✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


✅:አላማው ˙ እንዴት የኢስላማዊ አስተምህሮት ግንዛቤን መጨመር እንችላለን።
ᘛ በሌላም በኩል࿐
▮ሀዲስ📚
▮በድምፅ ትምህርቶች🎤
▮የቁርአን ቲላዋ📖
▮አጫጭር ትምህርቶች📝
▮ከታሪክ ማህደር📜
▮ጠቃሚ አፖች📲
▮ሌላም. . .📧
ᘛ ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉ ✓
@Muslim_group2
─────⊱◈🌟◈⊰─────
📬:አስተያየት ༻
@Muslim_comment_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


መከራ ያልፈታው ነቢያዊ ሕይወት 🍃

➣:እኛና አላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

:በምድር ላይ እያለን ጉዳት ደርሶብናል ፤ ብዙ መከራ አይተናል የምንል ሰዎች እስቲ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማስተዋል የኛን እና ከአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ሁኔታ እናነፃፅር፡፡ ምን እንደረሰባቸውና ምን እንደደረሰብን እናመዛዝን ⚖

🪴:እናት አባትህ አሉ?

➣:እርሣቸው እኮ ያለ እናትና አባት ነው ያደጉት፡፡ አባታቸው ሳይወለዱ ፣ እናታቸው ደግሞ ገና
#የአምስት እና ስድስት ዓመት ልጅ እያሉ ነበር የሞቱባቸው፡፡

🪴:ልጆችህን አጥተሃል?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሁሉም ስድስት ልጆቻቸው እርሣቸው በህይወት እያሉ  ሞተዉባቸዋል፡፡ ከሴት ልጃቸው ፋጢማ በስተቀር፡፡

🪴:ሥምህ ጠፍቷል አሊያም ተሰድበሃል፣ ተደብድበሃል?

➣:እርሣቸው እኮ ተሰድበዋል፣ ተደብድበዋል፣ ገጣሚ፣ መተተኛ/ደጋሚ ተብለዋል፡፡ የመካና የጣኢፍ ምድሮችም የሚመሰክሩት ይህንኑ ነው፡፡

🪴:በቤተሰብህ የመጣብህ ችግር አለ?

➣:ባለቤታቸው በመናፍቃን በዝሙት ሥማቸው ጠፍቷል፡፡ በዚህም የእርሣቸውም የታላቁ ነቢይ
#ክብር ተነክቷል፡፡

🪴:ዕዳ አለብህ?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሲሞቱ ዕዳ ነበረባቸው፡፡ የጦር ልብሳቸው አንድ አይሁዲ ዘንድ በዕዳ ተይዞ ነበር፡፡

🪴:ተቸግረህ ፣ ተርበህ ታውቃለህ?

➣:ረሱሉ እኮ ከርሃብ የተነሳ ሁለት ሶስት ድንጋዮችን በሆዳቸው ላይ ያስሩ ነበር፡፡ ለምግብ ማብሰያ የሚሆን እሣት በቤታቸው ሳይቀጣጠል ተምርና ውሃ ብቻ እየተመገቡ ወራትን ያሳልፉ ነበር፡፡

🪴:ልጅህ ወይም የቅርብ ዘመድህ ተፈታ በሷ ሥነልቦና ተጎድተህ ታውቃለህ?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እስልምናን በመስበካቸውና የአላህን የሐቅ መንገድ በማሳየታቸው ብቻ ተጠልተው  ሁለት ሴት ልጆቻቸው በባሎቻቸው ተፈተዋል፡፡

🪴:ሳትወድ በግድ ከምትወደው የትውልድ ሀገርህ ተሰደህ ታውቃለህ?

➣:የአላህ መልዕክተኛ እኮ ተከታዮቻውን ይዘው እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ ተሰደዋል፡፡ ለዓመታትም የስደት ሕይወት ገፍተዋል፡፡ 

🪴:የግድያ ሙከራ ተደርጎብህ ያውቃል?

➣:ነቢዩ (ﷺ) ከአንድና ሁለት ሶስት ጊዜ በላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡

🪴:በአደባባይ ቆሻሻ ተጥሎብህና ተስቆብህ ያውቃል?

➣:
#ነቢዩ እኮ ሰላት በመስገድ ላይ እያሉ ሱጁድ ላይ ሆነው ቆሻሻ ተጥሎባቸዋል፡፡ለዛውም የግመል ፈርስ።

🪴:የእምነት ነፃነትህን ተነፍገሃል?

➣:የአላህ መልዕክተኛ
#ለሶስት አመታት እምነታቸውን ደብቀው ኖረዋል፡፡

🪴:ማዕቀብ ተጥሎብህ ያውቃል?

➣:ረሱሉ እኮ
#ለሦስት አመታት ያህል ማዕቀብ ተጥሎባቸው ከማህበረሰቡ እንዲገለሉ ተደርገዋል፡፡

🪴:አካልህ ላይ ጉዳት ደርሶ ያውቃል?

➣ነቢያችን እኮ ተፈንክተዋል፣ ጥርሣቸው ተሰብሯል፡፡

❦ ════ •⊰
🌴⊱• ════ ❦

📌:ምናልባት አንተን እና እኔን አንድ ችግር አግኝቶን ያንኑ ችግር መቋቋም ተስኖን ይሆናል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ግን ከነኚህና መሰል ብዙ ችግሮች ጋር  ምንም እንዳልሆኑ ሆነው እያመሰገኑ ደስተኛ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዐለይሂ~~~৲
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CH
L@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁
•═════╣
🌐 #SHARE_The_خ
ير🔺


ሰላት ውስጥ መሳቅ 🔍

📌:ሶላት ውስጥ ብዙ ጊዜ ሳቅ ያስቸግረኛልና ሶላቴን ያበላሸዋልንዴ ፣ ከዚህስ ነገር ምን ባደርግ መከላከል እችላለሁ

#መልስ 💬

¹:ሶላት ውስጥ መሳቅ #ድምፅን በማውጣት ወይም ሁለትና ከዛ በላይ #ፊደላትን በማውጣት ከሆነ ይህ እንደ ንግግር ይቆጠራልና ሶላቱን #ያበላሸዋል። ድምፅና ፊደል የሌለው #ፈገግታ ግን ሶላቱን #አያበላሸውም። ሳቁን መቆጣጠር ያልቻለና #ከአቅሙ_በላይ የሆነ ግን ከፍላጎቱ ውጭ ስለሆነ ሶላቱ #አይበላሽም

²:ሶላት ውስጥ በተደጋጋሚ በመሳቅ #የተፈተነ ሰው ደግሞ በተደጋጋሚ ውዱእ በመፍታት እንደሚቸገር ሰው አይነት ፍርድ ይኖረዋልና ሶላቱ #አይበላሽም። በዚህ የተፈተነ ነው ሶላት ውስጥ #በማስተንተን ፣ ሀሳብን #በመሰብሰብ ፣ አሏህ #ፊት መቆምንና በአሏህም #እይታ ስር መሆንን በማሰብ ሳቅን #ለመከላከል መሞከር ተገቢ ነው።

•📗。*。📙。
📘。\|/。📒
        ▽{ምንጭ🗂}
📔。/|\。📕
•📓。*。🗃 °

[ሸርሁል ሙምቲዕ ፣ ለኢብኑ ዑሰይሚን ፣ 3/366 ፤ ኒሀየቱል ሙህታጅ ፣ ለኢማሙ አሽሻፊዒይ ፣ 3/39 ፤  ኪታቡል ሙግኒ ፣ ለኢብኑ ቁዳማህ ፣ 1/741]

©MJUD
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CH
L@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁
•═════╣
🌐 #SHARE_The_خ
ير🔺


100 መፅሀፍ 📔 ❔

📝:ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነውና #ትዕግስትን በተላበሰ ህሊና ይነበብ፡፡

─━━━━━━⊱
🖱️⊰━━━━━━─

¹:በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።

²:ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንክ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።

³:የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን #አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ #አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል።

⁴:ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

⁵:የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።

⁶:ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት 💡

⁷:ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስክ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።

⁸:ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።

⁹:#እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ።

¹⁰:ሥልጣን ሲሰጥህ #መሪ(leader) እንጂ አለቃ(boss) አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምክ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ። ለበለጠ ለመረዳት👉 @Better_understanding

¹¹:በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።

¹²:የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።

¹³:ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! 👏

¹⁴:መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠሉሃል ።

¹⁵:ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።

¹⁶:#ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ።

#እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ~ ⚠️

¹⁷:#ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው።

¹⁸:#ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ #ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ #ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

¹⁹:የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ። የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

²⁰:ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን።

²¹:ሁሉን #ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

²²:#ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።

²³:እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጀነት ውስጥ . . .🍀


📨:ወደ መልካም ነገር ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው። መሥራት ባትችሉ አመላክቱ ፣ መፃፍ ባትችሉ ሌሎች የፃፉትን አጋሩ።

↬ዱንያ ላይ የምንቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። ምድር ላይ እንደሁለተኛ ዕድሜ ሆኖ የሚያገለግለን ዛሬ እዚህ የምንጽፈው ነገር ነው። ከሶላታችን ፣ ከፆማችን ምንም ምንዳ ላይኖረን ይችላል። መልካም ነገሮችን ማጋራት ወደ አኺራችን ከምናስቀድማቸው ጠቃሚ ስንቆች መካከል አንዱ ነው። ብልህ እንሁን። አላህ ያፅናን።

🔴 ዓለማዊ ጥቅም አለው ብዬ አልወተዉታችሁም፣ በስነልቦናም ሆነ በዲኑ ጉዳይ ሊጠቀምበት የሚችል ሰው ሊኖር ይችላልና ይህን #ቻናል አጋሩት።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ሙሉ ለማዳመጥ ⬇️

T.me/Muslimchannel2/1843


#ጭንቀት 😣

💥:በመጨነቅና በማማረር ያመጣነው ለውጥ የለም፡፡ ተነስቶ መንቀሳቀስ እንጂ ዘግቶ ማልቀስ የፈየደን ነገር አላየንም፡፡ በጭንቀት ስንዝር ያህል እንኳን ነገሮችን መግፋት አንችልም፡፡ የጎደለ ኑሮ የሚሞላው #በሥራ እንጂ በጭንቀት አይደለም፡፡ ተጨንቀን ብዙ አየን፡፡ ጭንቀትን ትተንም አየን፡፡ ሰፊ ልዩነቱን በርግጥም አስተዋልን፡፡ ዘና ብለን ስንስቅላቸው ረጃጅም ቀናቶች አለፉ፡፡ ትላልቅ ሸክሞች ረገፉ፡፡ ከባባድ ችግሮችም ተረሱ፡፡ እናም ፈታ በል ፤ ዘና በል፡፡ አትጨነቂ ፣ አትጨነቅ 🦋

:የነገሮች ዋና መሰረታቸው ቀደር ነው፡፡ ቀደር ማለት ደግሞ ቀድሞ የተላለፈ የአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ውሳኔ ነው፡፡ ለተወሰነና ላለፈ ነገር "መዐልኤሽ!" ምንም ማለት አይደለም በል፡፡

❗️ብርጭቆ ሰበረ ብለህ ልጅህን ከቤት አታባርር፡፡

❗️እንጀራው አረረ ብለህ ከሠራተኛህ ጋር ቦክስ አትግጠም፡፡

🔎አንዳንድ ሰዎች ይገርሙኛል ፤ ሳይመቱ ከተመቱት በላይ ይጮሃሉ፡፡ መቶኝ ነበር ፈንክቶኝ ነበር ለጥቂት ነው የሳተኝ ብለው ቂያማ ያቆማሉ፡፡ እንኳንም የሳተህ ባይስትህ ኖሮ ጣጣህ ብዙ ነበር፡፡ ሳይፈነክትህ እንዲህ የሆነክ ቢፈነክትህ ኖሮ እንዴት ትሆን ነበር!፡፡ በዚህች ዓለም ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ በርሱ ፈቃድ ነው፡፡ በፈቃዱ ተማረን ምን ልናመጣ ነው?፡፡ የወደደውን አንወድም ብለን ምን ልንሆን!፡፡ ፌንጣ ብትቆጣ ክንፏን ጥላ መብረር ካልሆነ ምን ልታመጣ!

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

💡:እስልምና አትጨነቁ ይላል፡፡ የፈጠረን ጌታ ‹እመኑ፣ በርቱ፣ ትጉ፣ ተስፋ አትቁረጡ፣ አትስነፉ፣ አትድከሙ፣ አትዘኑ፣ አይዟችሁ፡፡ …› ብሏል፡፡ በመልካም ትዕግስትና ተስፋ አደራ ይላል፡፡ በጥሩ መጨረሻና ስኬት ቃል ይገባል፡፡ ነቢዩ (ﷺ) ምንም ሊረዷቸው ባልቻሉ ጊዜ ‹የያሲር ቤተሰቦች ሆይ! ትእግስት አድርጉ ቀጠሮአችሁ ጀነት ነው፡፡› ብለዋቸዋል፡፡

:ሞኝ የሆነ ይጨነቅ፡፡ እኔ ሞኝ አይደለሁም አልጨነቅም፡፡ ዕድሜዬ አጭር መሆኗን አውቃለሁ፡፡ መሞቴ ላይቀር ለምን ቀድሜ እሞታለሁ፤ ለማንስ ለምንስ ብዬ እታነቃለሁ፡፡ መድረሱ ላይቀር ለምን ቀድሜ ፈግማለሁ፡፡ አልጨነቅም - ተጨንቄ ምን አገኘሁ! ተበሳጭቼስ ምን አተረፍኩ፡፡ ተናደውና ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቶአቸው ሰው የደበደቡ እስር ቤት ናቸው፡፡ ተበሳጭተው የተሳደቡ ‹ምኑ ባለጌ ነው?› ተብለው በሰዎች ትዝብት ዉስጥ ገብተዋል፡፡ ስብእናቸውን አስንቀዋል፡፡ ምን አስጨነቀኝ፡፡ ቦታዬ አላህ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ አላህ ዘንድ አልጉደል እንጂ እዚህ ኪሎዬን ቢቀንሱ ስድባቸው አይለጠፍብኝም፡፡ ከአላህ ጋር እስካለሁ ዘና እላለሁ፡፡

:የደስታችን መሰረቱ አላህ ብቻ ይሁን፡፡ ከሁሉም በላይ ከርሱ ጋር የሚኖረንን ግንኙነት እናሳምር፣ እሱ እንዳለውና እንዳዘዘው ለመኖር እንሞክር፣ ህግጋቱን ከመጣስ እንጠንቀቅ፣ ድንበሩን አንጋፋ፡፡ ከአላህ ጋር ስንሆን አካላዊ ለውጥ ላይኖረን ይችል ይሆናል፣ ኪሎ ላንጨምር እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ዉስጣዊ ሰላምና የበዛ ደስታ ይኖረናል፡፡ በዚህ ደግሞ ሁሉንም ነገር ማሸነፍ እንችላለን፡፡ ጣሉት ጃሉድን ያሸነፈው፣ ሙሳ ፈርዐውንን የረታው፣ ኢብኑ መስዑድ አቡጀሀል አንገት ላይ የወጣው … በሥጋ ግዝፈት ሳይሆን በኢማን ጥንካሬ ነው፡፡ የኢብኑ መስዑድ እግር ቅጥነቱ ቢያስገርምም ‹የቂማ ቀን ሚዛን ላይ ከኡሑድ ተራራ በላይ ክብደት አለው፡፡› ብለዋል ነቢዩ (ﷺ)፡፡

┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀
📚
┊  ✿
🔝
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺


#መልካም_ኒያ ❤️‍🩹

:አንድ አማኝ መልካም #ኒያ እስካለው ድረስ በእያንዳንዱ ተግባራቱ ከአላህ #ምንዳን ይሸለማል። በኒያው ማማርና በቀልቡ መስተካከል ምክንያት ፍቁድ የሚባሉት ነገራቶች በሙሉ ከመልካም ስራዎቹ ይመደቡለታል።

𖡇 ኢብኑ ተይሚያህ
🌿

#ይህም_ማለት

😎:መብላት፣ መጠጣት፣ መተኛት፣ ዱንያዊ ስራን መስራት፣ መልበስ፣ መጫወት፣ መዝናናት----- በመልካም ኒያ ምክንያት አጅር የሚያስገኝ መልካም ስራ ሆኖ ይመዘገባል ማለት ነው።

📑:አልወሷያ ሰለፊያ

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌 


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ገራሚ ቲላዋ😍


📌:መልካም ስራ በ3 ነገሮች ቢሆን እንጂ የተሟላ አይሆንም፦

: ስራውን በማፍጠን ¹

:ትንሽ አድርጎ በማየትና ²

:በድብቅ መፈፀም ³

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌 


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🦋


💠አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና። የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን ስታስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

አላህ መልካም የምንስራ ያድርገን
~🤲

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🥹


ጂን | جن 👺

:"ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው። “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ኢብሊስ ደግሞ ተፈጥርዎ #ከጂን ነው፦

🔹:وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ . . .

🔸:ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ከጋኔን (ጎሳ) ነበር፡፡ . . .(18:50)

:ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፦

🔹:وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ

🔸:ጃንንም (ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡(አል ሂጅር)

🔹:يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

🔸:እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡(2:21)

🔹:وَاتَّقُوا الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالْجِبِلَّةَ الْأَوَّلِينَ

🔸:«ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች (የፈጠረውን) ፍሩ፡፡»(26:184)

   ─━━━━━━⊱
⬇️⊰━━━━━━─

:ጂኒዎች እንደ ሰው ነፃ ፈቃድ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው ፤ እንደ ሰው አላህን ሊያመልኩ የተፈጠሩ ፍጡሮች ናቸው፦

🔹:وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

🔸:ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡(51:56)

:በመቀጠል #ኢብሊስ በአላህ ላይ ሲያምፅ #ሸይጧን ሆነ፤ “ሸይጧን” شيطان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شياطين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ ሸይጧን የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም።

:ጂኒዎች ህይወት እንዳላቸው ሁሉ ይሞታሉ፦

🔹:أَوَلَمْ يَنظُرُوا فِي مَلَكُوتِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ مِن شَيْءٍ وَأَنْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ قَدِ اقْتَرَبَ أَجَلُهُمْ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ

🔸:በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛው ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜያቸውም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መኾኑን አያስተውሉምን ከእርሱም (ከቁርኣን) ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ፡፡(7:185)

:የሞት ጊዜ ካለበት ፍጡር መካከል አንዱ የጅን ሞት ነው፤ ነብያችንም”ﷺ” ይህንን ነግረውናል፦

📗:ኢማም ቡኻሪይ በዘገቡት ሀዲስ ላይ ነብዩﷺ እንዲህ ይሉ ነበር፦

"በሃያልነትህ እጠበቃለው፤ በእውነት የሚመለክ ከአንተ ከማትሞተው ሌላ የለም፤
#ጂን እና #ሰው ግን #ይሞታል

أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ “‏ أَعُوذُ بِعِزَّتِكَ الَّذِي لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، الَّذِي لاَ يَمُوتُ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ يَمُوتُونَ ‏”‌‏.‏

   ─━━━━━━⊱
⬇️⊰━━━━━━─

:የትንሳኤ ቀንን ቀጠሮ ጂኒዎች ማወቃቸው የምናውቀው የትንሳኤ ቀንን የሚያሳስቡ ከጂኒዎች መካከል የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞች ለጂኒዎች ተልከው እንደ ነበር አላህ መናገሩ ነው፦

🔹:وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ قَدِ اسْتَكْثَرْتُم مِّنَ الْإِنسِ ۖ وَقَالَ أَوْلِيَاؤُهُم مِّنَ الْإِنسِ رَبَّنَا اسْتَمْتَعَ بَعْضُنَا بِبَعْضٍ وَبَلَغْنَا أَجَلَنَا الَّذِي أَجَّلْتَ لَنَا ۚ قَالَ النَّارُ مَثْوَاكُمْ خَالِدِينَ فِيهَا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ

🔸:ሁሉንም የሚሰበስብባቸውንም ቀን (አስታውስ)፡፡፡ የአጋንንት ጭፍሮች ሆይ! ከሰዎች (ጭፍራን በማጥመም) በእርግጥ አበዛችሁ (ይባላሉ)፡፡ ከሰዎችም የኾኑት ወዳጆቻቸው፡-«ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ፡፡ ያንንም ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን» ይላሉ፡፡ እሳት አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ መኖሪያችሁ ናት ይላቸዋል፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡(6:128)

🔸:የጋኔንና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ!፡- «አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን (ቅጣት) ማግኘትን የሚያስፈራሩዋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን» (ይባላሉ)፡፡ «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን፤ (መጥተውልናል)» ይላሉ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት አታለለቻቸው፡፡ በነፍሶቻቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ፡፡(6:130)

:ይህ የትንሳኤ ቀን ቀጠሮ ለሁሉም የተቀጠረ ነው፦

➣(44:38-40) ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም። ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፤ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።”
#የመለያው #ቀን #ለሁሉም #ቀጠሯቸው” ነው።

➣(55:31-39) እናንተ ”
#ሁለት ከባዶች ሰዎችና ጋኔኖች” ሆይ፥ ለናንተ መቆጣጠር በእርገጥ እናስባለን፤ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? #የጋኔንና #የሰው ጭፍሮች ሆይ ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፤ በስልጣን እንጅ አትወጡም። ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?”#በሁለታችሁም” ላይ ከእሳት ነበልባል ጭስም ይላክባችኋል፤ ሁለታችሁም አትረዱምም። ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፥ እንደታረበ ቆዳ በሆነች ጊዜ፤ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? “#በዚያም #ቀን #ሰውም “ጃንም#” ከኃጢአቱ ገና አይጠየቅም።

:ለጂኒዎችም ጀነት ወይም ጀሃነም አለ፦

➣(11:119) የጌታህም ቃል፣ ገሀነምን ከጂኒዎና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ በማለት ተፈጸመች።

➣(55:45-46) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው፥ ሁለት ገነቶች አሉት።

🔎:በተለይ “ጌታችሁ” የሚለው ቃል “ረቢኩማ” رَبِّكُمَا ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ “ታስተባብላላችሁ” የሚለው ቃል “ቱከዚባኒ” تُكَذِّبَانِ ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል።

منقول
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
📌
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺


🐏የበግ ሽንት🤔

📌:የበግ እና የፍየል #ሽንታቸውና #በጠጣቸው ይነጅሳልን? ከነጀሰስ በሱ የተሰገደ ሶላት #መድገም አለብን

➡️≠「 #መልስ  」∬

:ስጋቸው #የሚበላ ማንኛውም እንስሳ ሽንታቸውም ሆነ ሰገራቸው #አይነጅስም። ለዛም ነው ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም  ወደ መዲና ገብተው የታመሙትን ሰዎች የግመል #ሽንትና ወተት እንዲጠጡ ያዘዟቸው። ሽንቱ ነጃሳ ቢሆን ኖሮ እንዲጠጡት ባላዘዟቸው ነበር።

➡️በሌላም ወቅት #የበግ ጉረኖ ወይም ማደሪያ ሽንታቸውና በጠጣቸው ያለበት መሆኑን #እያወቁ ውስጡ #መስገድ እንዴት ይታያል ተብለው ሲጠየቁ ችግር እንደሌለውና እንዲሰግዱ አመላክተዋቸዋል ። ይህ ሽንትም ሆነ ሰገራ የነካውን #ልብስ ማጠብም ግዴታ አይደለም። በሱም መስገድም #ይቻላል። ሶላቱንም መድገም አይጠበቅበትም።

•📗。*。📙。
📘。\|/。📒
       
🖱{ምንጭ🗂}
📔。/|\。📕
•📓。*。🗃 °

➡️[ 📚ኢብኑ ተይሚያ ፣ መጅሙኡል ፈታዊ ፣ 21/542 ፣ 📚ኢብኑ ቁዳማ ፣ ኪታቡል ሙግኒ ፣ 2/492 ፣ 📚የሳዑዲ የኢልም ጥናትና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ፣ 6/414 ]⬅️
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📚
┊  ✿
📌
❀ ✨                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP•
@Muslim_group2      
┣━━━━╗
❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL•
@Muslimchannel2
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير🔺


#ከአላህ_ተዓምራት(ከእንስሳት ዐለም) 💡:በህይወት ዘመኑ መቼም ቢሆን የማይታመመው ወይም በሽታ የማያጠቃው(ካንሰርን ጨምሮ) እንስሳ ማን ነው❓
Опрос
  •   ሻርኮች🦈
  •   አይጦች🐁
  •   ኤሊዎች🐢
254 голосов


💡ልብ በል ! #ጀነት ተውበት በሚያደርጉ ወንጀለኞች የተሞላች ናት። በአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ !

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
⚡️


#ካገኘሁት 🖥

:መልካምነት ደግ መስራት ብቻ ሳይሆን ክፉም አለመስራት ነው።

:መኖርን እንደተቀበልቅ ፈተናዋንም ተቀበል።

:እየሳቀ ሀጢአት የሰራ እያለቀሰ ጀሀነም ይገባል።

:ለማወቅ ተቸገር ለማገኘት ጣር ከትልቅ ባህር ምርጥ አሳ ይገኛል።

;አጀማመርህን ካሳመርክ ከፊሉን ጨረስክ ማለት ነው።

:ለራበው ሰው ሁሉም ነገር ጣፋጭ ነው።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

Показано 20 последних публикаций.