ነበልባለቹ በጠላት ምሽግ ታሪክ ሰሩ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር የነበልባል ብርጌድ በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠና
የአገዛዙ 84ኛ ክ/ጦር እስካሁን 726 የግልና የብዱን መሳርያ ያጣው በአዲስ የመጣው አመራር በአንድ ወር የሄዱትን መሳርያ አስመልሳለሁኝ በማለት የለሊት ኦፕሬሽን ከጀመረ ሰነባብቷል ።
ይህም ህልሙ አልሳካ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ተጨማሪ 17 መሳርያዎች እስካሁን ወደ ፋኖ ገቢ ሆነውበታል። አገዛዙ በርካታ ሙትና ቁስለኛ እየሸከፈ ወደ ከተማ መፈርጠጥ የቀን ተቀን መደበኛ ስራው ሆኗል።
በአዲሱ ዘዴው የለሊት ኦፕሬሽን የሚያደርገው የአገዛዙ ሰራዊት ተከትሎ ተናዳፊዎቹ የነበልባል ብርጌድ አዲስ አካሄድ ጀምሯል።
እንሆ ዛሬ 01/08/2017 ዓ.ም የአገዛዙ ሰራዊት እንደተለመደው ኬላ ወደሚዘረጋበት እና ቀን ደፈጣ ወደሚይዝበት የተለመደ ምሽጉ ከባልጪ ወደ በሳ መስመር ወርካ ከጠዋቱ 2:00 አካባቢ ኬላ ለመዘርጋት እና በኬላ የተለመደ ዘረፋውን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ በ50 አለቃ ሰለሞን አድነው የሚመራው ሻለቃ 3 ሻንበል 3 ቀድመው የጠላትን ምሽግ ይዘው ሲጠባበቁ የቆዩት ተርቦቹ የሺ አለቃ ሶስት ፋኖች አንግጦ ወደ ምሽግ የሚመጣውን ልብልብ የአገዛዙን ሰራዊት በገዛ ምሽጉ የመሸጉት የነበልባል አናብስቶች 12 ሆኖ ኬላ ጥበቃ የመጣውን አራዊት ሰራዊት በከፈቱበት ቅፅፈታዊ ተኩስ ስድስቱን ግንባር ግንባራቸውን በቀይ ጥይት ነቅሰው እስከወዲያኛው ከምድር ቆይታቸው ያሠናበቷቸው ሲሆን ስድስቱ እግሬ አውጭኝ በማለት እየፈረጠጡ ባልጪ ከተማ ገብተዋል ።
ነበልባሎቹም በሚገባ ግዳጃቸውን ፈፅመው ወደ ነፃ ቀጠናቸው በሰላም ተመልሰዋል።
በተያያዘ ዜና አገዛዙ አሁንም እዬፈራረሰ ሲገኝ ሶስት የአገዛዙ ሰራዊቶች አገዛዙን በመፀዬፍ የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር ነበልባል ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
አዲስ ትውልድ
አዲስ ተስፋ።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማእታት
ከአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር ነበልባል ብርጌድ ሚድያ ክፍል።
ሚያዚያ 1/8/2017ዓ.ም
ነበልባሎቹ።
ድል ለአማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ፋኖ
ንሥር ብሮድካስት መረጃ
ረቡዕ ሚያዚያ 01 ቀን 2017 ዓ.ም
=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! በጋራ ትግል፡ የጋራ ድል !
ዩቱብ:
https://www.youtube.com/@nibcnews-EthiopiaFacebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=61574918731906ትዊተር:
x.com/nisirinternati1 ቴሌግራም:
https://t.me/nisirbroadcastingቲክታክ:-
https://www.tiktok.com/@nisirbroadcast?
_t=ZP-8vDbj8Rmftu&_r=1
WhatsApp: +1 (252) 574‑6084
Telegram: +1 (252) 574‑6084pp