Mereja Tv


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ωєℓ¢¢σмє тσ Mereja TV™🇪🇹
✅ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ነው
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
መረጃ ቲቪ -Mereja TV Satellite Eutelsat 8 West B Frequency 11637 / 11636 Symbol Rate 27500 5/6
🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
@meraja_tv

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


🕌☪ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለታላቁ ረመዳን ወር በሰላም፣በጤና አደረሳችሁ እያልን መልካም የፆም፣የፀሎት፣የኢባዳ ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።


ለእስልምናም ለክርስትናም ሀይማኖት ተከታዮች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ስራው ከሚያሳድብርን ጫና አንፃር ያስቀየምኳችሁ በሙሉ ይቅርታ እንድታረጉልኝ በአላህ ስም እጠይቃችኋለው!

#ረመዳን_ከሪም ☪☪
@happybirthdaypic


#ጥበብ_እንቁ_ልጇን_ተነጠቀች

ትውልዱ እዚሁ አዲስ አበባ ተክለ ሀይማኖት ሰፈር የነበረው ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) ብዙዎች የሚወዱትና የሚያደንቁት የጥበብ ልጅ ነበረ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይም በቅንነትና በታዛዥነት ተሳትፏል።

ከሰራቸው ፊልሞች መካከል፦
ባላ ገሩ, 300 ሺ , አስነኪኝ,  የፍቅር ABCD, ብላቴና, 3+1, ቦሌ ማነቂያ, እንደ ባል እና ሚስት, ኢንጂነሮቹ, እርቅ ይሁን, ኢዮሪካ, ጉዳዬ, ሀገርሽ ሀገሬ, ሕይወቴ , ህይወት እና ሳቅ, ከባድ ሚዛን, ፍቅር እና ፌስቡክ, ከቃል በላይ, ላውንድሪ ቦይ, ኮከባችን, ማርትሬዛ, ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2, ሞኙ የአራዳ ልጅ 4, ትዳርን ፍለጋ, አንድ ሁለት, ወደው አይሰርቁ, ወፌ ቆመች, ወንድሜ ያዕቆብ, እንደ ቀልድ, ወቶ አደር, አባት ሀገር, የሞግዚቷ ልጆች, ብር ርር, ይዋጣልን, ዋሻው, ወሬ ነጋሪ, ወጣት በ97

ሞትህን መስማት ያማል፡
#ነፍስህን_ይማር። ልቅሶ መድረስ የምትፈልጉ የታሬ ቤት ተክለሀይማኖት ፔፕሲ አጠገብ ነው።
😢😢😢
Join us
@meraja_tv


ድምፃዊ አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ‼️

እዉቁ እና ተወዳጁ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ድምፃዊ አሊ ቢራ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ባወጣዉ የሀዘን መግለጫ አስታዉቋል።


#ተፈፀመ

የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥተ ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።

ከሥርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ዘመድ ወዳጆች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና አድናቂዎቹ በተገኙበት በመኖሪያ ቤቱ እና በወዳጅነት ዐደባባይ የአስከሬን ሽኝት ተካሂዷል፡፡

በመንበረ ጸባኦት ቅድሥተ ሥላሴ ካቴድራል በነበረው የቀብር ስነሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ፣ የድምፃዊው ቤተሰቦች ፤ የስራ ባልደረቦች ፤ ጓደኞች ፤ ወዳጆች ፤ አድናቂዎች ተገኝተው ነበር።

መስከረም 17 ህመም ተሰምቶት ወደ አንድ ክሊኒክ ከሄደ በኃላ ህይወቱ ያለፈው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የአንዲት የ17 ዓመት ሴት ልጅ አባት ነበር።

ከድምፃዊ ማዲንጎ ህልፈት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን እንደሚያሳውቅ መግለፁ አይዘነጋም።

@meraja_tv


ሰበር አስደሳች
ዜና block ያረጋችሁን ሰዉ unblock ሚያረግ telegram bot መጣ ፎቶ ላይ ምታዩት bot ነዉ block ያረጋችሁን ሰዉ ስልክ ቁጥር ወይ username ላኩለት ቦቱ unblock ያረጋል😎ከስር start bot ሚለሁን ነክተዉ መመልከት ትችላላቹ ማሳሰቢያ ቦቱ ለwifi ተጠቃሚ አይሰራም


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የማዲንጎ ወንድም ያሬድ አፈወርቅ ከካናዳ የማዲንጎ ወዳጆችና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት ወደ ኢትዮጵያ ሸኝተውታል::


#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ፦

- በኮምፒውተር ሳይንስ፣
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣
- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣
- ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም እና ተዛማጅ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ተማሪዎች #በልዩ_ሁኔታ የስራ ቅጥር ለመፈፀም ማስታወቂያ አውጥቷል።

በሶፍትዌር ልማት ላይ ልዩ ተሰጥኦ ወይም አቅም ያላቸሁ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን መሰረታዊ መረጃችሁን የያዘ ሲቪ (CV) ከሁለት /2/ ገፅ ያልበለጠ እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም እንድታያይዙ ተቋሙ ጠይቋል።

@meraja_tv


#MadingoAfework

የተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

ስርዓተ ቀብሩ 4 ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ነው የተነገረው።

የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ሲሆን የኮሚቴው ቃል አቀባይ ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን " የቀብር ሥነ ስርዓቱ ሐሙስ ዕለት በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል። ከቀብር ሥነ ስርዓቱ አስቀድሞም የሽኝት ፕሮግራም ይካሄዳል " ብሏል።

ይህን በተመለከተ ዝርዝሩን ኮሚቴው በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ተናግሯል።

@meraja_tv


" እስካሁን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው የለም፤ ነገር ግን አንድ ሐኪም ቃል እንዲሰጥ ተደርጎ ተለቋል " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አስክሬን ምርመራ እንደተጠናቀቀ ውጤቱ ለህዝብ ይገለፃል ሲል አሳውቋል።

ማምሻውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤  " ማዲንጎ ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 17/2015 ዓ.ም. ጠዋት 1፡30 አካባቢ ለሐኪሙ ስልክ እንደደወለና ወደ ክሊኒክ መሄዱን ፖሊስ ተረድቷል። " ብለዋል።

ከዚያም በኋላ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወደሚገኘው አንድ የግል ክሊኒክ በመሄድ የህመም ማስታገሻዎችን እና ሌሎች መድኃኒቶችን ወስዶ እንደነበር ተናግረዋል።

ማዲንጎ ሕይወቱ ያለፈው ረፋድ 3፡00 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል።

የድምጻዊ ማዲንጎ አስክሬን ሕይወቱ ካለፈበት የግል ክሊኒክ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ማርቆስ " ፖሊስ በቀረበለት አቤቱታ መሠረት የድምጻዊውን ሞት መንስኤ ለማወቅ የአስክሬን ምርመራ ውጤቱን እየተጠባበቀ ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ፖሊስ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ከማዲንጎ ህልፈት ጋር በተያያዘ ህክምና ካገኘበት ክሊኒክ ሠራተኞች ታስረዋል ስለሚባለው ጉዳይ ም/ኮማንደር ማርቆስ ፤ " እስካሁን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው የለም፤ ነገር ግን አንድ ሐኪም ቃል እንዲሰጥ ተደርጎ ተለቋል " ሲሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@meraja_tv


ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ?

- ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 ወሩ ወላጆቹ ደብረ ታቦር መግባታቸውን ተከትሎ በደ/ታቦር ነው ያደገው።

- ማዲንጎ አፈወርቅ ያደገው በጦር ቤት ውስጥ ነው፤ እናት እና አባቱ "ተገኔ" /የኔ ጠበቃ/ ነበር የሚሉት፤ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ተገኔ" ነው። ማዲንጎ የሚለውን ስም ያገኘው በወታደር ቤት ውስጥ እየሰራ እያለ ነው፤ ከዛ በኃላ መጠሪያው ሆኖ ቀጥሏል።

- በልጅነቱ የሙዚቃ ፍቅር ያደረገበት ማዲንጎ ከደብረ ታቦር ወደ አዘዞ በተመለሰበት ወቅት በ7ኛ ክፍለ ጦር ካምፕ ውስጥ በ603ኛ ኮር ውስጥ ያለ የሙዚቃ ቡድን ልምምድ ሲያደርግ በመግባት ዘፈን እንደሚችል በመግለፅ እድል እንዲሰጠው ይጠይቃል፤በኃላም እድል ተሰጥቶ የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃ ከተጫወተ በኃላ አድናቆት በማግኘቱ ተቀባይነት አግኝቶ በዛው ሊቀጥል ችሏል።

- ማዲንጎ ከጦሩ ከወጣ በኃላ በ1982 ዓ/ም አካባቢ ገና በ12 ዓመቱ በባህር ዳር የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አንድም ድምፃዊ የመሆን ህልሙን መስመር ያስያዘበት በሌላ በኩል ገቢ በማግኘት እራሱንና ቤተሰቦቹን ማገዝ የቻለበትን ሁኔታ መፍጠር ችሏል።

- ማዲንጎ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኃላ በተለያዩ የሙዚቃ ክበቦች የተለያዩ አንጋፋ ድምፃዊያንን ስራዎች ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን በኃላም የራሱን ስራዎች (ነጠላና የአልበም ስራዎች) ለአድናቂዎቹ አቅርቧል።

- ማዲንጎን በስራዎቹ የሚያውቁት ወዳጆቹ ዜማ በመያዝ ችሎታ፣ ሙዚቃን አሳምሮ በመጫወትና የአድናቂዎቹን ቀልብ በመሳብ የተካነ በማህበራዊ ህይወቱም ተግባቢ፣ ቅንና ተጫዋች እንደሆነ ይመሰክሩለታል።

(ከጨዋታ እንግዳ ፕሮግራም/ከቅርብ ወዳጆቹ የተገኘ መረጃ)

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

@meraja_tv


" አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል " - ፖሊስ

ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ከሆነ ፤ ድምፃዊው ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወደ ሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ለሕክምና መሄዱና ሕክምና ማድረጉን ከቆይታ በኋላም ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ማዲንጎ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።

የድምፃዊው ወዳጆች በበኩላቸው ፤ ማዲንጎ ህመም ተሰምቶት እራሱ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ህክምና ስፍራ መሄዱን ከዛ በኃላ ህይወቱ እንዳለፈ ጠቁመዋል።

@meraja_tv


#MadingoAfework

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@meraja_tv


እጃቸውን ከሠጡ አንደበት ‼️

በማይጠብሪ ግንባር እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊታችን የሠጡ የአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች እንደተናገሩት የትግራይ ወጣቶች አማራጮች ሁሉ ተዘግተውበታል።

ይህ የሆነው ደግሞ የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች ተከበሃል፣ከጦርነት ውጭ አማራጭ የለህም እያሉ በመስበክ እና የጦርነት ነጋሪ በመጎሰም ነው።

ትግራይ የምትኖረው የትግራይ ህዝብ ሲኖር ነው ያሉት እጃቸውን የሠጡት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች የትግራይ አመራሮች ህዝቡን ወደ ጦርነት እየማገዱ አያስጨረሱት ነው ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ተኩሰናል። ሰራዊቱ አልገደለንም። ሰብአዊነታቸውን በተግባር አይተናል። ከተነገረን በተቃራኒ በእንክብካቤ ነው የያዙን። አክመውናል፣ አብልተውል፣ አጠጥተውናል ብለዋል።

ትክክለኛዉ የቶፕ መረጃ ቴሌግራም ገፅ ይህ ብቻ ነው ሼር አድርጉ 👉  t.me/meraja_tv


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በከባድ መሳሪያ በታገዘ ጥቃት 3 ቀናትን ያስቆጠረው የአፋርና የሶማሌ ክልል ግጭት በብዙ የንፁሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የፌዴራል መንግስቱ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
@meraja_tv

Показано 14 последних публикаций.

1 926

подписчиков
Статистика канала