ቻይና በዓለማችን ውድ የሚባለውን አዲስ ማዕድን አገኘች፡፡
የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና ቶሪየም የተሰኘውን ተፈላጊ ማዕድን ማግኘቷን አረጋግጣለች፡፡
አሁን ላይ የዓለም የሀይል ምንጭ ወደ ታዳሽ እና የከፋ የአካባቢ ብክለት የማያደርስ አማራጭ በመፈለግ ላይ ሲሆን የጸሀይ ሀይል፣ ከውሃ የሚመነጭ የሀይል አማራጭ እና የኑክሌር ሀይል ዋነኛ አማራጮች ናቸው፡፡
ዩራኒየም እና ቶሪየም ደግሞ ለኑክሌር ሀይል አማራጭ ዋነኛ ግብዓት ሲሆኑ ዩራኒየም ማዕድን እንደ ልብ አለመገኘት፣ ማዕድኑም በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት ብቻ መገኘቱ እጥረቱን ሲያባብሰው ቆይቷል።
ቻይና አገኘሁት ያለችው ቶሪየም ማዕድን አንድ ሚሊዮን ቶን መጠን አለው የተባለ ሲሆን፤ ሀገሪቱ የሀይል ፍላጎቷን ለ60 ሺህ ዓመታት እንድትሸፍን ይጠቅማታል ተብሏል፡፡ እንደ መንግስታዊው የሳውዝ ቻይና ፖስት ዘገባ ከሆነ ቶሪየም ማዕድኑ የተገኘው በደቡባዊ የሀገሪቱ አካባቢ ሞንጎሊያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ቶሪየም ማዕድን በተለይም የኑክሌር ሀይልን ለማመንጨት፣ ቴሌስኮፕ ሌንሶችን፣ ሴራሚክ፣ ካሜራዎችን እና ሌሎች ተፈላጊ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ለማምረት ይውላል ።
Via
@mussesolomon