Talk about love ስለፍቅር እናውራ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"💞ፍቅር💞
❤ገደብ የሚባል ነገር❤
አያውቅም አይቀበልም
መሰናክል እና አጥር ዘሎ ግንብ ደርምሶ
መድረስ ያለበት ቦታ ይደርሳል
ምክንያቱም💕ፍቅር💕እውነት ነው
እውነትም አሸናፊ ነውና::”
📺በቻናላችን ላይ
📩እወድሀለው/እወድሻለው
📩Happy Birth Day ለማለት contact @wakanda0

እየተዝናናን ስለ ፍቅር♥
አስተያየት @wakanda0

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በዝግታ

First ቀስብዬ ገላዋን አሸዋት
ለስላሳ አካሉዋን በጆቼ ዳበስኳት
ከዛም ቀስ እያልኩኝ ገላዋን አራስኳት
በሰሜት ውስጥ ሆኜ በዝግታ ናጥኳት
በጣቶቼ ውስጧን በደንብ ጎረጎርኳት
.
.
.
.
.
.
በስተመጨረሻም ውዷ ብርጭቆዬን
በደንብ አለቅልቄ ውሀ ጠጣውባት::

ግን ምን አስባቹ ነበር😳 ሆ
   
            ✍ተገጠመ በኪያ


┈┈••◉❖◉●••┈
ዝም ብለሽ ስሚኝ🌺
❣️ :¨·......................:¨·.❣️


......... ✍️ፃፍኩልሽ💌 ........

አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ
ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ
ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል
ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል
አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ
ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ
ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ
የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ
እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት
ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት
ዛሬ ግን
ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ
አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ
በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ
ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ
እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ
ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ


እኔው ተሰቃየው
ላንቺ ያለኝ ፍቅር ሊያሳብደኝ ደርሶ
ጠዋት ቀን ማታ አልጋዬ በእንባ እርሶ
አይዞህ ስትይኝ ውስጤ በቃልሽ ታርሶ
ችግርተኛው ልቤ ንፁህ ፍቅርሽን ጎርሶ
ሳላይሽ ባድር ልቤ ያድራል ፈራርሶ
😔ታድያ ምን ያደርጋል😔
የሆዴን በነገርኩ እኔው ተሰቃየው
ቃልሽን ባልሰማው እኔ ተንገላታው
እኔ ብቻ ሆኜ ፈላጊ ናፉቂ
አንቺ ኮራሽብኝ ሆንሽና ታዋቂ
ምነው ባልነገርኩሽ የልቤን ቋጠሮ
ይሻለኝ ነበረ ባይፈታ ታስሮ
✍y
የተመቸው👌


❣ #ማፍቀር እኮ ሀጥያት አይደለም

❣ነገር ግን በፍቅር ስም በሰው ስሜት
ላይ መጫወት ትልቅ ሀጥያት ነው!

#ወዳጄ ፦
❣እውነተኛ ፍቅር እኮ ለምትወደው ሰው ምንም
ሳትሰስት እራስህን አሳልፈህ መስጠት እንጂይ
በማስመሰል ተጀምሮ በጥላቻ የሚደመደም አይደለም፤

❣ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር ስሜት
ሳይሆን ዘልአለማዊ መተሳሰብ ነው።

የሚስማማ ሼር ያድርግ


አብዛኞቹ ሴቶች ለምን እንደተፈቀሩ ምክንያት ይፈልጋሉ፡፡ ፍቅር ግን ምክንያት አያሻዉም.... ይህቺን ጽሁፍ ያንብቧት፡፡

ልጅቷ፡- ለምን ወደድከኝ? ለምን አፈቀርከኝ?

ልጁ፡- ምክንያቱን መናገር አልችልም፤ ነገር ግን የእውነት እወድሻለው፡፡

ልጅቷ፡- ምክንያትህን እንኳን መናገር ሳትችል እንዴት እወድሻለው፤ አፈቅርሻለው ለማለት ቻልክ?

ልጁ፡- እውነት ለምን እንደወደድኩሽ አላቅም ግን እንደምወድሽና እንደማፈቅርሽ ማረጋገጥ እችላለው፡፡

ልጅቷ:- ማረጋገጥ? አይሆንም፤ ለምን እንዳፈቀርከኝ ምክንያቱን ነው የምፈልገው፡፡ የጓደኛዬ ፍቅረኛ ለምን እንዳፈቀራት ነግሯታል፤ አንተ ግን ምክንያትክን አታቀውም፡፡

ልጁ፡- እሺ እሺ በቃ እነግርሻለው፡፡ ምክንያቱም ቆንጆ በመሆንሽ፤ ለጆሮ በሚለሰልሰው ድምፅሽ፤ ስለምትንከባከቢኝ፤ መልካም አሳቢ ስለሆንሽ፤ በሚያምረው ፈገግታሽ፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴሽ ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡

ልጅቷ በልጁ ምላሽ በጣም ረካች፤ እጅግም ደስ አላት፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ ከቀናቶች በኀላ ልጅቷ አደጋ ደርሶባት ኮማ ውስጥ ገባች፡፡ መንቀሳቀስ አትችል፤ ማውራት አትችል፤ መሳቅ አትችል፤ ዝም ብቻ፡፡

ልጁ ደብዳቤ ፅፎ እያለቀሰ ከጎኗ አስቀምጦት ወጣ፡፡ ደብዳቤውም እንደዚህ ይላል፡፡

"የኔ ውድ በሚለሰልሰው ድምፅሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤ አሁን ግን ማውራት ትችያለሽ? አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡

ስለምትንከባከቢኝ እና ስለምታስቢልኝ አፍቅሬሻለው፡፡ አሁን ግን ይህን ማድረግ አትችይም፤ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችል፡፡

በፈገግታሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፤ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴሽ ምክንያት አፍቅሬሻለው፡፡ አሁን መሳቅ ትችያለሽ? መንቀሳቀስ ትችያለሽ? አትችይም፡፡ ስለዚህ ላፈቅርሽ አልችልም፡፡

ፍቅር እውነት ልክ እንዳሁኑ ምክንያት ካስፈለገው ከአሁን በኀላ አንቺን ላፈቅር የምችልበት አንድም ምክንያት የለኝም፡፡

ፍቅር ምክንያት ይፈልጋል? አይፈልግም፡፡ ስለዚህ ዛሬም እንደትናንቱ ካለምንም ምክንያት አፈቅርሻለው፡፡ ከዘላለሙ ፍቅሬ ጋር ሁሌም ያንቺ ብቻ ነኝ፡፡"


ዳሌሽን አይቶ ያፈቀረሽ ዳሌሽ የከሳ እለት የእሱም ፍቅር አብሮ ይከሳል፡፡ ያጎጠጎጡ ጡቶችሽን አይቶ ያፈቀረሽ ቀን ጥሏቸው የወረዱ እለት የእሱም ፍቅር አብሮ ይወርዳል፡፡ አንተም እንደዛው ወንድሜ ሀብትህን አይታ ያፈቀረችህ ጋዝናህ ባዶ የሆነ ቀን የእሷም ልብ ለፍቅር የማይሆን ባዶ ዋሻ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ፈጣሪ እውነተኛ ፍቅርን ይስጠን፡፡


ለፈገግታ

💎"C" በአማርኛ አንደ "ጨ" ናት ብለው ነግረውህ
"Coca cola" ን ጮጫ ጮላ ብለህ ያነበብከው ልጅ ግን ትውልድ ቢረሳህ እኔ አልረሳህም 😂😂

🛎 "Curriculum" የሚለውን ሠርካለም ብሎ ያነበበውን ልጅ ግን በስም ማጥፋት ወንጀል መከሰስ የለበትም?

💎 ፈረንጅ ሀገር supermarket ዶሮ ለመግዛት ሄደሽ እንቁላል አንስተሽ where mother?ያልሺው ልጅ ኮርተንብሻል

🛎 ስልክሽ battery full ሲል ማንኣባቱ ነው beautiful ያለሽ? ብሎ ሲቀጠቅጥሽ ያደረው ባልሽ እንግሊዘኛ ለመደ ወይ ?

💎 ጋዝ ተልከህ total የሚለውን ተትቷል ብለህ አንብበህ የተመለስከው ልጅ ቤት እስካሁን በከሰል ነው የሚሰሩት?


Share😘 Share😘 Share😘


ትክክለኛ አፍቃሪ!!!

ውበትሽን አይቶ የተመኘሽ እና ከውበትሽ ጀርባ ያለውን ማንነትሽን አውቆ
ያፈቀረሽ ሰው የተለያዩ ናቸው። ለምን እነደዚህ አልከኝ እንዳትይኝ ?
እኛ ወንዶች የፈለግነውን እስክናገኝ ሴትን ንግስት ማድረግ
እናውቅበታለን። ያፈቀረ ግን ንግስቱን ንግስቴ ብሎ ለመጥራት እንኳን ቃል
አጥሮት ይንተባተባል፤ ውበትሽን ለመግለፅ እንኴን አንደበት የለውም፤
ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትሽ እሱነቱን አጥቶ ሌት ከቀን አንቺን በምናቡ
ሲያወጣና ሲያወርድ ውበትሽን ለመግለፅ ሲቸገር ፣ የአንቺን ህይወት
በማድመቅ የራሱን ሲያፈዝ፣
ከሰው በላይ የነበረው ማንነቱን መቀመቅ ሲያወርድ........ያኔ ላንቺ
ያንስብሻል። እናም ፍቅርሽን ገላሽን ለተመኘው ትሰጪና ደግመሽ ብትፈጠሪ
እንኴን የማታገኝውን ንፁህ አፍቃሪሽን ልብ አንኮታኩተሽ ጥለሽ
ትሰብሪዋለሽ። እሱም ለዘለዓም ልቡ ታሞበት እንደማቀቀ ፍቅሩን ተቀምቶ
አዝኖ አፈር ይሆናል። አንቺ ሳታውቂ ራስሽን የሰጠሽው ግን አውቆ ይተውሻል።
በቃላት ድርደራ በስጦታ ጋጋታ በአፉ ንግስት ያስመሰለሽ.......ያሻውን
ፈጽሞ ሲያበቃ ከጥፍሩ ቆሻሻ እንኴን ሳይቆጥርሽ ይርቅሻል ።
ለዚህ ነው የተመኘሽ እና ያፈቀረሽ የተለያዩ ናቸው የምልሽ።
ምርጫው ግን ያንቺ ነው።

ፈጣሪ ለሁሉም ሰው የሚመኘውን ሳይሆን በልቡ የሚያፈቅረውን ይስጠው !!!

Показано 7 последних публикаций.

12 170

подписчиков
Статистика канала