ፍቅር አልባ ሳልሆን መጡ በሂወቴ
በሩቅ የናፈቁ እያሉ ኡመቴ
ሲቃይ መከራ ርሀብ በሞላበት
በዛ በበረሃ ነበር ያንቱ ሂወት
ናፍቀውኝ በሩቁ ሳልወለድ ያኔ
ደስታዬ ቅጥ አጣ ያንቱ በመሆኔ
በናፍቆቴ ብዛት ሳያለቅስ አይኔ
ሳልሆነ ካጠገብ ነበሩ ከጎኔ
የሂወት ተምሳሌት መሪ መምህሬ
በተግባር የተየ አይደለም በወሬ
ዝንት አለም የኖረ የፍቅሬ ምርኮኛ
አለም ያስለቀሱ ሆነው ጥበበኛ
አይወራ እንጂ ቢወራማ ከቶ
የስቃዩ ነገር አያልቅም ተወርቶ
ናፈቁኝ ሀቢቢ ናፈቁኝ ያነቢ (2×)
የመካ ሙሽሪኮች ትዛዙን አዘዙ
እብድም ውሸታም ብለው አወገዙ
ቢሎ ቢመክራቸው አላህን ተገዙ
አንሰማም ብለው ፃኦትን ተናዘዙ
ተሰበረ ጥርሱ ሆዱንም አሰረ
የሚበላ ጠፍቶ ሂወት እየኖረ
ምግብ ውሃ ሳይቀምስ ፆሙንም አደረ
ለነብሱ ሳይሳሳ ለአላህ ሲል የኖረ
አንጀቱ ያሰረ በራብ ተንገላቶ
አኖረኝ አንግሶ ጊዜውን ሰውቶ
ቆሰሉና ደሙ ግንባር ተፈንክቶ
ቢራቡ ነውጂ መች ሆዳቸው ሞልቶ
ናፈቁኝ ሀቢቢ ናፈቁኝ ያ ነቢ(2×)
ማሸቅ ነው ለነቢ ለአለሙ ምርጥ
ሇላ እንዳይቆጨን አለብን ሲራጥ
ናፍቆቴ ሀይሎ ገንፍሎ ቢወጣ
ሁሌ የሚኖረው ከልብ የማይወጣ
አስቸግሮጂ የናፍቆቱ ነገር
እያደር የባሰ ሰው ሚያደናግር
ሆዴን ይፈጀኛል ያንቱማ ከበር
የሲዲቅ ጓደኛ የጀግናው ኡመር
ፊዳ ልሁን ብዬ ባፌ ብናገር
አውርቼ ቀረሁኝ አቅቶኝ ተግባር
ሩሄን አድርጎት ከዚሁ ሀበሻ
አንቱ ነሁ ሀቢቢ የፍቅሬ መነሻ
አልቅሰው የኖሩ ያን ጊዜ በሩቁ
ያኔ በዛ ዘመን ወንድም የናፈቁ
ያንጊዜ በሩቁ እንባ ያፈሰሱ
ኡመቴ ኡመቴ ብለው አለቀሱ
✍️አቡበከር ሰኢድ