ማ ስታወቂያ
ውድ የ2015 ትምህርት ዘመን ተፈታኞች በሙሉ:
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ተፈታኞች የሚከተሉትን ሶስት አማራጭ አድራሻዎችን ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡
• በዌብ ሳይት፡-
eaes.et • በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
• ቴሌግራም አድራሻ፡-
@eaesbotጥብቅ ማሳሰቢያ፡-
ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን እያሳወቅን በማመሳሰል ውጤት እንገልጻለን ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራስዎን ይጠብቁ። በተጨማሪም ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን ይወቁ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
አጠቃቀም
በዌብ ሳይት ለማየት
1.
eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ
በአጭር የጽሁፍ መልዕክት
6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር ) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በማላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ
በቴሌግራም ቦት
1.
@eaesbot ይፈልጉ
2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።