"የአድዋ ድል ያለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጎዶሎ/ባዶ ነው"
"አድዋ ያለ ንጉሰ ነገስት ምኒልክ ባዶ ተራራ ነው"
በመሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ
ጥቂቷን እንጨልፍ
የካቲት 22 ለየካቲት 23 አጥቢያ የእግዚአብሔር መልአክ በአውአሎም አድሮ ጠላት ከምሽጉ እንዲወጣ ስላደረገ ጠላት ከምሽጉ መጥቶ ሌሊት ሲጓዝ አድሮ ዐድዋ እንደሚገባ በመረጋገጡ ቅዳሴው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ እንዲፈፀም ተወሰነ፡፡
ይህንንም ኢጣልያኑ ኩንቲ ሩሲኒ የተባለው ታሪክ ጸሐፊ እንደሚከተለው ዘግቦታል፡፡ “ከልዩልዩ ምንጭ እንዳገኘሁት ፣ ከሐበሾችም ጽሑፍ እንደተረዳሁት፣ ጦርነቱ ሲጀመር አፄ ምኒሊክ፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ ራስ መኮንን፣ ራስ መንገሻ አቲከም፣ ፊታውራሪ ገበየሁ፣ ሌሎችም ብዙ አለቆች ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምረው ዐድዋ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያ ያስቀድሱ ነበር፡፡”
ቀዳሹም አቡነ ማቴዎስ ነበሩ፡፡ እርሳቸውም በሚቀድሱበት ግዜክፍት በሆነ በር በኩል የጦርነቱ ተኩስ ወደደ ውስጥ እየገባ ተሰማ፡፡ ወዲያው ቃፊሮች መጥተው የኢጣልያን ጦር መድረሱን ተናገሩ፡፡
በዚህ ግዜም አፄ ሚኒልክ የድንጋጤም የመበርገግም መልክ አልታየባቸውም ፡፡ በጸጥታ ቆመው ጥቂት ደቂቃ እንደቆዩ ወደ አቡነ ማቴዎስ ጠጋ ብለው ትንሽ ንግግር ከተለዋወጡ በኋላ ተመልሰው እስፍራቸው ቆሙ፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ማቴዎስ በቀኝ እጃቸው መስቀላቸውን ከፍ አድርገው ይዘው በዚያ ላሉት ሁሉ እንደዚህ ብለው አስተዛዝነው ለቅሶ ጭምር ተናገሩ፡፡
“ልጆቼ ሆይ! ዛሬ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሚፈጸምበት ቀን ነው፡፡ ኺዱ ለሃይማኖታችሁ ለሀገራችሁ ሙቱ፣ እግዚአብሔር ይፍታሕ” አሉ፡፡
አቡኑ ይኸን ተናግረው ሲጨርሱ መኳንንቱ ሁሉ እየተሸቀዳደደሙ የአቡኑን መስቀል ተሳልመው ወጡ፡፡ እያንዳንዱ በችኮላ ወደየሰፈሩ ኼዶ በሰፈርም የነበረው የጦርነቱን መጀመር ሰምቶ ዝግጅት በማድረግ ወደ ጦሩ ግምባር ተጓዘ፡፡፡ ዕለቱ ጊዮርጊስ ስለነበር አፄ ምኒልክ አቡነ ማቴዎስ ወደ ማይጓጓ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ኼደው ስብሐተ ፍቁር እያደረሰ ሳለ አንድ ፈረሰኛ በድጋሚ ደርሶ ጠላት መምጣቱን ለአፄ ምኒሊክ ነገራቸው ፡፡ ወዲያው አፄ ምኒሊክ ገና ማይጓጓ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እያሉ ጦርነቱ ተጀምሮ የመጀመሪያው የአበሻ ጥይት ተኩስ በሚሰማበት ጊዜ አፄ ምኒሊክ ለእግዚአብሔር ልባዊ የሆነ ጸሎታቸውን በማድረስ ለጦራቸው ድልን ተመኝተዋል፡፡ ከዚያም ገስግሰው ወደጦርነቱ ግምባር ኼዱ፤ ግርማዊት እቴጌ ጣይቱም የእቴጌነት ክብራቸውን ዝቅ አድረው ፊታቸውን ተገልጠው በጾም በጸሎትና በልቅሶ አምላካቸው ኢትዮጵያንና ዘማቾቹን እንዲረዳ በመረረ ኀዘን አቤቱታ ያቀርቡ ነበር፡፡
....................................
ለወዳጅህ ሼር አድርገው🙏🙏🙏
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot