# የአዳም ልጅ ነኝ
ሲፈጥረን የሰው ልጅ ባፈር እንዳልነበር
ባፈርም ተፈጥሮ አፈር መሆኑ ላይቀር
ለዚ አጭር ህይወት ሀጥያትን አርግዞ
ክፋት እና ተንኮል ቂም በቀልን ይዞ
ለዘረኝነት ሰልፍ ልቡን አመርዞ
ወንድሙን ገደለ እህቱን አጠፋ
አባቱንም ከዳ እናቱ ላይ ተፋ
ምንም ለማይጠቅመው ጥፋትን አጠፋ
ምነው ግን የሰው ልጅ ሞኝነቱ በዛ
ለማይጠቅመው ሀጥያት እራሱን ሚገዛ
ቋንቋዬ ከ ቋንቋክ ቢለያይብክ
ሊገባኝ አልቻለም ዱላ ማንሳትክ
እምነቴ ከምነትክ ቢለያይብክ
ሊገባኝ አልቻለም እንዲ ሚያስቆጣክ
ባታውቀው ነው እንጂ ባይገባክ ታሪኩ
የኢትዮጵያነት የፍቅር ጫፍ ጥጉ
ልዩነቷ ዉበት ብዛቷ አንድነት
ተከብሮ የኖረ በፍቅር በህብረት
ይኸው ዛሬ ከፋ በዚ ዘመን ጠፋ
ታሪክ ተቀየረ ሀጥያት ተስፋፋ
እባክህ ወንድሜ ልብህን መልሰው
ዘር ለሰብል እንጂ አልጠቀመም ለሰው
አንተ ኦሮሞ ነህ ትግሬ ነክ አትበለኝ
ዘራችን ቢለያይ እኔም የሰው ልጅ ነኝ
አንተም የአዳም ልጅ እኔም የሄዋን ነኝ
ሲፈጥረን የሰው ልጅ ባፈር እንዳልነበር
ባፈርም ተፈጥሮ አፈር መሆኑ ላይቀር
ለዚ አጭር ህይወት ሀጥያትን አርግዞ
ክፋት እና ተንኮል ቂም በቀልን ይዞ
ለዘረኝነት ሰልፍ ልቡን አመርዞ
ወንድሙን ገደለ እህቱን አጠፋ
አባቱንም ከዳ እናቱ ላይ ተፋ
ምንም ለማይጠቅመው ጥፋትን አጠፋ
ምነው ግን የሰው ልጅ ሞኝነቱ በዛ
ለማይጠቅመው ሀጥያት እራሱን ሚገዛ
ቋንቋዬ ከ ቋንቋክ ቢለያይብክ
ሊገባኝ አልቻለም ዱላ ማንሳትክ
እምነቴ ከምነትክ ቢለያይብክ
ሊገባኝ አልቻለም እንዲ ሚያስቆጣክ
ባታውቀው ነው እንጂ ባይገባክ ታሪኩ
የኢትዮጵያነት የፍቅር ጫፍ ጥጉ
ልዩነቷ ዉበት ብዛቷ አንድነት
ተከብሮ የኖረ በፍቅር በህብረት
ይኸው ዛሬ ከፋ በዚ ዘመን ጠፋ
ታሪክ ተቀየረ ሀጥያት ተስፋፋ
እባክህ ወንድሜ ልብህን መልሰው
ዘር ለሰብል እንጂ አልጠቀመም ለሰው
አንተ ኦሮሞ ነህ ትግሬ ነክ አትበለኝ
ዘራችን ቢለያይ እኔም የሰው ልጅ ነኝ
አንተም የአዳም ልጅ እኔም የሄዋን ነኝ