ይድረስ ለእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ★
★ እናንተ ቤት የምትለኩሱትን እሳት እንዴት ታዩታላቹ ?
★ሼር በማድረግ አድርሷቸው ★
ሰሞኑን በቲክቶክ ፕላቶ ፎርም በእስልምናና በክርስትና መጻሕፍት ዙሪያ በሚወያዩ ወጣቶች የተነሱ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ ከሙስሊም ወገኖች ለምን ተጠየቅን በሚል ግልፍተኝነት ጉዳዩን ከቲክቶክ ወደ ተቋማዊ ጉዳይ ከፍ አድርገውታል እኛ ዝምያልነው የቲክቶክ ጉዳይ ነው ብለን ነበር።እናንተ በተቋም ደረጃ ካመጣችሁት እኛም ጥያቄ አለን።
አንዳንድ ኢስላም ወንድሞችና ኡዝታዞች ክርስትናን በኢስላሞች ዘንድ የተጠላ ለማድረግ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖችን ወደ እስልምና ለመውሰድ በርካታ ክብረ ነክ መፅሐፍትን ጽፈዋል፣ እየፃፉም ይገኛሉ።
ክርስትናን ከእስልምና እያነጻፀሩ እጅግ በሚያስነውር መልኩ ከሚጽፉትና የክርስቶስን አምላክነት ከሚፃረሩት መካከል ቀዳሚዎቹ ቀመር ሁሴንና ኡዝታዝ አቡ ሃይደር ይጠቀሳሉ። አቡ ሃይደር "ላለመደናገር ማመሳከር" በሚል መጽሐፉ ክርስትናን በማጥላላት፣ ክርስቶስን ፍጡር በማድረግ ነውረኛ ጽሑፍ ፅፏል። በየዩቲዩብ የሚናገረው ፀባ ጫሪ ንግግሩና ደም አፋሳሽ የሽብር መልዕክቱ በስፋት ተሰራጭቷል።
ሸይኽ ሐሰን ታጁ "ሰይፉን ፍለጋ" እና "የኀመረ-ኖህ ቅጥፈት በእስልምና እውነት" የሚሉ ድርሰቶችን በመፃፍ በክርስትናውና እስልምናው መካከል ልዩነቶች እንዲሰፉና መከባበር እንዲያከትምለት የድርሻውን አበርክቷል። አሁንም ድረስ ለስሙ አምባሳደር ተብሎ ተቀምጦ ከፍተኛ የሽብር ተግባራትን ውስጥ ለውስጥ እንደሚሰራ ተደርሶበታል።የመንግስትን ፓሊስ ከማስፈጸምና ሃገራዊ ሥራዎችን ከመሥራት ይልቅ ጽንፈኝነት በማባባስና የሽብር ወላፈን በማቀጣጠል የተጠመደ መሰሪ ሰው በመሆኑ መንግሥት እርምጃ ውሳኔ ሊያስተላልፍበት ይገባል።
ዶ/ር እንድሪስ የተባለ ሰውም የቁራኑ ኢሳና የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የተለያዩ ቢሆኑም "ኢየሱስ የኢስላም ነቢይ" የሚል ክብረ ነክ መፅሀፍ አሳትሞ አሰራጭቷል። በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል ከፍተኛ ፀብ፣ጥላቻ፣አምቧጓሮ እንዲፈጠር አድርጓል።
አሁን ላይ በክርስቲያኖችና ኢስላሞች መካከል ሰፋፊ የመለያያ አጥሮች በማስቀመጥና ከፍተኛ የጥላቻ መርዝ በመርጨት የሚታወቀው አህመዲን ጀበልም "303 ጥያቄዎች ለክርስቲያኖች" የሚል ድርሰት ፅፎ ተገቢው መልስ ተሰጥቶታል። ዋሂድ እና ኤልያህ እንዲሁም ሰልማን የተባሉ አክቲቪስቶችም የየራሳቸውን መጽሐፍ ፃፉ ርካሽ የሆኑ ቃላትን በመጠቀም ከፍተኛ ደም አፋሳሽ ቅስቀሳዎችን አደረጉ ።
እኒህ ከላይ የጠቀስናቸው ግለሰቦችና መጻሕፍት ክርስትናን ለማጥላላት፣ክርስቲያኖች ላይ ግድያ ለማምጣት የተጻፉና የሰበኩ ናቸው። በስብከት ደረጃ ደግሞ እጅግ ብዙ ኡዝታዞችንና አክቲቪስቶችን መጠቃቀስ ይቻላል። ለዓመታት ደም ደም የሚል ንግግሮችንና ፀባ ጫሪ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ክርስቲያኖች በመጽሐፍትም በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችም ለተነሱ ጥያቄዎች በራሳቸው ድንበር ላይ ሆነው በቂ ምላሽና ማብራሪያ ከመስጠት በስተቀር እስልምናን የሚነካ አንዳች ነገር አልተናገሩም።
አክራሪዎች የፃፏቸው መጽሐፍትም ሆኑ ድርሰቶች በሙስሊሞችና በሌላው እምነት ዙሪያ ያስገኙት ጥቅም የለም። ይልቁንም የመለያያ ድልድይ ሰሩ እንጂ። በሁለቱም ዘንድ የነበረው ጥላቻ እጅግ እንዲያይል እና ሁሉም ራሱን ከመከላከል ወጥቶ ወደ ማጥቃት እንዲሸጋገር በር ከፍቷል።
አክራሪ ፀሐፍት ያስገኙት ጥቅም ቢኖር ክርስቲያኖች እምነታቸው ላይ እንዲጣበቁና እንዲያውቁ ብቻ ነው። ሃይማኖት ለማስለወጥ የተፃፉ የጥላቻ መጽሐፍት ሃይማኖትን አጥብቆ የሚይዝ ወጣት እንዲፈጠር፣ ሞጋችና ሌላውን ጠያቂ ክርስቲያን እንዲበዛ አድርገዋል።
የራሳቸውን እምነት በቅጡ ተርጉመው ያላስተማሩ አክራሪያን የማያውቁትንና በአግባቡ ያልተረዱትን መጽሐፍ ቅዱስ ሚሊየን ጊዜ ለማብራራት ሞክረው አልተሳካላቸውም። ክርስትናን ለቆ ኢስላም የሆነም በታሪክ አጋጣሚ አላገኙም።በገንዘብ እየተደለሉ ኑሮን ለማሸነፍ ሃይማኖቴን ለወጥኩ የሚሉት እነርሱ የድራማ ተዋናዮች ስለሆኑ በንቀት እናልፈዋለን።
አሁን ለፈተፈቱት ጉዳይ በልካቸው እየተሰፈረ ሲመለስላቸው እሪታና ዋይታ፣ ሰላማዊ ሰልፍና ዛቻ ጀመሩ። ምን ጠብቀው ኖሯል? ድሮ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ! ድንበር ዘለልነት የመጨረሻ ጣጣው ይህ ነው።
ሙስሊሞች አንድ እውነት ተረዱ ዘመኑ የዕውቀትና የመረጃ ዘመን ነው ወጣቱ ትውልድ ቁርዐኑንም ሆነ ሐዲሳቱን በሚገባው ቋንቋ እየተረጎመ መመርምር የሚችልበት ዘመን ላይ ነው ያለነው።ከራሳቹ መጽሐፍ ለምትጠየቁት ጥያቂ በቂና አሳማኝ መልስ መስጠት እንጂ ኡኡኡ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው የሜዳ ላይ ጩኸት ጥያቄዎችን አያሳቆምም ትውልዱ ከእንግዲህ በአረብኛ ብቻ የተጻፈ ጽሑፍ አይቶ አሜን ብሎ አይቀመጥም በየቋንቋው ስለተተረጎሙ እያንዳንዱን መጽሐፍት እያራገፈ መጠየቁን ይቀጥላል።አንድ ግለሰብ ላይ ስትዘምቱ ሺዎች ተፈጥረው እንደሚያድሩ ዕወቁ።
ሼርና ታግ አድርጉላቸው
#followers
#highlight
👉 ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo