TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀

7 May 2019, 10:41

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

​​የቀጠለ ነው። share

እርግጥ ይህንን ምክንያቶች ለመከራከሪያ ከሚጠቀሙት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የፕሮቴስታንት ምሁሮች ውስጥ :-

📚Reformed Theologian Evangelist Dr. Ian Paisley ። 📚 Pro. Norman Geisler ( A Popular
Survey of theOld Testament. p= 15-17)።📚 Christian Apologetic and Research Ministry. በዋናነት ይጠቀሳሉ። ይህንን መልካም የሆነ የመጽሐፍ
ቅዱስ ምንጭ እና የቀኖና አፈጣጠር ( Formation of Canon) በተለይ ወንድም ናቲ ባወቀው እና በተረዳው፡ እና ያገኛቸውን ማስረጃ በመጠቀም የተቻለውን ያህል ለመግለጽ ያደረገውን ጥረት ሳላደንቅ አላልፍም። አሳዛኙ ነገር ይህንን እጅግ ጥንቃቄ የሚሻውን ርዕስ ከአንድ ወገን ብቻ ባገኘው መረጃ ላይ ተንተርሶ 81ዱን የኦርቶዶክስ መጽሐፍ ቅዱስ የተቸበት መንገድ ጥንቃቄ የጎደለው እና በአድሎ የተሞላ አስመስሎበታል።

በፕሮቴስታንቱ መጽሐፍ ቅዱስ የሌሉትን መጻሕፍቶች ሲተች አንዱ የስጠው ምክንያት ከ66ቱ ውጪ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸው 15ቱ መጻሕፍቶች
አይሁዶች ባህላቸውን እንዳይረሱ የተጻፉ እንጂ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ የሚወሰዱ መጽሐፍቶች አይደሉም በማለት ይናገራል ።


ነገር ግን የትኞቹ መጻሕፍቶች የአይሁድ ባህል እንደሆኑ ምዕራፍ እና ቁጥሩን አልጠቀሰልንም?

⚪ ሲጀመር መጻሕፍቶቹ ከባህል ጋር የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም።

⚪ መጽሐፈ ሔኖክ እና ዕዝራ ስቱኤል የትንቢት መጽሐፍ ( Prophetical Apocalypse) ናቸው

⚪ ተረፈ ምናሴ የንስሐ ጸሎት መልዕክት ነው

⚪ መጽሐፍ ሲራክ የዜና መዋዕልን የአጻጻፍ መርህ ተከትሎ ከትንቢተ ዳንኤል በስተቀር ሁሉንም የብሉይ መጽሐፍ ጠቅሶ የጻፈ ነው

⚪ መጽሐፈ ኩፋሌ ከፍጥረት ታሪክ ተከፍሎ የቀረውን የሚዘረዝር ትንሹ ዘፍጥረት (The Little Genesis) የሚባለው መጽሐፍ ነው

⚪ ጦቢት፤ ዮዲት፤ ተረፈ ኤርሚያስ፤ የታሪክ መጽሐፍ ናቸው

⚪ መቃቢያን አይሁዶች የአባቶቻቸውን እምነት ይሁዲነትን ( Judaism) ከሔለናውያን የግሪክ የፍልስፍና አስተምሮ እና የጣኦት ልማድ ለመጠበቅ ተጋድሎ ያደርጉበት ( Faith Building እምነትን የሚገነባ መጽሐፍ ነው) ቅዱስ ጳውሎስ እንኳን ጠቅሶ ያስተማረበት መጽሐፍ ነው። ዕብ=11:35 ፡፩ኛ መቃቢያን= 3 እንደተገለጸው። በከንቱ አንዳችን የአንዳችንን ስም ለማጥፋት ጥረት ባናደርግመልካም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ነገረ መለኮትን ህግጋተ እግዚ አብሔርን፡ ሥርዓተ አምልኮትን እና ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ምግባራትን የመሳሰሉትን የምንማርበት እንጂ የአይሁድን ባህል የምናጠናበት መጽሐፍ አይደለም። የራሳችን ባህል እያለን የአይሁድ ባህልን በአምልኮ መጻሕፍቶቻን ውስጥ የምናካትትበት ጠቀሚታው ምንድነው? ይህ ውሃ የማያነሳ እና በበጎ አስተሳሰብ ተቀባይነት የሌለው ( irrational or illogical) ምክንያት እንዴት ሌሎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሊገባኝ አልቻለም?

የኦርቶዶክስ እና የካቶሊኮች የጥንቶቹ ቤተ ክርስቲያናት ለምን የአይሁዶችን ቀኖና እንዳልተቀበሉ ምክንያቱን
ሊነግረን አልቻለም? ለማወቅም ምንም ጥረት እንዳላደረገ ከንግግሩ መረዳት ይቻላል።

ልክ እንደ ሐገራችን የብሽሽቅ ፖለቲካ ስሜታዊነት የተሞላበት እከሌ እኛን ስለሚተቸን ብድር መመለስ አለብን አይነት የፌስ ቡክ ብሽሽቅ ጥንቃቄ ሊደርግበት እንደሚገባ እንኳን ከግምት ውስጥ አለማስገባታቸው ክርስቲያናዊ
ጥንቃቄ አለማድረጋችሁ ያሳዝናል?

በዚህ ስሜታዊ መነቃቃት የሚደረግ አግባብነት የሌለው እና በቂ ጥናት ያልተደረገበት ትችት አላስፈላጊ ስድድብ ውስጥ ከማስገባት በቀር ማንን ያንጻል?

ንባቡ እና አውደ ንባቡ ሳይጠና ፡ መጻሕፍቶቹ በጥልቀት ሳይነበቡ( Textual, Contextual and Historical study) ሳይጠኑ እንዴት መተቸት ይቻላል?

የዚህ ጽሑፍ ዓላም ፕሮቴስታንቶች 15ቱን የኦርቶዶክስ መጻሕፍት ቅዱሳት ላለ መቀበል ያቀረቡትን ምክንያት በጥልቀት መመርመር እና ብዥታን አጥርቶ በማሳየት እውነቱን መግለጽ ነው።

🌟 ፍርዱን ለአንባቢው እተወዋለሁ
🌟 ይህ የመግቢያ የክፍል አንድ ጽሑፌ ይሆናል
🌟 በፕሮቴስታንቶች አመለካከት መጽሐፍ ቅዱስ ተቀባይነት የሚገባው( Authoritative) እምነት የሚጣልበት ( Reliability ) እና እውነተኛ( Authenticity) መሆኑ
የሚታወቀው የሚከተሉትን መስፈርት ቀኖና
( Measure of Standard ) ሲያሟላ ነው።

⭐ 1ኛ= የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ባለአደራ ጠባቂ ( Custodians) የሆኑት አይሁዶች የተቀበሏቸው መጻሕፍት መሆን አለባቸ ጠባቂ በኦርቶዶክስ መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱትን 15ቱ መጻሕፍቶች በመለኮት ምሪት( Divinely inspired) ስላልተጻፉ አይሁዶች አልተቀበሏቸውም ስለዚህ እኛም አንቀበላቸውም

⭐ 2ኛ= ኢየሱስ እና የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ሐዋሪያቶች ጠቅሰው (Citatioጠቅሰው Quotation ) ያስተማሯቸው ወይም በተዘዋዋሪ ሃሳቡን የሚገልጽ ቃላት ( Allusion ) ሆነው መገኘት አለባቸው። ከእነዚህ 15ቱ የኦርቶዶክስ መጻሕፍት አንድ እንኳን ጥቅስ( Citation) ወይም ሐሳቡን በተዘዋዋሪ የሚገልጽ ነገር( Allusion) ኢየሱስ እና የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ሐዋሪያቶች አለመጥቀሳቸው ?

⭐3ኛ= ከፕሮቴስታንት ከእምነት የመዳን ትምህርት ጋር ( doctrine of soteriology) አብሮ አይሄድም፤ ለሙታን ጸልዩ ይላል፤ መዳን ምጽዋት በመስጠት ነው ይላል ስለዚህ አንቀበለውም።

⭐4ኛ= የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቀምባቸው ከ66ቱ ውጪ ያለው
15ቱ መጽሐፍ ጥንቆላ ያበረታታል። አጋንንት በኢየሱስ ስም እንጂ መጽሐፈ ጦቢት እንደገለጸው የአሣ ጉበት በመብላት አይወጣም። ስለዚህ እንዲህ ያለውን
አስተምሮ አንቀበልም።

⭐ 5ኛ= እንደ አባ ጀሮም፤ አርጌንስ፤ አትናትዮስ፤ አሬኖዮስ፤ የሰርዴሱ ሚላጦን
ወዘተ የመሳሰሉት የጥንት የቤተ ክርስቲያን አባቶች ከ66ቱ ውጪ የተጠቀሱትን
የኦርቶዶክስ መጻሕፍት አልተቀበሏቸውም፤ ከእነዚህ መጻሕፍት ጠቅሰውም
አላስተማሩም። ስለዚህ እኛ ፕሮቴስታንቶች አንቀበላቸውም።

⭐ 6ኛ= እነዚህ ከ 66ቱ ውጪ የተጠቀሱት የኦርቶዶክስ 15ቱ መጻሕፍት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ( Thus says the Lord ) ወይም ተብሎ ተጽፎአል ( As it was written ) ወይም በዚህ መጽሐፍ እንደተባለው የሚሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ( The Scripture says) ቃሎች የማይገኙበት ስለሆነ እንደ
ቅዱስ መጽሐፍ አንቀበለውም።

🔅 እግዚአብሔር ቢወድ ቢፈቅድ በህይወትም ብኖር እነዚህን ያነሷቸውን ጥያቄዎች እና ሌሎቹንም ሁሉ እንዲሁ በሚገባ መልኩ ሁላችንም ፕሮቴስታንቶችም፤ ኦርቶዶክሳውያንም እንማማርበት ዘንድ አዘጋጀዋለሁ።

🔆 ጥያቄዎቹ መልስ ከተሰጠባቸው በኋላ
- የመጽሐፍ ቅዱስ የቀኖና አፈጣጠርን?
- መቼ ስም ተሰጣቸው?
- ምዕራፍ እና ቁጥር መቼ ተሰጣቸው?
- ለምን የሚሉትን ? እንመለከታለን ጌታ በፈቀደ መጠን። አስጀምሮ እንዲያስጨርሰኝ ጸሎታችሁ አይለየኝ። የማልጠቅም ባሪያው ተስፋዬ

ይቀጥላል....

Tesfaye GB ( ክንፈ ሚካኤል)
መጋቢት 19/2011, Mar 28/2019

@orthodoxzelalemawit
@vitiz1bot ለጥያቄ እና አብሮ ለመሥራት ለሚፈልግ

Share share በማረግ ይተባበሩን

1.9k 0 26
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot