ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


The channel of mahibere kidusan

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በተጨማሪም ስለ አገልግሎቱ ሐሳብ አስተያየት ካላቸው ማንሳት እንደሚችሉ ም/ኃላፊው ገልጸው አገልግሎቱን በስፋት ለማስቀጠል አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ስለሚስፈልጉ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ምእመናን ጥሪ አቅርበዋል።


በ“ሃሎ መምህር” አማካኝነት ከምእመናን ለተነሱ ከ60 በላይ  ጥያቄዎች ምላሽ እንደተሠጠ ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ገለጸ

መጋቢት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት “ሃሎ መምህር” የተሰኘ ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ በሚሰጥ አገልግሎት ከምእመናን ለተነሱ  ከ60 በላይ  ጥያቄዎች ላለፉት ሁለት ወራት ከ አስራ አምስት ቀን ውስጥ  ምላሽ  መሰጠት እንደተቻለ ገልጸዋል።

በማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት የስብከተ ወንጌልና ዕቅበተ እምነት ዋና ክፍል ምክትል ኃላፊ ዲያቆን ዐብይ ጌታሁን እንደገለጹት አገልግሎቱ በዋናነት ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን በመመለስ ያመኑትን ለማጽናትና አዳዲስ አማንያንን ለማጠንከር የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ላለፉት ሁለት ወራት ምእመኑ ከጠየቁት ጥያቄዎች አኳያ በየትኛው እድሜ ክልል ምን አይነት ጥያቄ እንደሚነሳ በተለይ ከጾታ፣ ከጾም፣ ከንስሀና ከሌሎች ጋር ተያይዞ ጥያቄዎች መጠየቃቸውን  ተናግረዋል።

ምክትል ኃላፊው አያይዘው ማንኛውም ምእመን በውስጣቸው የሚመላለስ ጥያቄዎችን መጠየቅና ምላሽ ማግኘት እንደሚችሉ አሳስበዋል። 

በዚህም ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 4፡00 - 10፡00 ሰዓት አገልግሎቱ የሚሰጥ ሲሆን ሰኞ፣ ረቡዕና ዓርብ በኦሮምኛና በአማርኛ እንዲሁም ማክሰኞና ዓርብ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ እንደሚሰጥ ምእመኑ አውቆ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

ከሀገር ውጪ ለሚገኙ ምእመናን ለጊዜው ሀገር ውስጥ በሚገኙ ምእመናን በኩል ጥያቄያቸውን እንደሚያስተናግዱ የገለጹ ሲሆን ለቀጣይ በምን መልኩ መካሄድ እንዳለበት ታስቦ እንደሚሠራበት ጠቁመዋል።


ተመራቂ መምህራን በተማሩት የትምህርት መስክ በትጋት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማገልገል እንደሚገባቸው ተገለጸ።

መጋቢት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል በግቢ ጉባኤያት ዋና ክፍል ሥር ከሚገኙ አራት ግቢ ጉባኤያት የተወጣጡ በአንደኛ ደረጃ ተተኪ መምህራንነት ሲሠለጥኑ የቁዩ 28 በኦሮምኛ እና 18 በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቀዋል።

ዲያቆን ዳኜ ዘርፉ በማህበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የሃገር ውስጥ ማእከላት ማስተባበር ምክትል ተጠሪ እንደገለጹት ተመራቂ መምህራን የተማራችሁትን ትምህርት አንድ መክሊት ተሰጥቶት እንደቀበረው አገልጋይ ሳትሆኑ በትጋት ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማገልገል ይገባችኋል ብለዋል።


47 አዳዲስ  አማንያን የሥላሴ ልጅነት አግኝተው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኅብረት መቀላቀላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን የነጌሌ ቦረና ማእከል አስታወቀ ።

መጋቢት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

በጉጂ፣በምዕራብ ጉጂ፣ ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከት እውቅናና በብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬና መመሪያ መሠረት በማኅበረ ቅዱሳን የነገሌ ቦረና ማእከል ከነጌሌ ቦረና ደብረ መዊዕ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሰንበት ት/ቤት እና ከወረዳው ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር ላለፉት ሦስት ወራት በምሥራቅ ቦረና ዞን ማረሚያ ቤት በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ሲያስተምራቸው የነበሩት 47 አዳዲስ አማንያንን  መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በመጠመቅና የሥላሴ ልጅነት በማግኘት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኅብረት መቀላቀላቸው ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ የሀገረ ስብከት እና የወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች፣የነገሌ ቦረና ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት እንዲሁም አጋር አካላት ተገኝተዋል።


የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አባል የሆኑት ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ  ሙሉጌታ በበኩላቸው  ሥልጠናው  ከየካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 21 ቀን ጀምሮ  ለሠላሳ ቀናት  ትምህርተ  ሃይማኖት ፣  ነገረ እግዚአብሔርና ሥነ-ፍጥረት) ፣ አምስቱ አእማደ ምስጢር ፣ ሐዋርያዊ ተልእኮ እና የስብከት ዘዴ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፣ ነገረ ማርያም እና ነገረ ቅዱሳን ፣ ነገረ ቤተ ክርስቲያን እና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፣  የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት እና ሥርዓት  ፣  ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እና መንፈሳዊነት ፣  ባሕል እና ክርስትና ፣  የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ቃለ አዋዲ ፣ የአገልግሎት መሪነት (አስተባባሪነት) ፣  ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ፣  የአሕዛብና መናፍቃን ጥያቄዎቻቸውና መልሶቻቸው የሚሉ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

ለተተኪ መምህራኑ ”የዚህ ሥልጠና ስኬታማነት የሚለካው በቆይታችሁ ባገኛችሁት ዕውቀት ብቻ ሳይሆን በምትሰማሩበት የሐዋርያዊና የእረኝነት አገልግሎት የድካምና የመሰልቸት መንፈስ ሳይሰማችሁ ስታገለግሉና ነፍሳትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትቀላቅሉ ብሎም ወደ ቅድስና ሕይወት ስትመሩ ነው“ በማለት ምክር ለግሰዋል  ፡፡

በመጨረሻም ለተተኪ መምህራኑ የምስክር ወረቀት የመሥጠት መርሐ ግብር የተከናወነ  ሲሆን የደብሩ አስተዳዳሪ ”ከጠረፋማ አካባቢ ተተኪ መምህራንን አምጥቶ  ማሠልጠን  አዲስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መመሥረት ነው የሚቆጠረው“  ብለው በመግለጽ  መልእክትና አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።


ለአንድ ወር ያህል ሲሰለጥኑ የቆዩ ሠላሳ  ተተኪ መምህራን በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም መመረቃቸው ተገለጸ

መጋቢት ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት ከሰበካ ጉባኤውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ለአንድ ወር ያህል ያሠለጠናቸውን  ሠላሳ ተተኪ መምህራን በትናትናው ዕለት መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ማስመረቁ ተገልጿል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ሀብተ ማርያም ወልደ ጊዮርጊስ፣  የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አባል  ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም (ዶ/ር) ፣ በሰሜን አሜሪካ በዴንቨር ኮሎራዶ ሀገረ ስብከት  የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ  መልአከ ሰላም  ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ፣ የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት ም/ሥራ አስኪያጅ ዲያቆን ሲሳይ ብርሃኑ፣ የበገና ዘማርያንና ምእመናን ተገኝተዋል።

መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው እንደገለጹት  መምህርነት ማለት  አደራና ጸጋ በመሆኑ መመረጥ፣ መቀደስ፣ ማስተማርን ይጠይቃል ያሉ ሲሆን ከጠረፋማ ና ከገጠራማ  አካባቢ የመጡ ተመራቂ  ተተኪ መምህራንን  በኀላፊነት  አከባቢያቸውን በቋንቋቸው እንዲያገለግሉ  መክረዋል።


የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሰብሳቢ መምህር እንዳለ ጸጋዬ   ለሥልጠናው የበኩላቸውን ድርሻ ላደረጉ ተቋማት፣ ማኅበራት፣ ጉባኤያት፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚገኙ አባላት እንዲሁም  ምእመናንን አመስግነዋል።


ወርኃዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ



Показано 8 последних публикаций.