"እረዳሻለው"
ዘማሪት አስቴር አበበ
ውጪ ብሎ አስወጥቶኝ ከኖርኩበት ቀዬ ሰፈር
ሊሰራብኝ ገንዘብ ሊያደርገኝ ለእርሱ ስራ ለእርሱ ክብር
ከዳር ማድረስ ሳይችል ቀርቶ ጥሎኝ አይሄድ በበረሃ
ያመንኩትን አውቀዋለው አይቼዋለሁኝ ትላንትና
አይቼዋለሁኝ ትናንትና አይቼዋለሁኝ ትናንትና
ለነገም አመንኩት ልቤ በእርሱ ፀና
አይቼዋለሁኝ ትናንትና አይቼዋለሁኝ ትናንትና
ለነገም አመንኩት ልቤ በእርሱ ፀና
ልቤ እርሱ ጋር ፀና
ልቤ እርሱ ጋር ፀና
ትናንት ሲደግፈኝ አይቻለሁና
ልቤ እርሱ ጋር ፀና
ያለኝ እውነት ሆኖ እያለ
መልካምነቱንም ፍጥረት እያወቀ
እንደተረሳሁ እንደተወኝ
እንደማያየኝ እንደጣለኝ
ያ ክፉ ጠላቴ ብዙ ብዙ ዋሽቶኛል
እውነታውን ግን ቃሉ ነግሮኛል
እረዳሻለው አግዝሻለው
በጸናች ክንዴ ደግፍሻለው
ልብሽ ቤቴ ነው የኔ የአንቺ ነው
ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ጥልቅ ነው
ሁኔታ የሚለው ሌላ ሌላ ነው
ቃሉ ያለኝ ግን አይዞሽ ነው
ሁኔታ የሚለው ሌላ ሌላ ነው
ቃሉ ያለኝ ግን በርቺ ነው
እረዳሻለው....
ጠላቴ ያለው ሁሉ ውሸት ነው
ጌታ ያለኝ ግን እውነት ነው
ጠላቴ ያለው ሁሉ ውሸት ነው
ቃሉ ያለኝ ግን እውነት ነው
እቀጥላለው ገና ሄዳለው
እጁ ይዞኛል ምን እሆናለው
ብዙ ብዙ መልካም ነገር ብዙ ብዙ በጎ ነገር
ብዙ ብዙ ጥሩ ነገር ትላንቴ ላይ አድርጎልኛል
ብዙ ብዙ መልካም ነገር ብዙ ብዙ በጎ ነገር
ብዙ ብዙ ጥሩ ነገር ትላንቴ ላይ አድርጎልኛል
አመሰግነዋለው (8)
ቅኔዬ አልሻገተ ትውልድ አላለፈው
ገና በልጅነት በልቤ ያኖረው
ከአፉ በወጣው ቃል የተጻፈ ነገር
እርጅና አያውቀው ይህ ሰማይ ይናገር
አይቼዋለሁኝ...
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ
🎼🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 🎼🎼
@Protestantmezemur@Protestantmezemur─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───