© ከ Atiqa Ahmed Ali Facebook የተወሰድ
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!
አንድ የክፍለ ሃገር ሰው መሃል አገር ገብቶ ንብረቱ ተዘርፎ በሌላም በሌላም ነገር ተማሮ ወደ አገሩ ሊመለስ እንደተሳፈረ ዞር ሲል ሰማዩ ጠቋቁሮና ደመና አርግዞ ቢያይ "የታባቱ በልልኝ ይሄን ከተማ ጌታዬ!" አለ። ይሄ ወግ ትዝ ያለኝ ከሰሞኑ ግርግር በኋላ አንድ ወዳጄ "እኔማ እንደ በደዊኑ (የዓረብ ገጠሬ) ‘ጌታዬ ሆይ እኔንና ሙሐመድን ብቻ ምረህ ሌላውን ቅጣልኝ’ ትያለሽ ብዬ ነበር የጠበቅኩት።" ብሎ አስቆኝ ነው።😀
እነሆ የዓረቡ ገጠሬ ታሪክ…!
የኔ ውድ ነብይ ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ ዓለይህ ‘አምር ቢልመዕሩፍ ወንነህይ አኒል ሙንከር’ ስለተባለ ብቻ ሰውን ከመጥፎ ለመከልከልና በመልካም ለማዘዝ በሚል አያስደነግጡም አያስደነብሩም!…የኔ ወለላ ሁሉን ሲያደርጉ ከማር በጣፈጠ መንገድ ነበር። ተግሳፃቸው ሆነ አስተምህሮታቸው የግብር ይውጣ እና ራስን ቅዱስ ሌላውን እርኩስ ያደረገ አይነት አይደለም! አዛኝና እጅግ ለስላሳ ነበሩ። ለዛም ነው
فَبِمَا رَحْمَةٍ مِّنَ اللَّهِ لِنتَ لَهُمْ ۖ وَلَوْ كُنتَ فَظًّا غَلِيظَ الْقَلْبِ لَانفَضُّوا مِنْ حَوْلِكَ ۖ فَاعْفُ عَنْهُمْ وَاسْتَغْفِرْ لَهُمْ وَشَاوِرْهُمْ فِي الْأَمْرِ ۖ
ያላቸው። "ከአላህም በሆነች ችሮታ ለዘብክላቸው። ዐመለ መጥፎ፣ ልበ ደረቅም በሆንክ ኖሮ ከዙሪያህ በተበተኑ ነበር። ከእነርሱም ይቅር በል። ለእነርሱም ምህረትን ለምንላቸው።"
ታድያ አንድ ጊዜ ምን ሆነ መሰላችሁ?…ያ የገጠር ሰው መስጅድ ውስጥ ገብቶ በአንዱ ጥግ ላይ ሽንቱን መሽናት ጀመረ። በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ ተንጫጩበት፣ ጮሁበት።
ያኔ ጥበብን እንደ ሸማ የደረቡት አዛኙ ነብይ "ተውት አታቋርጡት ይጨርስ!" አሉና ቦታው ላይ በባልዲ ውሃ አምጥተው እንዲደፉበት ሰዎችን አዘዙ። ከዚያም ተነስተው ወደ ሰውዬው በመሄድ "መስጅድ የሚገነባው አላህን ለማስታወስና ሶላት ለመስገድ ነው፤ ስለሆነም አይሸናበትም።" አሉት። ሰውዬውም ምክራቸውን እንደሰማ "አላህ ሆይ!እኔና ሙሐመድን ብቻ ማር ከእኛ ጋር ሌላ ማንንም አትማር!" አለ።😀
ውጤቱን ግን አያችሁ?!… ጥበብ፣ ሥነ ምግባርና እዝነት ሲጠፋ ሰዎች ሳያውቁት ለሙስሊሞች በአጠቃላይ ቀስ በቀስም ለኢስላም ጥላቻ ያድርባቸዋል፣ እንደ ውዴዋ በጥበብ መላሽ ካላገኘ ስንቱ ከመንገድ እንደወጣ፣ ስንቱ ከመግባት እንደታቀበ አላህ ይወቀው! ረሱልም ሰ.ዓ.ወ በሰውዬው ንግግር ፈገግ ብለው "ለሁሉም የሚዳረሰውን የአላህን ምህረት አጠበብከው!" አሉት።
ሰውዬው ከዚያ በኋላ እንዲህ ሲል ይሰማ ነበር…"ለነብዩ አባቴም እናቴም መስዋእት ይሁኑላቸውና ከመቀመጫቸው ተነስተው ወደ‘ኔ መጡ፤ አልሰደቡኝም፤ አልወቀሱኝም፤ አልመቱኝም!"
መርዝ የተባለ ሁሉ ወተትም ሀውድም በሆነው ዚክራቸው ይረክሳልና ወዳጆቻቸው ትካዜ አያገኛቸውም!
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለሏህ!
#ሶሉ_ዓለል_ሃቢብ!
አላሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓለይህ!💚💚💚
https://youtu.be/wE9v0d9yvHY?si=Y6im8DzyZTOFRdmm