ከእዉነታ መራቅ (Dissociative disorder)ይህ ችግር በአለማችን ላይ 1.5 በመቶ የሚሆነውን የማህበረሰብ ክፍል የሚያጠቃ የአዕምሮ ህመም መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በልጅነታቸው ፆታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ልጆች ለዚህ የስነ ልቦና ችግር የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ድንገተኛ አደጋ የሚያጋጥማቸው ሰዎችም ለዚህ ችግር ተጋላጭ መሆናቸው ይነሳል፡፡
ለዚህ ችግር ከሴቶች በበለጠ ወንዶች ተጋላጭ መሆናቸዉም ነዉ የሚገለጸዉ፡፡
ከእውነታ መራቅ (Dissociative disorder) ምን ማለት ነዉ?ዕለት ከዕለት ከሚያጋጥሙን እውነታዎች መነጠል አልያም ከአደጋ በኋላ ያጋጠሙንን ነገሮች መርሳት ማለት መሆኑ ይገለጻል፡፡
አልፎ አልፎ ደግሞ የምንወዳቸውን ሰዎች ስናጣ አዕምሯችን የምንወዳቸውን ሰዎች ማጣታችንን መቀበል ስለማይፈልግ ለዚህ ችግር ሊዳርገን እንደሚችልም ይነገራል፡፡
መንስኤዉ ምንድን ነዉ? - እራሳችን ላይ የሚያጋጥም አደጋ ወይም የምንወደውን ሰዉ በድንገት ማጣት
- ያየነውን ወይም የሰማነውን ነገር መቀበል ባለመፈለጋችን ለመሸሽ መሞከር
- የአስተዳደግ ሁኔታ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ምልክቶቹ ምንድን ናቸዉ?- አደጋ ከተፈጠረ በኃላ ሙሉ ለሙሉ ከነበሩበት ባህሪይ ወጥቶ አዲስ ባህሪይ ማሳየት
- ነገሩን ሙሉ ለሙሉ አለማስታወስ አልያም በወቅቱ የተፈጠረዉን ጥቂት ነገር አስታዉሶ ቀሪዉን ደግሞ ፈጽሞ መርሳት
- ከእዉነታው ርቆ አዕምሯችን በፈጠረዉ ነገር መኖር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?- አብሮን ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መስማማት አለመቻል
- ከስራ ባልደረባ ጋር ለመግባባት መቸገር
- እዉነት የሆነዉንና ያልሆነዉን ነገር መለየት አለመቻልን ሊያስከትል ይችላል፡፡
አብዛኛዉን ጊዜ እንደዚህ አይነት የስነ ልቦና ችግሮች የመከሰት እድላቸው ያነሰ ቢሆንም በሚከሰትበት ወቅት ግን ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ ያስፈልጋል።
በተጨማሪም በልጅነት የሚከሰቱ ጥቃቶች ለችግሩ እንደ መንስዔ ስለሚነሱ፤ ህፃናት ልጆች ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ እንዳይሆኑ በቂ ክትትል እና እንክብካቤ ሊደረግላቸዉ ይገባል፡፡
አቶ ልዑል አብርሀም (የስነ ልቦና ባለሙያ)
Via: ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@melkam_enaseb