ነይ ነይ እምዬ ማርያም መዝሙሮች


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Музыка


♦️⛪️የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ⁉️
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት
⛪️ የንግስ መዝሙራት
🤲 የምስጋና  መዝሙራት
🙏 የንስሐ  መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @kingo08bot ላይ ትገኛላችሁ=

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Музыка
Статистика
Фильтр публикаций


🗓 #ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ጥር ፲፬ ፳፻፲፯ ዓ.ም
በቅድስት ቤተክርስቲያናችን
✅🔸🔹
አቡነ አረጋዊ (አመታዊ)
አባ ጳኩሚስ ፣ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ፣ አቡነ ተስፋ ጽዮን ፣ ሰማዕቱ አብሮኮሮስ ፣ አባ ዘሚካኤል ፣ ሙሴ ጸሊም


አክብረን እና አስበን እንውላለን

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊




በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የተዘጋጀ የደም ልገሳ መርሐግብር

በእለቱ ደም በመለገስ በቋሚነት አባል መሆን ከፈለጉ ፎረሙን በመሙላት ይመዝገቡ።
👇👇👇
https://forms.gle/3dK8tm6EKbZHNADy9

"ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ " ሮሜ 12:9


ጥምቀትን የጀመረዉ ማነዉ ?
Опрос
  •   አዳም
  •   አብርሃም
  •   ሙሴ
  •   መልስ የለም
1 голосов


ጥር ፲፪ ( ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል ፣ አሳዳጊዬ )
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!!

ሚካኤል “መኑ ከመ አምላክ ፤ ማን እንደ እግዚአብሔር” ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ወንጌላዊው ቅደስ ዮሐንስ በራእዩ “በእግዚአብሔር ፊት የቆሙ ሰባት መላእክትን አየሁ” ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል፣ ለእኛ ለሰዎች አማላጅ ሲሆን ለቅዱሳን፣ ፃድቃን ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው ነው፤ በሕይወታቸውናተ በተጋድሏቸውም እስከ መጨረሻው ይረዳቸዋል፡፡



እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


እሰይ ነጋ - ቅዱስ ኃያል፣ የድንግል ልጁ ልዑል እግዚአብሔር ክበር ተመስገንልን።
በፍቅር ዋሉ ክርስቲያኖች

➕ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቁ ምክንያት ጥምቀትን በእርሱ ጥምቀት ባርኮ ሰጠን።
➕ክርስቶስ የተጠመቀበት የዮርዳኖስ ወንዝ
መለኮታዊውን ብርሃን ለበሰ። በእርሱ ጥምቀት ወንዞች ፣ ጅረቶች ፣ ምንጮች ፣ ሁሉ ተቀደሱ።
➕መድኅናችን ሆይ በአንተ ጥምቀት የውኃ ምንጮች ሁሉ ተቀደሱ ፤ ስለዚህም ውኃ የመንፈሳውያን ልጆች መገኛ ማኅፀን ሆነች።
#ቅዱስ_ኤፍሬም 

 

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን ፣
መልካም በዓል🙏






Репост из: NIB DECOR 💥
💐ንብ ዲኮር 💐
ለሰርግ
ለብራይዳል
ለመልስ
ለቤቢ ሻወር
ለልደት
ለምርቃት እንዲሁም ለተለያዩ ፕሮግራም ዲኮር እንሰራለን
ያናግሩን @pilupadier
በስልክ መስመር 0927334801
0717273301
ለመቀላቀል👇👇

https://t.me/nib_decor




#ደጅሽ_ላይ_ቆሜ

ደጅሽ ላይ ቆሜ ስለምንሽ
ባርኪኝ እናቴ ማርያም ስልሽ
ተደላደለልኝ ህይወቴ
ባንቺ በእናቴ በእመቤቴ

አንቺ በመሆንሽ የህይወቴ ፋና አልፈራም ጨለማ ብርሃን አለኝና
አይጠፋም ዘላለም ስምሽ ከአንደበቴ
አለ በደሜ ውስጥ ፍቅርሽ በህይወቴ
አልቀርም ደጅሽ ለዘለዓለም/2/
ካንቺ ሚለየኝ ማንም የለም/2/
አዝ ======
እጅግ የተከፋ ደካማ ሰው አለ
መቅደስሽ የቆመ አማልጂኝ እያለ
ይቁም ይሄ ልጅሽ ሃዘን የሰበረው
ካንቺ በቀር ወገን መጠጊያ የሌለው
ያንሳው ኪዳንሽ ከውድቀቱ/2/
ያርግ በእጆችሽ ያ ጸሎቱ/2/
አዝ =====
ጽልመት የለበሰ ፈታኝ አደከመኝ
የምቋቋምበት ጉልበት አስፈለገኝ በርትቼ እንድፀና ሳትጎዳ ነፍሴ
ሁኚኝ እናቴ ሆይ ግርማዬ ሞገሴ
ልፅና ደግፊኝ እመቤቴ/2/
ይውለቅ ከእጄ ላይ ሰንሰለቴ/2/
አዝ ======
አበው የለበሱሽ የክብራቸው ካባ
መዓዛሽ የሚስብ የሮማን አበባ
ለውጪው እናቴ የህይወቴን ቃና
ባዶ ጋኔን ምልጃሽ ወይን ያስሞላውና
አፅጂልኝ በእጅሽ ማድጋዬን/2/
በወይን አስሞዪው እንስራዬን/2/

ሊ/መ/ቀ ምንዳዬ ብርሃኑ


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


#ብፅዕት_ነሽ

ከእግዚአብሔር ተልኮ የነገረሽን ቃል
አምነሽ የተቀበልሽ ብፅዕት ነሽ ድንግል (2)

በገሊላ ሳለሽ በናዝሬት ከተማ
ከመላዕክት ዓለም ከሰማይ ከራማ
ብርሃናዊው መልአክ ተሸክሞ ዜና
ደስታን አበሰረሽ በታላቅ ትህትና

እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል

ሰላም ለኪ ማርያም ድንግል ሆይ አትፍሪ
መዓዛሽን ወዷል እግዚአብሔር ፈጣሪ
ሞገስ አግኝተሻል በቅድመ  ሥላሴ
ክብርን የተመላሽ ምልዒተ ውዳሴ

እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል

ትወልጂያለሽ ጌታን በመንፈስ ቅዱስ
ትጠሪያለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ
በያዕቆብ ወገን ይነግሣል ዘላለም
ለመንግስቱ ሽረት ፍጻሜ የለውም

እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል

ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ሳትወልድ የኖረች
በእርጅና ዘመኗ ወንድ ልጅ ጸነሰች
እያለ ሲነግርሽ የሰማዩ ምስጢር
ይሁንልኝ ብለሽ ተቀበልሽ በክብር

እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊




• ሥላሴ ማለት ሦስትነትን የሚገልፅ ቃል ነው፡፡

የእግሊዝኛውም መዝገበ ቃላት(Trinity)ይለዋል ይህም
ሦስትነትን የሚያሳይ ቃል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ምሥጢረ
ሥላሴ በዘመነ ብሉይ ግልጽ አልነበረም ነገር ግን ብዙ
ማስረጃዎች ነበሩ በአዲስ ኪዳን ግን ግልጽ ሆኗል፡፡
• ሥላሴ ‹‹‹አንድም››› ‹‹‹ሦስትም››› ናቸው፡፡

*የሥላሴ አንድነት*

• በሥልጣን
• በመለኮት
• ዓለምን በመፍጠር
• በአነዋወር(በአኗኗር)
• በአገዛዝ
• በሕልውና
• በማሰብና በመናገር ፍፁም አንድ ናቸው፡፡

የሥላሴ ማለትም
የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያቸው

‹‹እግዚአብሔር›› ይባላል፡‹‹እግዚአብሔር›› የሚለው ቃል
የተገኘው፡

‹‹‹እግዚእ››› ‹‹‹አብ››› ‹‹‹ሔር››› ከሚለው ሦስት የግዕዝ
ቃላት ነው፡፡

‹‹‹እግዚእ››› ማለት (ኢየሱስ ክርስቶስ)

‹‹‹አብ››› ማለት (እግዚአብሔር አብ)

‹‹‹ሔር››› ማለት ደግሞ ጠባቂ፣ ቸር፣ ሩህሩህ (መንፈስ ቅዱስ) ማለት ነው፡፡

ይህም ማለት፡-

• አብ እግዚአብሔር ነው
• ወልድም እግዚአብሔር ነው
• መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ብሎ ተናግሮ ይህን ቃል ለአብ ብቻ ነው
ማለት በጣም ትልቅ ስህተት ነው ምክንያቱም ቃሉ የሦስቱም
ፍጹም አካላት የአንድነት መጠርያ ነውና! የብዙዎችም የውድቀት
መነሻም የእግዚአብሔርን ሥምና ትርጓሜን ያለማስተዋል
ነው፡፡

ለምሳሌ ዓለምን ሲፈጠር አብ ብቻውን አልፈጠረም
ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንጂ ማስረጃ፡- “በመጀመሪያ
እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ” ዘፍ 1÷1 በዚህ
አስተምህሮ ሥላሴ በአንድነት ዓለማትን እንደፈጠሩ
በግልፅ ታውቋል፡፡

*የሥላሴ ሦስትነት*

• በስም
• በአካልና
• በግብር (በሥራ)
***ሥላሴ በሥም ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አብ፣ ወልድ እና
መንፈስ ቅዱስ (ማቴ 28÷19)፡፡

*ሥላሴ በአካል ሦስት ናቸው*

• ለአብ የራሱ መልክ ,ገፅ እና አካል አለው፡፡
• ለወልድም የራሱ መልክ ,ገፅ እና አካል አለው፡፡
• ለመንፈስ ቅዱስም የራሱ መልክ ,ገፅ እና አካል አለው፡፡
አብ እና መንፈስ ቅዱስ ረቂቅ አካላት ሲኖሯቸው
የሚዳሰስስ እና የሚጨበጥ ግዙፍ አካል ያለው ግን ወልድ ብቻ ነው፡፡ ይህም በተዋህዶ ከድንግል ማርያም በነሣው ሥጋ ነው፡፡
በአካል አብ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን መሆን አይችልም! ወልድም አብና መንፈስ ቅዱስን መሆን አይችልም!
መንፈስ ቅዱስም አብና ወልድን መሆን አይችልም!
ሦስቱ አካላት በአካል ቅልቅል የለባቸውም! ነገር ግን ሦስት አካል
እንላለን እንጂ ሦስት አምላክ(መለኮት) አንልም!

አንድም ሦስት ስም እንላለን እንጂ ሦስት እግዚአብሔር አንልም!

*አብ*፡- አካላዊ *ልብ* ነው (የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ
*ልባቸው* ነው)

*ወልድ*፡- አካላዊ *ቃል* ነው(የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ
*ቃላቸው* ነው)

*መንፈስ ቅዱስ*፡– አካላዊ *እስትንፋስ* ነው(የአብ እና
የወልድ *ሕይወታቸው* ነው)፡

*ሥላሴ (በአብ) ልብነት ያስባሉ (በወልድ) ቃልነት ይናገራሉ
(በመንፈስ ቅዱስ) ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ፡፡

*ሥላሴ በግብር (በሥራ) ሦስት ናቸው*

+ አብ፡- አባት(ወላዲ አስራጺ) ነው፡፡ (ወልድን ይወልዳል
መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻል)

+ ወልድ፡- ልጅ(ተወላዲ) ነው፡፡ (ከአብ ይወለዳል)
+ መንፈስ ቅዱስ፡- ሰራጼ ሕይወት ነው፡፡ (ከአብ ይሰርጻል)

*ነገር ግን*

-አብ አባት ቢባል ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን በአኗኗርም
ሆነ በሥልጣን ፍፁም አይበልጣቸውም!

-ወልድም ልጅ ቢባል ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በአኗኗርም
ሆነ በሥልጣን ፍፁም አያንስም!

-መንፈስ ቅዱስም ከአብና ከወልድ ጋር በሥልጣንም
በአኗኗርም ፍፁም እኩል ነው!

*እንዲሁም*

-አብ ወልድን ስለወለደ እና መንፈስ ቅዱስን ስላሰረጸ ቅድምና የለውም!

-ወልድም ከአብ ተወለደ ስንል ፍፁም አብን መስሎና አብን አክሎ ተገኘ ማለት ነው!\

-መንፈስ ቅዱስም ከአብ ሰረጸ(ወጣ) ስንል ፍጹም አብን መስሎና አብን አክሎ ተገኘ ማለት ነው!

***አብ መቼ ወልድን እንደወለደ እና መንፈስ ቅዱስን እንዳሰረጸ
አይታወቅም!

ወልድ ከአብ መቼ እንደተወለደም አይታወቅም!

መንፈስ ቅዱስም ከአብ መቼ እንደሰረጸ አይታወቅም!

ወልድ ከአብ መቼ ተወለደ ብሎ መጠየቅ
እግዚአብሔር ከመቼ ጀምሮ ነው የነበረው ብሎ እንደመጠየቅ ይሆናል! ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ መቼ እንደተወለደ ቢታወቅ ኖሮ ፍጡር ነው የሚሉ ሰዎች ምክንያት ባገኙ ነበር፡፡ ልክ እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ ከአብ መቼ እንደሰረጸ አይታወቅም! መቼ
እንደሰረጸ ቢታወቅ ኖሮ መንፈስ ቅዱስ ፍጡር ነው የሚሉ
ሰዎች ለስህተታቸው ምክንያት ባገኙ ነበር፡፡

ምስጢረ ሥላሴም ረቂቅነቱም እዚህ ላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለአነዋወሩ ጥንት ፤ ለዘመኑም ፍጻሜ የለውም! ጥንት የነበረ ዐልፋ ፤
ለዘለዓለም የሚኖር ዖሜጋ አምላክ ነው ፡፡ መቼ ነበር ፤ እስከ መቼስ
ይኖራል አይባልም አይመረመርምም!

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

6.3k 1 105 1 63



በአብርሃም ቤት የተገኙ ቅድስት ሥላሴ በቤታችን በሕይወታችን ይግቡ 🙏❤️🙏




🕯ጥር ❼ 💓
።።።።።።።።።።


እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

5k 1 11 5 85



🗓 #ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ጥር ፯ ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን
✅🔸🔹
አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ (ዓመታዊ)
ስዕለተ ማርያም ፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ ፣ ቅድስት እኅተ ጴጥሮስ


አክብረን እና አስበን እንውላለን።

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊


ዘማቾች ይዘምቱበታል እርሱ ግን ተከታትሎ ይዘምትባቸዋል የተባለለት ማነው?
Опрос
  •   ይሳኮር
  •   ሮቤል
  •   ይሁዳ
  •   ጋድ
25 голосов




#ቸሪቱ_አማላጅቱ_ሆይ

ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በሥላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2)

ተጥሎ አዝኖ የኖረው
በልጅሽ ነው ቀናቀና ያለው
ንጉሱን ስትወልጂ በበረት
ተፈታ አዳም ከእስራት
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ

ከሚያስብ ከማይዘነጋ
ፍጥረቱን ከሚያረጋጋ
ስላለሽ በእግዚአብሔር ቀኝ
ለኃጥአን ድንግል ለምኝ
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ

ከሰማይ ሰማያት ወርዶ
መለኮት ሥጋን ተዋህዶ
አየነው በጠባብ ደረት
ወሰንሽው በአጭር ቁመት
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ

ሰነድ ነሽ መታረቂያችን
ከተማም መማፀኛችን
በሰማይ በምድርም ያሉ
ለክብርሽ ቅኔ ይቀኛሉ
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇


@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏


🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊

8k 1 107 1 102
Показано 20 последних публикаций.