© ከ Atiqa Ahmed Ali Facebook የተወሰድ
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ
እንደ ዓይን እንደ ጆሮ እንደ እግር እንደ እጅ፣
ወዳጅ ማለት አብሮ የሚጓዝ ነው’ንጂ፣
ይሄ ምን ያደርጋል የሚቀር እደጅ። ይላሉ ሸኽ ሁሴን። አዎን! ወዳጅ ሁልጊዜ የሚያዋየው፣ አብሮ የሚዘልቀው፣ ሲፈልጉት የሚገኘው፣ ሲጠሩት የሚመልሰው ነው!ሙሐባ ማለት ከራሚው ነው! "እወዳው ድረስ!" ይላል የወሎ ሰው ሲመርቅ!የተጀመረ ሁሉ ሲጨረስ ደስ ይላል። ኺትማ ድረስ ያልዘለቀ እንኳን ሙሐባ ቡንም ደግ አይደለም እል የለ?!የነቢ ውዴታችንም ስንሰግድ ስንቀራም፣ ስንበላ ስንተኛም፣ ስንነቃም፣ እንደው በቁም ብቻም ሳይሆን መለከል መውት ሲጎበኘን በጘርጘራም፣ በለሕድም በሲራጥም ሲሆን ነው! "የቂያማ ለታ ሙሐመድ ነው ዋሴ!" ያሉት ድረስ ከዛ በጀነትም!
አንዴ ስሙ የሚያምረኝ ገብረሏህ ገብረልዐዚዝ ሸይኽ በድሩዲን አል ሑሰይንይ ስለተባሉ ታላቅ የሻም ወልይ አውግቶ ነበር። ሸይኹ እያሰገዱ ባሉበት ሰዓት ባልተለመደ መልኩ ተሸሁድ (አተሕያት) ላይ ብዙ ጊዜ ቆዩ። ከጨረሱ በኋላ ሰጋጁ ስለ ምክንያቱ ጠየቃቸው። እሳቸውም « ተሸሁድ እየቀራሁ “አሰላሙ ዐለይከ አዩሃ ነብዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" ስል ሰላምታዬን አልመለሱልኝም ነበር። እናም እስኪመልሱልኝ ድረስ ደጋግሜ እያልኩ ነበርና ነው የዘገየሁት» ብለው መለሱላቸው። ሰዎቹም በጣም በመገረም «ሰላምታውን ሲመልሱልዎት ይሰማዎታል እንዴ?» ብለው ሲጠይቋቸው አስገራሚ ምላሽ ነበር የመለሱት «በኛና በሳቸው መካከል ለአፍታ እንኳ ግርዶሽ ከገባ ሩሓችን ከአካላችን ትወጣለች» 😢 አሶላቱ ወሰላሙ ዐለይከ ያረሱለሏህ!
ያጫፈረ ሁሉ መች ባልደረባ ነው፣
ብዙው ተደላቂ ድቤ ጋር ቀሪ ነው። ብለዋል ሌሎቹ አባቶቻችን ደግሞ!
አዎን ደጅ ከሚቀሩት አያድርገን! ሙሒቦቹ ጭፈራው ሳይሆን በነቢ የተቃኘው የቀልባቸው ዜማ ነው የሚሰማቸው፣ ከድልቂያውና ከድቤው ምት በላይ ነቢን እያለ የሚመታው ልባቸው ነው የሚወዘውዛቸው! ከዳር ላለ ባይገባውም ቅሉ!
ከቶ የኔን ነገር የሚያውቅልኝ ማን ነው?፣
እሆዱ ካልገባ የዳር ሰው አማን ነው። አይደል ያሉትስ?
ፊት ያስለመደውን አይተውም ትልቅ ሰው፣
ሲሆን ይጨምራል የፊቱ እያነሰው። ይላሉ ሌላው ማዲሕ ደግሞ። በዱንያ ሳለን በሲድቅ የደጋገምነው ስም፣ የናፈቅነው ዛት እስከ መጨረሻው ይከተለናል እንደ ታላቁ ሸዕራዊና ሌሎቹ ደጋጎች!!
ሙፈሲር መሐመድ ሙተወሊ ሻዕራዊ በሀያኛው ክፍለ ዘመን ኖረው የእውቀት እና የአስተሳሰብ ምጥቀታቸው ግና የ‘ነ ኢማም ሻፊዒና ኢማም አቡ ሀኒፋ ዘመን ሰው የሚያስመስላቸው ስማቸውም ምግባራቸውም የገዘፈ ታላቅ ዓሊምና የነቢ ወዳጅ ነበሩ። ታድያ ሽይኽ ሻዕራዊ በሞቱበት ቀን በአልጋቸው ላይ እያሉ ከልጆቻቸው አንዱ ሸሐዳን ሊያስይዛቸው ወደርሳቸው ቀርቦ "ያ ሸይኽ መሐመድ ላኢላሃኢልለሏህ ሙሐመድ ረሱሉሏህ በል" አላቸው። ሽይኽ ሻዕራዊ "ላኢላሃኢለሏህ!" ብለው ዝም አሉ። ጌታችን ረሂሙ ያስጠጋው ስሙን ከስሙ ነውና ሸሐዳ የሚከምለው ስማቸውን ከስሙ ጋር በመጥራት መሆኑን የሚያውቀው ልጃቸው ሙሉውን ሸሐዳ እንዲሉ ደግሞ ነገራቸው "ያ ሸይኽ ላኢላሃኢልለሏህ ሙሐመድ ረሱሉሏህ በል" ከዛ ሸይኽ ሻዕራዊ አሽሀዱአላ ኢላሃ ኢለላህ ብለው መሰከሩና ፊታቸውን ወደ አንዱ ጥግ አዙረው በጣታቸው በመጠቆም "አንተ የአላህ መልዕክተኛ እንደሆንክ እመሰክራለሁ!" ብለው ወደ አኸራ ተሻገሩ። መገን ሰው! ሰይዱል ከውነይን ከጎናቸው ሆነው እኮ ነው!!
ወዳጅ ማለት አብሮ የሚጓዝ ነው‘ንጂ አሉ! ዳኢመን ቢላ አደድድድ እያሉ መወዝወዝ ነው አቦ!
ሰይዲ! በቀልባችን፣ በፊታችንም በሁለት ዓለም ቤታችንም አንጣሁ!
#ሶሉ_ዓለል_ሀቢብ!
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዱና ወመውላና ሙሐመድ!💚💚💚
t.me/mahbubil