቁጥር መልካም ዜና ይዛ መጣች እና ዕድልኛ ስላደረገቻቸው በ1ኛ ዕጣ የ4 ሚሊየን ብር ቼካቸውን ተረክበዋል ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ የንግድ ስራቸውን እንደሚያስፋፉበት ገልጸውልናል ፡፡


በአንድ ቀን የሚሊዮን ብር እድለኛ መሆን የሚቻለው በሎተሪ ነው፣ 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌ ብር በ10 ብር የ4 ሚሊዮን ብር እና የሌሎችም ዕድሎች አሸናፊ ይሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ https://t.me/lottery_service1


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ 1ኛው ዕጣ የ20ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሽልማታቸውን ሲረከቡ


የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ28ኛው ዙር አሸናፊ ዕድለኞች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያቤት ነገ ህዳር 34 ቀን 2017 ዓ.ም ሽልማታቸውን ይረከባሉ ፡፡
የሽልማት ስነ-ስርዓቱም በድርጅት የቴሌግራምና ቲክቶክ አካውንቶች በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን ደንበኞችም መከታተል ትችላላችሁ ፡፡
አድማስ ዲጂታል ሎተሪ በየወሩ በሞባይልዎ የሚሞክሩት የዕድል አማራጭ በመሆኑ ለእርስዎም የ29ኛ ዙር ገበያ ላይ አለሎት አሁኑኑ ይሞክሩ ፡፡
መልካም ዕድል !
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከ ኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተዘጋጀ


የልዩ ዕድል ሎተሪ መውጫው ቀን ሕዳር 4 ቀን 2017 ደርሰዋል ፡፡ እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ
ቲኬቱን ቆርጠው ዕድልዎን ይሞክሩ ፡፡


የሎተሪ ትኬቱንና በቴሌግራሙ ገጽ ላይ የተለጠፈውን የሎተሪ ማውጫ ካሳያቸው በኃላ ግን ዕለቱ ሁለት በዓል፤ ድርብ ደስታ ሆኖ ነበር ይላል፡፡
አስረሳኸኝ ጌታቸው የኦሮሚያ ስቴት ዮኒቨርስቲ መምህር ነው፡፡ በመቱ ከተማ የተወለደው አስረሳኸኝ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እዚያው መቱ ከተማ አጠናቆ ከሲቪል ሰርቪስ ዮኒቨርስቲ በአካውንቲንግ የበ.ኤ ዲግሪ፣ከኢንድራ ጋንዲ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በገጠር ልማት (Rural Development) የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ጀምሮ ሎተሪ መቁረጥ እንደጀመረ የሚናገረው አስረሳኸኝ ዕድለኛ ሆኜ ህይወቴን ለመቀየር ሎተሪ ሁልጊዜ እቆርጣለሁ ሲል ይናገራል፡፡

ዛሬ የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነሀል፡፡ ወደፊትስ ሎተሪ ትቆርጣለህ ብለን ስንጠይቀው፣ ኪሴ የሎተሪ ትኬት ብቻ ነው፤ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም የሚወጣውን የልዩ ዕድል ሎተሪ እያንዳንዱን በመቶ ብር አራት የሎተሪ ትኬቶች ገዝቻለሁ፤ ወደዚህ እየመጣሁ እያለሁ ሚሊዮን የተባለ ሎተሪ አይቻለሁ፤50 ሚሊየን ብር የሚያሸልም ስለሆነ ከዚህ እንደወጣሁ እገዛለሁ፤ስለዚህ ወደፊትም የሎተሪ ትኬት መቁረጤን እቀጥላለሁ ብሏል፡፡

በመጨረሻም ያቀረብንለት ጥያቄ በ20 ሚሊየን ብሩ ምን ለማድረግ አቅደሀል የሚል ነበር፤
ከአንገቱ ቀና ሳይል ለደቂቃ ያህል ፀጥ ብሎ ቆየና ለጊዜው ግልጽ ያለ እቅድ አልያዝኩም፤ ሆኖም በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ፤ ከኪራይ ቤት እወጣለሁ፤ወደምገዛው አዲሱ ቤቴ እገባለሁ አለን፡፡
መልካም ህይወት እንመኝለታለን!


በአዲስ ዓመት በመጀመርያዋ ቀን 20 ሚሊየን ብር ማን ይሰጣል?መስከረም 1 ቀን፣ሁለት በዓል፣ ድርብ ደስታ ነበር
አስረሳኸኝ ጌታቸው ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም የወጣው የዕንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ነው፡፡

መስከረም 1 ቀን 2017 የዘመን መለወጫ ዕለት ጠዋት፣አስረሳኸኝ በኪራይ ቤቱ ነበር፡፡በዓሉን በጋራ ለማክበር ጎረቤቶቹን በመጥራቱ ቤቱ በበዓል ድባብ ደምቃለች፤ጎረቤት ተሰብስቧል፤ጨዋታው ደምቋል፤ሳር ተጎዝጉዞ፣ ቡና ተፈልቶ፣ ዳቦ ተቆርሶ፣ ማእድ ቀርቦ አዲሱን ዓመት እየተቀበሉት ነው፡፡

አስረሳኸኝ ጎረቤቶቹን ጠርቶ በዓሉን ቢያደምቅም በዚያን ሰአት በሙሉ ልቡ ከነሱ ጋር እንዳልነበረ ይናገራል፡፡ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ በዋዜማው ጳጉሜ 5 ስለወጣና እድሉን ለማወቅ ጓጉቶ ስለነበር የገዛቸውን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ትኬቶች ከኪሱ አውጥቶ ከደራው ጨዋታ ገለል አለ፡፡ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎትን የቴሌግራም ገጽ ከፍቶ የዕጣ ማውጫውን ሲመለከት የአንደኛው ዕጣ ቁጥር 0103072 ደምቃ ታየችው፡፡ ማመን ስላልቻለ ደጋግሞ አየ፡፡ የ1ኛው ዕጣ የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ መሆኑን ደጋግሞ አረጋገጠ፡፡ በተደበላለቀ ስሜት ሆኖ የሞቀ ጨዋታ ይዘው የነበሩትን ጎረቤቶቹን የምስራች አለኝ፣የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆኛለሁ ቢልም የቀልድ ስለመሰላቸው የምስራቹን ከቁም ነገር የቆጠረው አልነበረም፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


መደበኛ ሎተሪ 1724ኛ ዕጣ ዛሬ  ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ  አገልግሎት በዕድል አዳራሽ የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አቶ ሸምሱ ተማም የቶምቦላ ሎተሪ 2ኛ ዕጣ በዲላ ከተማ ሽልማታቸውን ሲረከቡ ፡፡

Показано 20 последних публикаций.