ኢትዮ ግጥም እና ፍልስፍና ethio poem&philosophy


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Цитаты


የግጥም ተሰጥዖ ያላችሁ አድሚን እናደርጋችኋለን በቦቱ ተመዝገቡ ግጥም ብቻ ሳይሆን መነባንብ ሆነ ሌሎችም ተሰጥዖ ያለው መሳተፍ ይችላል
For any comment👉 @e_t_l_bot
Buy ads: https://telega.io/c/qdist

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Цитаты
Статистика
Фильтр публикаций


#እናቴ

ልንገርሽ እናቴ የሆዴን አውጥቼ
ሳርቅ ካጠገብሽ መቼም የሁን መቼ
ሁሌም በልቤ ዉስጥ ዙፋንሽን  ይዘሽ
ትኖሪያለሽ በልቤ ዉስጥ ለኔ ነግሰሽ።

የናትነት ፍቅርሽ መቼም ሳይለየኝ
አለ በልቤ ውስጥ ሁሌም ትዝ እንዳለኝ
ልጄ ብለሽ ስትጠሪኝ በጣፋጭ አንደበትሽ
ማረገውን ሳጣ ከደስታ ብዛትሽ
አያልቅም ተነግሮ እማ ያንች ውለታ
ቢዘከር ቢዘከር ሁሌ ጠዋት ማታ

ብትጨነቂ ለኔ ብትቆጭ  ለኔ
ምን ማርግ ....
ችላለው አያሳያኝ ያንችን ክፉ ለኔ

የአባቴ ምትኬ ነሽ የአምላኬ ስጦታ
ከሰማይ በታች ያለሽኝ መከታ

ለኔ ህይወት ስትኖሪ የአንችን  እረስተሽ ለኔ በፍቅር ብርሃን ብርሃኔን አብርተሽ
በይ እረፊ እንግዲ ልርዳሽ በተራዬ
ለሁሉም ቀን አለ አሁን ነው ፋንታዬ

ለውለታሽ ምላሽ የንሰኝል ቃል
ድንገት ዞር ስትይ እንካን ሳቅሽ ቁጣሽ ይናፍቃል
ክፉ አይንካብኝ እስከ ዘላለሜ
ካንች በፊት ያርገው ያንችን ክፉ ለኔ
ያላንች ባዶነው ሳስበው ህይወቴ
ክፉም ሆንክ ጥሩ ኑሪልኝሬናቴ።
    ጥሩ እና ለእናንተ ምንም መስዋትነት መክፈል ለሚችሉ እናቶች ይሁንላችሁ
መልካም ምሽት

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


ከእኔጋ ኦንላይን ስራ መስራት ምትፈልጉ ሊንኩን ነክታቹ ኑ ምንም አይነት ቅድሚያ ክፍያ የለውም ሰዎች like እንደ ቲክቶክ ነው appun አውርዳችሁ አናግሩኝ በቀን እስከ 50$ እነየሰሩ ነው trust me ሰዎች

ሴቶች ስትገቡ 3$ ይሰጣችዃል live መቀመጥ task መስራት ነው ስራው ዎንዶች agent ለመሆን ነው ዋና አላማችን ሴቶች የፈጠነ ስራውን ጀምሩት በዉነት ይለውጣችኋል


Appun አውርዱት👇👇

https://aaaonline.info/pF3NPw


ከእኔጋ ኦንላይን ስራ መስራት ምትፈልጉ ሊንኩን ነክታቹ ኑ ምንም አይነት ቅድሚያ ክፍያ የለውም ሰዎች like እንደ ቲክቶክ ነው appun አውርዳችሁ አናግሩኝ በቀን እስከ 50$ እነሰሩ ነው trust me ሰዎች

Appun አውርዱት👇👇
https://aaaonline.info/pF3NPw

በዚህ አናግሩኝ @esttiff


#ሁላችን_ከንቱ_ነን

የልብ አማኝ ጠፍቶ የአፍ አማኝ ከበዛ
በእውነት አመንጭቶ ፍቅርን ካልገዛ
መማር ከየት ይምጣ ልብ ተቆልፎ
የሰው ልጅ ካልጣለ ማስመሰልን ገፎ

ባንደበቱ ጌታን በልቡ ገንዘብን
አፉ አሜን እያለ በውስጡ ተንኮልን
ምላስ አምላክ ጠርቶ
ልብን ገንዘብ ሞልቶ
የስም ፃድቅ ሰፍቶ
በነብይ ተሞልቶ
ምህረት ከየት ይምጣ
እንዴት ይብረድ ቁጣ!
ጠዋት ክርስቶስን
ከሰአት ሰይጣንን
በግፍ ተሸፍኖ ልባችን በቀልን
የተንኮል አሽክላ አስልተን እየጣልን
ማረን እንላለን እንዴትስ ይማረን
በሁለት ቢለዋ አስብተን እያረድን
ዳዊት ከደገመ ጠዋት ምላሳችን
ማታ ላይ ስድብን ለምዶ አንደበታችን

ሊምረን ቢመጣ ቁጣውን ሊያበርደው
ምላስ ብቻ ቀርቷል ለካስ ልብ ባዶ ነው
በሐይማኖት ጥላ ተሸሽገን ከርመን
እምነት ግን ሲጠየቅ ሁላችን ከንቱ ነን።
ቼር ምሽት


#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#ጉቻለሁ_ፍቅሬ

ጓጉቻለሁ የምር
ሽክ ብለህ እምር
ስትመጣ ወደ'ኔ
ባንተ ድምቀት ምክንያት
ሲፈካልኝ ቀኔ
እንደ ወጣቶቹ እስካይህ ዘንጠህ፣
በሱሪ በሸሚዝ በካፖርት አጊጠህ፣
ወይ እንደ አባቶችህ ጋቢና ከዘራ፣
ሰው ሰው እስክትሸተኝ ነብስ እስክትዘራ፣

ጓጉቻለሁ በጣም....
ልክ እንደ ክርስቶስ....
ባይኖርህ ትንሳኤ በሶስተኛዋ ቀን፣
ትመጣለህ በሚል እየዎዘዎዘኝ
የናፍቆት ሰቀቀን፣
መቃብር ፈንቅለህ
እስካገኝህ ባካል፣
ስንት አመት ይፈጃል መቼላይ ይሳካል፣
እላለሁ...
ሁልጊዜ እብሰለሰላለሁ...

ግን እባክህ ፍቅሬ...
ባቆሰልኩት ፊቴ በደራረብኩት ማቅ፣
ንገረኝ መምጫህን ትንሳኤህን እንዳቅ፣

በቅርቡ ከመጣህ ሳይደክም ጉልበቴ ፣
እቀበልሀለሁ ደግሼ ከበቴ፣
ምናልባት ከሆነ ...
ለመምጣት ያሰብከው...
አመታት ተቆጥሮ ዘመንን ሲገፋ፣
እንዳንጠፋፋ...
እኔው እመጣለሁ ጠብቀኝ አትልፋ


#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#አንድ_ቀን

#አፍቅሪኝ አልልሽም
እኔ እንዳፈቀርኩሽ
ተጎጂ አልልሽም
እኔ እንደተጎዳሁት
አንቺን በኔ ቦታ ማየት አልፈልግም
ከቶ አያረካኝም…
ግን ብቻ አደራ…
ከልብሽ ውደጂኝ ከውስጥሽ አኑሪኝ
ከህሊናሽ ካልራኩ ቢቆጠሩ አመታት
ታፈቅሪኝ ይሆናል አንድ ቀን ምናልባት


#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


19😘😍

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የአመት ሰው ይበለን😍😘

@qdist


​​​​​#የመገፋት ህመም የማጣትን ፍቺ
ልንገርሽ እንጂ እኔ የት አውቀሽው አንቺ

ብዙ ነገ እየሳልኩ አብሬ ካንቺ'ጋ
ሳስብሽ አመሸሁ እያለምኩሽ ነጋ
ሀሳቤን ሰርቀሽው ቀኔ አላማረበት
ቀልቤን ሰውረሽው አዋዋል ጠፋበት
ከእኔ'ጋ ነሽ እያልኩ አብረሽኝ ከጎኔ
አንቺ ሩቅ ሄደሻል እዛው ቀረሁ እኔ

የቀረበሽ ልቤ አንቺን በወደደ
የማያውቀው ነፍሴ በእሳትሽ ነደደ
መላ አካሌ አፍቅሮሽ እኔን ጥሎ አበደ
የኔ ያልኩት ሁሉ ትቶኝ ተሰደደ
እፋረድሻለሁ በይ ካሽኝ እያልኩኝ
ለብቻየ ስቀር ብዙ እንዳልነበርኩኝ

ለማን ዳኛ ልክሰስ ማንስ ይሰማኛል
ጉዳቴን ያሰበስ ምንድን ይክሰኛል
ጉዳዬን የሰማ ያ ሁሉ ዳኛ ሰው
ክሴን አቃለለ ብሶቴን መለሰው
እንግዲህ ምን ላድርግ...
ፍትህ ንብረት አይደል አልገዛ አልዋሰው

የሰማኝ በሙሉ የነገርኩት ዳኛ
እሷን ነፃ አረጋት እኔን ጥፋተኛ
ከእንግዲህ ለማንም አልከስም በቅቶኛል
እስካሁን የሰማኝ አይሆንም ብሎኛል
አንቺ ጉልበተኛ አንቺ ባለጊዜ
እኔ ሟች ደካማ የዋጠኝ ትካዜ
አንቺን ማን ተሟግቶ ችሎ ያሸንፍሻል
የቀረበሽ ሁሉ ላንቺ ያዳላልሻል
ቁመናሽ እሳት ነው አይን ጥርስሽ ገመድ
ውበትሽ አሳሳች አሳሳቅሽ ወጥመድ
ማለፍ ቢሳናቸው ይሄንን ፈተና
እኔን 'በዳይ' ማለት ቀለላቸውና
እሷን ተበዳይ ሰው እኔን ወንጀለኛ
ብለው ፈረዱብኝ ከአንድም ሶስት ዳኛ

አምርሮ ቢያነባ እንባዬ ቢፈስም
በያገኘው ችሎት እልፍ ጊዜ ቢከስም
የፍርድን ጥም ሽቶ ከጫፍ ጫፍ ቢያስስም
ገሳጭ ሰው ነው እንጂ አይዞህ ባይ አይደርስም

በቃኝ አልካሰስ ይቅርብኝ ልጎዳ ልተወው ግዴለም
ብቻ አውቄዋለሁ በሰዎች ደጅ እንጂ ፍትህ በአገር የለም
አትፍሰስ ይበቃል ከእንግዲህ እንባዬ
ጩኸቴ አላዋጣም ይርታት ዝምታዬ

እንግዲህ ገብቶኛል...
ላገኘሁት ሰሚ አልከስ አልዘልፍሽም
በየአደባባዩ ስምሽን አልጠራሽም
በየችሎቱ በር ነይ ግቢ አልልሽም...
ስምሽን ባጠፋ ብሰድብሽም እንኳን አትደናገሪ
ጩኸቴ ምንም ነው ዝም ስል ግን ፍሪ

    
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


Репост из: 🎀 fôř ėvěř 🎀
ሲከፋህ አልወድም

አለሜዋ......
የልቤ እንጉርጉሮ
     የልሳኔ ዜማ
ጆሮ ዳባ አትበል
        ቃሌን ስማኝማ
ይቺ ወረተኛ
       ሽሙጠኛ አለም
ቢሮጡ ቢደክሙ
        መውደቅን ምታልም
ለዚች ተንጎራዳጅ
         ልብን ለማትሞላ
ጭፍራ አዘል ከጀርባ
       ለአምሳዮች ተድላ
ዛሬ ሙልት ስትል
        ጎደለዋ ነገ
የንጋት ፀሀይዋ
      ጭራሽ ላልፈገገ
ከዚች ካልሞላላት
          ሙላትን አጠብቅ
የተስፋህን እጅ
         "አላማ አትልቀቅ"

ልቤን ክፍት አለው እምም አለኝ እኔ
ሲከፋህ አልወድም የምወድህ እኔ(ሳቅልኝ).

🥀
@saktawocu🥀


#ቀን_ሲጥል

ሰምሃል ሊዲያና ራኬብ እየተሳሳቁ ልክ ወደ ዶርም ሲገቡ ኤቤጊያ ወደውጪ ለመውጣት እየተኳኳለች ነበር ሰምሃል ሳቋን በአንዴ አቆመችና ቦርሳዋን አልጋዋ ላይ አስቀመጠችና ወደ ሎከሯ ሄደች ራኬብና ሊድያ ደክሟቸው ስለነበር ሃደው አልጋቸው ላይ ተዘረገፉ ኤቤጊያ መኳኳሏን አቁማ ወደ ሰምሃል እየተጠጋች አረ... ሰሙዬ አሁንም እንዳኮረፍሽኝ ነው ወር ሞላኝ እኮ ካኮረፍሽኝ ያጨዋታሽና ሳቅሽ ናፈቀኝ እባክሽ ይቅር በይኝ በቃ አለቻት ሰምሃል ምንም መልስ ሳትሰጣት አድርጋቸው የነበሩትን ጉትቻ የጆሮ ጌጦች እያወለቀች ሎከሯ ውስጥ ስርአት ባለው መልኩ ታስቀምጣለች።

ኤቤጊያ የሰምሃል ዝምታ ሲበዛባት ጮክ እያለች እሺ ቆይ ምን እንድልሽ ነው ምትፈልጊው ከዚ በላይ መቶ ግዜ እኮነው ይቅርታ ያልኩሽ የምር ሰሙዬ ሁለተኛ አይለመደኝም የእውነት አንቺ የፈለግሺውን ነገር ቅጪኝ እና ልገላገል እኔ ዝምታሽ ሊበላኝ ነው አለቻት ሰምሃል እንደመበሳጨት እያለች የሎከሩን በር አጋጭታ ዘግታው ወደኤቤጊያ ዞረች እኔ አንቺን የመቅጣት ፍላጎት የለኝም የዛን ቀን ርክክለኛ ማንነትሽን ነው ያሳየሽኝ በጣም ነው ያዘንኩብሽ እንደዛ አይመት የቀሸመ ስብእና ይኖርሻል ብዬ አላስብም ነበር እኔ ባንቺ አዘንኩብሽ እንጂ አልተቀከምኩሽም ያስቀየምሽው እኔን ሳይሆን ናኦድን ነው አሁን ውጪ ሊያገኝሽ እየጠበቀሽ ነው ጥሪልኝ ብሎኛል ሄደሽ አናግሪው የእውነት ያደረግሽው ነገር ከፀፀተሽ ይቅርታ በይው ይቅርታ ሳትጠይቂው ብትመለሽ እኔን አያድርገኝ ብላ ጮኀችባት።

ሊዲያ እና ራኬብ የሁለቱን ጭቅጭቅ ድምፃቸውን አጥፍተው ከመስማት ውጪ ምንም ትንፍሽ አይሉም። ኤቤጊያ እያቅማማች እህህህ አሁን እኮ ከራስታው ጋር ልንወጣ ተቀጣጥረናል እንዴት ብዬ ነው ሞሮ ጋር እምሄደው አለቻት ተሳስታ ሞሮ እንዳለችው ስራውቅ በጣም ደነገጠች ሰምሃል ይበልጥ ፊቷ ሲቀላ ታወቃት እዛው በቆመችበት ደነፋች የምርሽን ነው!!! አንቺ እሚያስጨንቅሽ ከእንድ ሰው ጋር ስለመውጣት ነው ያስቀየምሽው ሰው ያስለቀስሺው ሰው አይታይሽም አለቻት ኤቤጊያ በአፍረት አንገቷን አቀረቀረች መልሽልኛ ብላ ጮኀችባት መሄድ ትችያለሽ አልከለክልሽም ግን ዳግም ጓደኛዬ ብለሽ አጠገቤ እንዳትደርሽ አለቻት ኤቤጊያ ደነገጠች እሺ በቃ እሄዳለው የቱ ጋር ነው ያለው አለቻት ሰምሃል ተናዳ ስለነበር እነሱን ጠይቂያቸው ብላ ወደነራኬብ ጠቁማት አልጋዋ ውስጥ ተጠቅላላ ገባች ራኬብ በመስኮት ናኦድ የቆመበትን ቦታ አሳየቻት እሺ ያው እየሄድኩ ነው ሰሙ በድጋሚ ይቅርታ ሁሉንም ነገር አስተካክለዋለው ብላት በፍጥነት ከዶርሙ ወጣች።


ይቀጥላል.....
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#ቀን_ሲጥል

አባዬ ብዙ ካሰላሰለ በኃላ ወደ ኪያር ዞረና ኪያር መኪና መንዳት ትችላለህ ብሎ ጠየቀው አው እችላለው ጋሼ አለው አባዬ የመኪናውን ቁልፍ አቀበለውና በል በቃ ደርሳችው ነገውኑ ዊዝድሮው እንደጨረሳችው ይዘኀው ተመለስ አደራ በጣም ተጠንቀቁ ብሎን ሄደ ልክ አባዬ የውጪውን በር ከፍቶ እንደወጣ yessss..ብዬ ከመቀመጫዬ ተነስቼ ዘለልኩ ወደ ሰሙ እያየው አይ ሰሙ መለኛ እኮ ነሽ ማነው በናትሽ ውሸት እንዲ ያስተማረሽ በአንዴ እዚው ፈጥረሽ አሳመንሽው እኮ አልኳት ሰሙ ኮስተር ብላ እየቀለድኩ አይደለም ናዲ እኔ የእውነቴን ነው የተናገርኩት ዊዝድሮው ሞልተህ ተመለስ እዛ ስንሄድ ምንም ነገር እንዳታደርግ just ዊዝድሮው ሞልተህ ነገውኑ ትመለሳለህ ተናግሪያለው አባትህ ለኛ ነው አደራ ብለውን የሄዱት ምንም ነገር እንዲፈጠር አልፈልግም አለችኝ እሺ ችግር የለውም ግን አንድ ነገር.ላስቸግርሽ እዛ ስንሄድ ኤቤጊያን እንድታገናኚኝ ብቻ ነው እምፈልገው ሌላ ምንም አልፈልግም አልኳት እእህህህህ ለካ ለሷ ብለህ ነው ናዝሬት እምትመጣው አለችኝ ልዋሻት ስላልፈለግኩ አዎ አልኳት እየተናደደች እሺ አለችኝ።

ከሰአቱን ከቤት ወጥተን እዛው ቦሌ አከባቢ ዞር ዞር ብለን ስንዝናና ዋልን ያው እኔ ከቤት ወጥቼ ስለማላውቅ እኔን ለማዝናናት ታስቦ ነው ታናሽ እህቴም አብራን ነበረች እኔና ሰሙ ከኃላ ቀስእያልን ወክ እናረጋለን መሃል ላይ ራኬብ እና ሊዲያ አንድ ላይ እያወሩ ናቸው ኪያር እና እህቴ ደሞ ከፊት ሆነው ይሄዳሉ። እዛው ከሰፈራችን ብዙም የማይርቅ ካፌ ገብተን ስንጨዋወት 11፡00 ሰአት ሆነ ሁላችንም ወደቤት ተመለስን እህቴ ስትቀር ሁላችን ናዝሬት ልንሄድ ተነሳን እናቴ ያዘጋጀችልኝን ትንሽዬ ሻንጣ መኪናው ውስጥ አስገባው እነሰሙም ቦርሳቸውን ምናምን ይዘው ከኃላ ገቡ  ኪያር ቁልፉን ተጭኖ መኪናዋን አስነሳ  እኔ እናቴን ቻው ብያት ወደመኪና ስሄድ ጠንቀቅ በል እሺ የትም እንዳታመሽ ደሞ አለችኝ ሃሳብ የገባት ይመስላል።

እሺ እማ የትም አልሄድም ቻው ብያት ጋቢና ገባው እህቴ ዋናውን በር  እየሮጠች ሄዳ ከፈተችልን ዛሬ የእህቴ ቅልጥፍና እያሳቀኝ ነው ዘበኛው እያለ ምን እሷ ያጣድፋታል እየወጣን እያለ ኪያርን ቻው አለችውና ስንሄድ ቆማ አየችን ገዞ ወደናዝሬት! መንገድ ላይ ሁላችንም  እየተንጫጫን እየቀወጥነው እያወራን ሄድን ሲመሻሽ ናዝሬት ገባን ኪያር መኪናዋን ቀጥታ ወደ ግቢ ይዟት ገባ እነሱሙን ወደ ዶርማቸው አከባቢ አደረሳቸውሊጠይቁኝ ስለመጡ በጣም አመስግኛቸው መሰነባበት ጀመርን ሰሙ ኤቤጊያን ጠራልሃለው መልካም እድል ብላኝ ከራኬብ ጋር ቶሎ ሄደች የሆነ የደበራት ነገር እንዳለ ቀልቤ ይነግረኛል ሊዲያን ምን ሁና ነው አልኳት አይ መንገዱ ነው ትንሽ አሟት ነበር ቅድምም አለችኝና እኔና ኪያርን ቻው ብላን ሄደች።

ኪያር በቃ በርታ በል እኔ እዛ ጋር ሆኜ እጠብቅሃለው እንዳትፈራ ሴቶች እሚፈራ ወንድ አይመቻቸውም እሺ መልካም እድል ብሎኝ ፊትለፊት ጨለማ ውስጥ ጥንዶች የሚቀመጡበት ወንደር ላይ ሄዶ ተቀመጠ። የመጨረሻዋ ሰአት ደረሰች!! ኤቤጊያ ከደቂቃዎች በኃላ ትመጣለች ልቤ በፍጥነት መምታት ጀመረ ሰውነቴ ከበደኝ እንደምንም ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩና ቀና ብዬ መኪናዋን ተደግፌ ቆምኩ ከትንሽ ቆይታ በኃላ አንዲት ሸንቀጥ ረዘም ያለች ውብ ከሴቶች ዶርም ወጥታ ስትመጣ አየው።


ይቀጥላል.....
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#ቀን_ሲጥል

ሰምሃል ለእኔ ብላ ኤቤጊያን አንድ ወር ሙሉ ማኩረፏ አስገረመኝ ተገረምኩባት ስብእናዋ ያስደንቃል አንድ ወር እንኲን በቅጡ ለማታውቀው ሰው ብላ ለአመታት የምታውቃትን ጓደኛዋን አኮረፈች ይገርማል። ብዙ ከጨቀጨቅኳት በኃላ እንዲታረቁ አስማማኃት ሲቀጥል እኔ ኤቤጊያን አልተቀየምኳትም የተናገረችው ነገር ደባሪ ሊሆን ይችላል ግን አሁንም ድረስ ወዳታለው የዛኔ የኔም ጥፋት ነበረበት መታመሜን ልትጠይቅ የመጣችን ሴት ዘልዬ አፈቅርሻለው ምናምን ማለት አልነበረብኝም እንደውም ጥፋተኛው እኔ ነኝ አልኳት።

እያወራን እያለ አባዬ ከቤተክርስቲያን ተመልሶ ነጠላውን አጣፍቶ ወደቤት ገባ አራቱም ደንገጥ ብለው አባዬን ሰላም ሊሉት ከመቀመጫቸው ብድግ አሉ እኔ ደሞ ሁኔታቸውን አይቼ ፈገግ አልኩ እነሰሙ በደምብ ስለማያውቁት ነው ከሁሉም ያሳቀኝ የኪያር ነበር ቤቴ ሁሌ ሲመጣ ኖሮ ዛሬ እንዳዲስ መደንገት ሃ..ሃ..ሃ... አይ ኪያር።

አባዬ ገና ሰምሃልም ሲያያት ነበር ደስ ያለው እንዴ መጣችው እንዴ ጠፍታችው ቆያችው ምነው አላቸው ወደ ሰምሃል እያየ እሷም አፈር እያለች አይ የፈተና ሰሞን ስለነበረ ትንሽ ተጨናንቀን ስለነበር ነው ጋሼ አለችው። አይ ደግ ይሁን በቃ በደምብ  ተጫወቱ እንደቤታችው ቁጠሩትቁጠሩት ብሏቸው ወደላይ ሄደ ቤተሰቦቼ ሰምሃልን በጣም ነው የሚወዷት ስለሷ ብዙም ባያውቁም እኔ ያደረገችልኝን ሁሉ ነግሪያቸው በጣም ወደዋታል በተለይ አባዬ። እኛም ጨዋታችንን ቀጠልን በመሃል እያወራን ዛሬ ከናንተ ጋር ወደ ግቢ ለምመጣት አስቢያለው አልኳቸው ደስ አላቸው ግን ችግሩ አባዬ እሚፈቅድልኝ አይመስለኝም እሱን ለማሳመን የተቻለኝን አደርጋለው እናንተም ታግዙኛላችው እሺ አልኳቸው ተስማሙ ግን ኪያር ቅር ያለው ይመስላል ምክንያቱም ለምን ለማን ብዬ ናዝሬት እንደምመለስ ያውቃል ድጋሚ ኤቤጊያን ለማግኘት እንደሆነ ያውቃል እየደበረው እሺ አለኝ።

ሁላችንም ምሳ ከበላ በኃላ ሁሉም ባሉበት ስፈራ ስቸር አባቴን ግቢ ደርሼ መምጣት እንደምፈልግ ነገርኩት  ወዲያውኑ የቲቪውን ሪሞት ከጠረጵዛው ላይ አንስቶ ድምፁን እየቀነሰ ኮስተር ብሎ ምን? አለኝ ድምፁ ይበልጥ አስፈራኝ። አይ አባዬ አሁን ተሽሎኝ የለ ደህና ነኝ እኮ ግቢ ዛሬ ደርሼ መምጣት ፈል.... አባዬ እስክጨርስ አልጠበቀኝም ቆጣ ብሎ አይቻልም! ብሎ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፈ። ኪያር ጋሽ ምሽጉ እኛ ስላለን እኮ ችግር የለውም እንጠብቀዋለን ምንም አይሆንም አለ አባዬ ግን በሃሳቡ ፀና አይሆንም የሆነ ነገር ቢሆን ፀፀቱን አልችለውም ብቸኛ ወንድ ልጄ ነው አለው።

ዝምታ ሰፈነ ሁሉም ከተረጋጋ በኃላ ሰምሃል ወደ አባቴ እያየች ጋሼ እኔም በእርሶ ሃሳብ እስማማለው ናኦድ ህመም ላይ ነው ነገር ግን ደግሞ ብዙ አመት የለፋበት ትምህርት አለ ያንን ትምህርት እንዲው እንደቀልድ መተው ለእርሶም ለናኦድም የህሊና እረፍት አይሰጥም ናኦድ በጣም ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ አውቃለው በዚ አመት ዊዝድሮው ፎርም ካልሞላ  ቀጣይ አመት መመለስ አይችልም ይባረረል ዩኒቨርስቲው የሚያውቀው አሁንም በትምህርት ላይ እንደሆነ እንጂ በህመም ምክንያት አቋርጦ እንደሄደ አያውቅም ስለዚህ ድጋሚ ተመልሶ ያለውን ሁኔታ ገልፃ ዊዝድሮው ሞልቶ መመለስ አለበት እኔም ባይሄድ ደስ ይለኝ ነበር ግን ፋይናል ፈተና ሳይጀመር ዊዝድሮው መሙላት አለበት አለችው። አባዬ በትምህርት ምንም አይነት ድርድር ስለማያውቅ ሊቃወምበት የሚችለው ምክንያት አልነበረውም።

ይቀጥላል.....

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


Репост из: 🎀 fôř ėvěř 🎀
ከማፍቀር የሚገኝ ደስታ የራስ ነዉ። ማፍቀር ምላሽ አይጠይቅም የግድ መፈቀርም አይሻም ማፍቀር በራሡ ደስስ ይላል
        
"እውነተኛ ፍቅር መራራ ነገርን በሚያስከትል እንደስኳር በሚጣፍጥ ቃላት ወይም ጨለማን በሚያስከትል ብርሃን የታጀበ አይደለም የእውነተኛ ፍቅር ብርሃን አንዴ ከበራ የማይጠፋ፣ካመነ የማይክድ፣ከወደደ የማይጠላ የራስን ሕይወት አሳልፎ ለሌላው እስከመስጠት የሚያደርስ መለኮታዊ ስጦታ ነው።

ይሕንን ውድ ስጦታ ከፈጣሪ የሆኑ ፈጣሪ የፈቀደላቸው ብቻ ይታደሉታል በመሆኑም ፍቅር የጨዋዎች አብይ መልእክት እንጂ የባለጌዎች ዲስኩር አይደለም አዎን  እውነተኛ ፍቅር ካምላክ በትጋት የሚሰጥ ነው


Join👇👇👇
@saktawocu
@saktawocu




#ቀን_ሲጥል

ወር ሞላኝ ቤት ከተቀመጥኩ ከህመሜ ድኛለው ማለት ይቻላል በየቀኑ ሰምሃል ሳትደውል የዋለችበት ቀን ትዝ አይለኝም ሁሌ ትደውላለች ክላስ ትንሽ ተጨናንቀው ስለነበር መጥታ ለመጠየቅ አልተመቻትም  ዛሬ  ግን ከጓደኞቿና ከኪያር  ጋር መጥተው እንደምትጠይቀኝ ነግራኛለች ያው ኪያር ሁሌ ቅዳሜና እሁድን እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር እነሰምሃልም ቤታችንን ስለማያውቁት ይዟቸው ይመጣል።

ቤት ውስጥ መቀመጥ ሲሰለቸኝ ውጪ ወጥቼ ከቧንቧው በጎማ አድርጌ  አትክልቶቹን ውሃ እያጠጣው እያለ ታናሽ እህቴ ከፀጉር ቤት መጣች አምሮባታል እየሳቅኩ ምን ተገኘ እንዴ ዛሬ አልኳት እሷም እየሳቀች በፍጥነት  ኪያር ይመጣል አይደል ዛሬ? አለችኝ እቺን ይወዳል ለኪያር ነው እንዲ ፏ ያልሺ ሃ..ሃ..ሃ...   ኪያር እኮ እኔን ሊጠይቅ ነው የሚመጣው አንቺ ምን ቤት ነሽ እምትኳኳይው ብዬ ሳቅኩባት አኩርፋኝ ለምቦጫን ዘፍዝፋ ገባች እኔም እየሳቅኩ ታናሽ እህቴና ኪያር ምን አይነት ጥንዶች ሊሆኑ እንደሚችሉ እያሰብኩ በሳቅ እየፈረስኩ አትክልቶቹን ማጠጣት ቀጠልኩ በርግጥ ኪያር በጣም ጥሩ ልጅ ነው ከእህቴ ጋር አንድ ላይ ቢሆን ምንም ቅር አይለኝም። እንዲ ብዙ እያወጣው እያወረድኩ እያለ አንድ ላዳ ታክሲ በራችን ጋር አቆመ እያጠጣሁበት የነበረውን ጎማ ሰብስቤ ማን እንደመጣ ለማየት ወደ ላዳዋ ሄድኩ እነ ስምሃል እና ኪያር ናቸው።

ሰምሃል ከመኪናው ወጥታ እየሮች መጥታ አቀፈችኝና አንገቴን ሳመችኝ በየቀኑ በስልክ ስናወራ ስለነበር በጣም ተቀራርበናል ሁሌም ስለኤቤጊያ ሳልጠይቃት አልውልም ምን እንደሰራች ከማንጋር እንደዋለች እየጠየቅኩ አሰለቻታለው ዶርም ውስጥ ሆና ስታወራኝ ደሞ ጓደኞቿ ሊዲያ እና ራኬብ ስልኳን በግድ እየቀሙ ያወሩኛል ሶስቱም ደስ እሚሉ ጓደኛሞች ናቸው ፍቅራቸው ያስቀናል። ኪያር ሊዲያና ራኬብም እየተሳሳቁ መጥተው ሰላም አሉኝና ተያይዘን ወደቤት እየገባን እያለ ኪያር ጮክ ብሎ እንግዲ ይህ የምታዩት ትልቅ የተንጣለለ እልፍኝ የጋሽ ናኦል እልፍኝ ነው ቤተመንግስ አይደለም እንዳትደናገጡ እሺ አላቸው ወደነስምሃል ዞሮ እያየ ሁሉም ሳቁ። ለእናቴ ዛሬ ጓደኞቼ ሊጠይቁኝ እንደሚመጡ ስለነገርኳት ለነሱ እሚሆን አሪፍ ምሳ እያዘጋጀች ነበር በአንድ ወር ውስጥ ከኪያር እና የቅርብ ዘመዶቼ ውጪ ማንም ሊጠይቀኝ የመጣ ሰው አልነበረም ብቸኛ የሆንኩ ያህል ነበር የሚሰማኝ። እናቴ  ልክ ስትወጣ ኪያር ድምፁን ዝግት አድርጎ ዝም አለ እናቴ ሰላም አለቻችው ሰምሃልዬ የኔ ቆንጆ እንዴት ነሽ በደህና መጣችው አይደል አለቻት እናቴ ሰምሃልን በጣም ትወዳታለች ህይወቴን ስላተረፈችልኝ።

አንድ ቀን እንደውም ለምን እሷን አታገባም ቀለበት አድርግላት በጣም ጥሩ ልጅ እኮ ናት ብላኝ በሳቅ ፍርስ ስታረገኝ ነበር እናቴ ጣጣ የለባትም ፈታ ያለች ናት ነገር አታከርም። አይ እማ ጉዴን አላወቀች እንዴት በሌላ ሴት ፍቅር እንደምሰቃይ። ሳሎን ውስጥ ቁጭ ብለን እህቴ ዝንጥ ብላ ከላይ መጣች እኔ ስለገባኝ ከት ብዬ ሳቅኩ መጥታ ሁሉንም ሰላም አለቻቸው እሷ ሰላም ስትላቸው እኔ የኪያርን ሁኔታ እያየው ነበር በመሃል አቅቶኝ ድጋሚ ፍርስ ብዬ ሳቅኩ ሁለትም እንደሚዋደዱ እማውቀው እኔ ብቻ ነኝ ደስ ሲል። እህቴ መጥታ ከኔ አጠገብ ተቀመጠች። ወሬ ለማስጀመር ይመስል ኪያር አንተ በጣም ተስማምቶህ የለ እንዴ ወዝህ መለስ አለ  ዛሬ ደሞ እንዴት ነው በሸበጥ እና ቁምጣ አለኝ እህቴ ስትቅለበለብ ናዲ እኮ እንዲ ነው ቅዳሜና እሁድ ቀለል ያለ ልብስ ነው ሚለብሰው ደሞ እቺን ነጭ ቁምጣ ሲወወወ..ዳት አለችው  ፍጥነቷ አስደንግጧት ዝም ብላ ትንሽ ከቆየች በኃላ እናቴን ላግዛት ለናንተ ዶሮ እየሰራች ነው አለቻቸውና ተነስታ ወጣች።

ልክ እንደወጣች ሊድያ ወደኔ እያየች ደስ እምትል እህት አለችህ አለችኝ እኔም እየሳቅኩ አው ባክሽ እንዲ ናት ብዙ ግዜ ቅልብልብ ናት አሁን 12ኛ ክፍል ናት ያው ስትጨርስ እኛ ጋር ትመጣለች አልኳት ሰአቱ ገና ረፋድ ስለነበር ጨዋታችንን ቀጠልን በጨዋታችን መሃል ወደሰምሃል ዞሬ ኤቤጊያ እንዴት ናት አልኳት ፈገግ እያለች ደና ናት አለችኝ። ርብቃ እንደመቆጣት እያለች የት አናግረሻት እምታውቂውን ነው ደና ናት ምትይው እስካሁን እንደተኮራረፋችው አይደል እንዴ ብላ አፋጠጠቻት። ሁለቱ እየተከራከሩ እያለ በመሃል አቋረጥኳቸውና ሰምሃልን ምን ሆናቹ ነው የተኮራረፋቹት ስላት ዝም አለችኝ ወደ ርብቃ ስዞር እኔ ምን አውቄላት እቺ ዝምብላ ከመሬት ተነስታ ነው የዘጋቻት አለችኝ አይኗን እያጉረጠረጠች። ዝምታው ሲበዛ በቃ የዛኔ አንተን ደባሪ ንግግር ስለተናገረችህ አናዳኝ ነው ያኮረፍኳት አለችኝ።

ይቀጥላል ....

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#ቀን_ሲጥል

ኪያር በእህቴ በኩል መጣና ቆይ ላግዝሽ ሲላት ቦታውን ለሱ ለቀቀችለት እና ወደ እናታችን ጋር ሄደ በስንት ትግል መኪናው ጋር ደረስን ላብ በላብ ሆኛለው አባቴ ቀድሞ በሩን ከፍቶልን ገባን ሰምሃል በጣም ደብሯታል በቃ አትጥፋ እሺ ቤት መጥቼ እጠይቅሃለው እግዜር ይማርህ አለችኝ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም በጣም ነው ማመሰግነው ሰሙ አንቺም አትጥፊ እደውልልሻለው ስልክሽን እህቴ ጋር ተዪልኝ እና ሂጂ አልኳት።

ሳቅ እያለች እሺ ብላ ስልኳን ለእህቴ ነግራት ልትሄድ ስትል አባቴ ጠራት ድንግጥ ብላ አቤት ጋሼ አለችው አባቴ እየሳቀ ወደሷ ተጠጋና በጣም ነው እማማሰግንሽ ልጄን ስላዳንሽልኝ ውለታሽን በምን እንደምከፍል ወላውቅም ብቻ... እያለ ወደኪሱ ገብቶ ብር ሊያወጣ ሲል አረ በእግዜር ጋሼ እኔ ምንም አላደረኩም ማንም ሰው እሚያደርገውን ነገር ነው ያደረኩት ምንም ብር አያስፈልግም ጋሼ አልቀበሎትም በእውነት የሰራሁትን ስራ በብር አይቀይሩብኝ አያስፈልግም ብላ እጁን ይዛ አስተወችው በግድ ሊሰጣት ሲል አይሆንም ብላ እየሮጠች ሄደች።

ሁላችን አረ ተቀበይው አልናት እየተሳሳቅን እሷም እየሳቀች አይሆንም እቤት መጥቼ እጠይቅሃለው በቃ ቻው ብላኝ ሄደች አባቴ እየሳቀ ወደመኪናው ገባ እህቴም ከኔና ከኪያር ጋር ከኃላ ተቀመጥን እናቴ ከፊት ገባች ኪያር እቤት አድርሶኝ በዛውም ቤተሰቦቹን አዲስ አበባ ጠይቆ ሊመለስ አስቧል።
መንገዳችንን አቅንተን ከ1፡30 ሰአት ጉዞ በኃላ አዲስ አበባ ቦሌ አከባቢ ደረስን ሰፈራችን ቤት ገባን ይዘውኝ ወጥተው ወደ ሳሎን በኪያር እና በእህቴ እገዛ ገባው ደክሞኝ ስለነበር ሶፋው ላይ ተኛው።

ኪያር እራት ከበላ በኃላ ስለመሸ በግድ ካላደርክ አልኩት እሱም ያው እየደበረው እሺ አለኝ። እንደለመድኩት በእህቴና በእሱ እገዛ ሁለተኛው ፎቅ መኝታ ክፍሌ ላይ በመከራ ይዘውኝ ወጡ እናቴ ከኃላ ተከትላን ገባች አልጋው ላይ ከተኛው በኃላ ምን ላምጣላችው አለችን ምንም እምንፈልገው ነገር አልነበረም እህቴና እናቴ ወጡ። ልክ እነሱ እንደወጡ ኪያር ወደኔ እያፈጠጠ እሺ... የቅባት ልጅ እንደዚ ሲያዩሽ የሸራ ቤት ውስጥ እምትኖር ቦርኮ ነበር ምትመስለው ለማያውቅች እእእ ለካ እንዲ የተጃር ልጅ ነሽ አለኝ እየሳቀ ክፍሉን በአይኖቹ እየቃኝ ሆዴን ቢያመኝም ከት ብዬ ሳቅኩ ባክህ ሃብት ምን ያረጋል ጥቅም የለውም እፕልኩት እሱም እየሳቅ ስላለህ ነዋ ምንም እማይነስልህ አለኝ።

ይልቁንስ እሱን ተወውና ኤቤጊያን አናግርልኝ በናትህ ያው እኔ ሲሻለኝ እመጣለው አልኩት ወሬ ለማስቀየስ ይመስል ኪያር በግርምት እያየኝ ትንሽ አታፍርም እንዴ ቆይ አንተ ሌላው ቢቀር እንኳን ለራስህ ክብር ይኑርህ እንጂ እንደዛ ውሻ አድርጋህ ሄዳ አሁንም ወዳታለው ልትለኝ ባልሆነ እፈር ጌታ...ትን እፈር አንተ የምር አመት ከምናምን ከሰውነት ተራ ወጥተ መርፌ እስክታክል ድረስ ወደሃት ምን ፈየደልህ እእእ ሰድባህ አይደል እንዴ የሄደችው ያውም እንደዚ ሆነህ እያየችህ ለመሆኑ የሰደበችህን ስድብ ራሱ ልብ ብለኀዋል እኔ ላንተ በጣም እየረሰናኝ ነበር  የምር ናኦድ እርሳት በቃ አትበጅህም ተዋት አለኝ ተበሳጨው እንዴት ነው ምረሳር እንዴት ነው እምተዋት ይሄን ሁሉ ግዜ ያቃጠልኩት ላላገኛት ነው እንዴ ... አልረሳትም መሄም አልረሳትም መቼም

ደነፋሁበት ወይ ናዲ እምልህን ስማኝ አተን ሌላ ሴት ጥበስ በቃ እሷን እርሳት እኔ አጣብስሃለው ከፈለክ ሌላ ሴት አንተ ብቻ እሺ በል አለኝ እምቢ አልኩት ኪያር ብርድልብሱን ጎትቶት አኩርፎ ተኛ እኔም እያመመኝ ስለነበር ተኛው።
ሲነጋ ኪያር ወደቤተሰቦቹጋ ሊሄድ በጥዋት ተነሳ ቤተሰቦቼም በስም ስለሚያውቁት አመስግነው ላኩት እህቴ ውጪ ድረስ ሸኝታው መጣች ስትመለስ እየሳቀች ነበር ምነው እላታልው እየተሽኮረመመች ምንም ብላኝ ወደክፍሏ ሄደች። እኔም ቀን ከቀን በቤተሰቦቼ እገዛ ራሴን ማስታመም መጠገን ጀመርኩ ቀናት እያለፉ በሳምንት ተተኩ አራት ወንድማማች ሳምንቶችም በአንድነት ተባብረው ወርን አስቆጠሩ

ይቀጥላል ....

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#ቀን ሲጥል

ጓደኛዬ ኪያር ቅር ቢለውም በአባቴ ትእዛዝ መሰረት እንዳለ ጓዜን በሻንጣ ከግቢያችን ይዞት መጣ። ሻንጣውን ይዞት ላብ በላብ ሆኖ ሲገባ እህቴና ሰምሃል ተቀብለው አገዙት ከሰሙ ጋር ብዙም ሳንተዋወቅ ወደ አዲስ አበባ ልመለስ እንደሆነ ሳስብ ደበረኝ ሰሙም የደብራት ይመስለኛል  ግን ምን ችግር አለው ቀጣይ አመት እመለሳለው ይሄ ሴሚስተር እንደሆነ ገና ሊጋመስ ነው::

ገና ወደቤት ሳልሄድ ይሄ አመት አልቆ  ቀጣይ አመት መጥቶ የኤቤጊያን አይን ድጋሚ እስከማይ ድረስ ቸኮልኩ አረ... እኔማ የሷን አይን ሳላይ ለወራት መቆየት እምችል አይመስለኝም ብቻ ትንሽ ይሻለኝ እንጂ ተመልሼ መምጣቴ አይቀርም ናዝሬት እንደሆን የአንድ ሰአት መንገድ ናት አረ... እመጣለው ቀላል እመጣለው።

አባቴ በእኔ በጣም ተናዷል ዶክተሮቹ ሁሉንም ነገር ነግረውታል ሰክሬ ከሰው ጋር ተጣልቼ እንደሆነ አውቋል አሁን ስለታመምኩ ነው እንጂ ቢጮህብኝ ደስታው ነው ንዴቱ ከፊቱ ያስታውቃል አባቴ በጣም ሃይለኛ ሰው ነው እወደዋለው ግን እፈራዋለው ከልጅነቴ ጀምሮ ሳውቀው በትምህርት ቀልድ አያውቅም ለኔም ለእህቴም ከምንም ነገር በፊት ትምህርታችንን እንድናስቀድም ሁሌም ይመክረን ነበር። ኪያር ያመጣውን ጥቁር ተጎታች ሻንጣ አባቴ ከፈተው ልብሶቹ ከታጠቡ ዘመናት ስላለፋቸው  እሚያስጠላ ሽታ አፈነው ወዲያው እየተገረመ አፍንጫውን ይዞ ዞር ብሎ አየኝና ተመልሶ ሻንጣውን መበርበር ጀመረ::

ድንገት የትምህርት ማስረጃዎቼን እማስቀምጥበት ሰማያዊ ባይንደር ከልብሶቹ መሃል ታየው በጣም ደነገጥኩ ያለፈውን ሴሚስተር ግሬድ ሪፖርት ፊት ለፊት እንዳስቀ መጥኩት በደምብ  አስታውሳለው
ሰማያዊውን ባይንደር አነሳውና ቁጢጥ ብሎ ከተቀመጠበት ቀስ ብሎ ተነሳ የልብ ምቴ ሲፈጥን ይታወቀኛል።

ገልጦ ውስጡ ያሉትን ወረቀቶች ማየት ጀመረ ፊቱ ቀስ በቀስ ወደ ቀይነት ሲቀየር አይኖቹ ተጎልጉለው እስኪወጡ ድረስ ሲፈጡ አየኃቸው በጣም ተበሳጭቶ ባይንደሩን ከደነውና ሻንጣው ላይ እንደነገሩ ጣል አድርጎት ከክፍሉ በፍጥነት ወጣ ያለፈውን ሴሚስተር ምንም አልተማርኩም ፋይናል ፈተናም በአግባቡ አልተፈተንኩም ነበር የከዚቀደሙ ውጤቶቼ አሪፍ ቢሆኑም ያሁኑን ግን ከ2 ነጥብ በታች አምጥቼ በማስጠንቀቂያ ነበር ወደዚኛው ሴሚስተር ያለፍኩት አስተማሪዎቹም ቀድመው ስለሚያውቁኝ እንጂ ኤፍ እንደሚሰጡኝ እርግጠኛ ነበርኩ በብዛት ሲ እና ዲ አምጥቼ በማስጠንቀቂያ ነበር ያለፍኩት አባቴ ይህንን ሲያይ ነበር የተናደደው።

ውጪ ከእናቴ ጋር ሆነው ሲጨቃጨቁ ይሰማኛል። ታናሽ እህቴ ወደኔ ጠጋ ብላ አንተ ምን ሆነህ ነው ልብስህ እንዲ እስኪሆን ድረስ  የማታጥበው በጣም ይሸታል ሌላው ቢያቅትህ እንኳን ላውንደሪ ቤት መስጠት ያቅትሃል ብር አልጎደለህ ለምን እንዲ ትዝረከረካለህ አለችኝ ለራሴ ወላጆቼን ይዛብኝ መጥታለች እዚው ራሴን አስታምሜ እነሱ ምንም ሳያውቁ እንድድን እንዳትነግራቸው ብላት ጭራሽ ይዛቸው መጣች ለምን ይዘሻቸው መጣሽ ብቻሽን ነይ አልነበር ያልኩሽ ብዬ ተቆጣኃት እንዴ እና ታዲያ እስክትሞት እንድጠብቅ ነው ምትፈልገው አለችኝ እሷም መልሳ እየተ ቆጣችኝ።

ሰምሃልና ኪያ ይህንን ሁሉ ድራማ ጥግ ላይ ካሉት ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ከማየት ውጪ ምንም ቃል አይተነፍሱም እነሱም ለኔ ጨንቋቸዋል። ከታናሽ እህቴ ጋር እየተከራከርን እያለ አባቴ ከአንዲት ነርስ ጋር ወደውስጥ ገባ እና ወደኪያ እያየ  እእእእ ኪያር እስኪ ሻንጣውን ወደመኪናው አስገባልኝ ብሎ አዘዘው ኪያር ምንም ሳያቅማማ ሻንጣውን ይዞት ወጣ አባቴ ብስጭቱ ጋብ ያለለት ይመስላል ነርሷ አጠገቤ መጥታ ጉሉካሱ የተሰካበትን ገመድ ከእጄ ላይ ነቅላ ማስተካከል ጀመረች እኔም ለመነሳት ስዘገጃጅ እህቴና ሰምሃል መጥተው አግዘውኝ ከአልጋዬ ተነስቼ መሬቱን ረገጥኩ።

አባቴ ከኃላ ሆኖ መድሃኒቶቹን በፊስታል ይዞ ተከተለን እናቴ ከጎን ሆና እንባ እንባ እያላት ከማየት ውጪ ምንም አትልም። እኛ በረንዳው ላይ ቀስ ብለን እየሄድን ኪያር ሻንጣውን የአባቴ መኪና ጌር አድርሶት እየሮጠ ሲመለስ ተገጣጠምን።


ይቀጥላል ....
ስለቆየሁባችሁ በጣም ይቅርታ ጠይቃለው ስላልተመቸኝ ነው 🙏
አሁንም አብሮነታችሁ አይለየን

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#ቀን_ሲጥል

መሬት ላይ ስወድቅ ህመሙ ቢበረታም ከህመሙ በላይ ውስጤ ገብቶ ያሳመመኝ ከኤቤጊያ የወጡት አስነዋሪ ቃላት ነበሩ ውጤን በጣም ተሰማኝ።

ሰምሃል እና ኪያር ሊያረጋጉኝ ቢጥሩም ምንም ለውጥ አልነበረኝም ኪያ ሲቸግረው ሮጦ ሄዶ ዶክተሯን ይዟት መጣና ከወደቅኩበት መሬት አንስተውኝ አልጋው ላይ አስተኙኝ ነርሷ ቁስሉን ድጋሚ አፀዳችው እያፀዳችው ፊቴን በእጄ ሸፍኜ አለቅሳለው። እያስለቀሰኝ የነበረው ህመሙ ሳይሆን የኤቤጊያ ንግግሮች ነበሩ ቁርጥ ቁርጥ እያሉ አእምሮዬ ውስጥ ይመላለሱ ጀመር "እኔ ውደደኝ ሙትልኝ አልኩህ፣ ጀዝባ ሁንልኝ ብዬሃለው እኔና አንተ እኮ አንመጣጠንም ፍቅር ምናምን የሚሉት እንቶፈንቶ አይገባኝም፣ ለመሆኑ ረስህን አይተኽዋል...የኤቤጊያ ድምፅ ራሴን እስኪያመኝ ድረስ አእምሮዬ ውስጥ እያቃጨሉ ነበር። 

ነርሷ ከሄደች በኃላ ሰምሃል ወደኔ መጥታ እጄን እያሻሸችኝ ይቅርታ በጣም ናዲ እንዲ ታደርጋለች ብዬ አልጠበቅኩም ነባር በጣም ይቅርታ ይዣት መምጣት አልነበረብኝም አለች የኔ እንባና ሃዘን እየተጋባባት። ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ በእንባ የራሰው ፊቴን በመዳፌ እየጠረግኩ። በቃ አታልቅስ አይዞህ እሺ ናዲ እኔ አናግታለው አለ ኪያ እልህ ይዞት።

የተፈጠረውን ነገር ለማስረሳት ይመስል ሰምሃል ወይ ረስቼው ቁርስ አምጥቼላቹሃለው ያው ቤት ያፈራውን አለች  ፈገግ እያለች ያው አንተ ጉሉኮስህን ትጠጣለህ ኪያ ይበላል ባይሆን ስትድን ውጪ ጋብዝሃለው አለችኝ የሰምሃል አባባል ፈገግ አስባለኝ ኪያ እየተጣደፈ በፌስታል ያመጣችውን ምሳቃ ከፍቶ ቶሎ ቶለ ይደፍቅ ጀመር ሁለታችንም የኪያርን አበላል አይተን ተሳሳቅን። ኪያ ሁኔታችንን አይቶ ምን ትገለፍጣለህ ለሊቱን ሙሉ አንተን ስጠብቅ ፃሜን ነው ያደርኩት አለኝ ወደኔ እያየ። ለግዜውም ቢሆን ከኤቤጊያ ጋር የተፈጠረውን ነገር ረሳሁት።

ኪያ በልቶ ከጨረሰ በኃላ ትንሽ እንዳወራን ሰምሃልን ወደውጪ ይዟት ወጣ እሚያወሩት አይሰማኝም ቀስ እያሉ ይንሾካሾካሉ እኔም እሚሉትን ለመስመት ጆሮዬን ወድሬ ለመስማት ጣርኩ። ትንሽ ቆይተው ገቡ ኪያር ወደኔ መጣና በቃ ናዲ ዛሬ ከሰሙ ጋር ትሆናለህ እሺ እኔ programming exam ስላለኝ ልሂድና ላጥና ላንተም አስፈቅድልሃለው የተፈጠረውን ነገር ለጋሽ አሴ እነግራቸዋለው ይፈቅዱልሃል አለኝ እሺታዬን ከሰማ በኃላ ተሰናብቶኝ ሄደ።

ከሰምሃል ጋር ብቻችንን ቀረን ምን እንደማወራት ግራ ገባኝ በመሃል ዶክተሯ መጣችና ዝምታውን ሰበረችው ሁሉንም ነገር አይታ ከጨረሰች በኃላ ዛሬስ ተነስተህ ተራመድክ አለችኝ አይ አልተራመድኩም ስላት ተነስተህ ወክ አድርግ ትንሽ አለችኝና ሄደች። ሰምሃል ልታግዘኝ ተነሳች ከአልጋው ላይ ደግፋኝ ከተነሳው በኃላ እንደትናንቱ ኮሪደሩ ላይ ወክ አድርገን ተመልሰን ገባን። አልጋዬ ላይ ተቀምጬ ስልኬን ሳይ ሚስኮል አገኘው ታላቅ እህቴ ነበረች መልሼ ደወልኩላት ሰላም ከተባባልን በኃላ ትንሽ አውርተን የተፈረውን ነገር ለእናትና አባቴ እንዳትናገር አስጠንቅቂያት ነገርኳት በጣም ደነገጠች አሁኑኑ ተነስታ ወደናዝሬት እንደምትመጣ ነገረችኝና ተሰነባበትን።

አሁንም ከሰምሃል ጋር ምን እንደማወራ ግራ ገባኝ ወሬ ለማስጀመር ያክል እስኪ ስለራስሽ ንገሪኝ አልኳት። ሰሙ ፈገግ እያለች ምን እነግርሃለው ማወቅ የምትፈልገውን ጠይቀኝ አለችኝ። ምን እንደምጠይቃት ግራ ገባኝና ዝም አልኩ። ከሰአታት በኃላ እህቴ እየሮጠች እኔ ወዳለሁበት ክፍል ዘው ብላ ገባች በአንዴ ክፍሉን ወከባ በወከባ አደረገችው ግን እሷ ብቻ አልነበረም የመጣችው እኔትና አባቴም አብረዋት ነበሩ ሲገቡ ሳያቸው ደነገጥኩ እህቴን በቁጣ አየኃት።

ጤንነቴን በደምብ ካረጋገጡ በኃላ ጭቅጭቅ ያዝን ሰምሃል ሁሉንም ነገር ዝም ብላ እያየች ነበር ቅር ያላት ትመስላለች። ከብዙ ጭቅጭቅ በኃላ ትምህርቴን አቁሜ ዊዝድሮው ሞልቼ ወደ አዲስ አበባ እንድመለስ ተወሰነ

ይቀጥላል...

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


#ቀን_ሲጥል

ድርቅ ብዬ ቀረው አንዲት መልከመልካም ሴት ከፊቴ ቆማለች ሌላ ማንም የሰው ዘር አይታየኝም አቢጊያ ወደ እኔ መጥታ ስላም ነው። ናኦድ አለችኝ ደንዝዤ ቀረው እጄ ይንቀጠቀጥ ጀመር አቢጊያ ህመሙ መስሏት ደነገጠች ወደ ሰመሀል ዞራ ሰሙ እየተንቀጠቀጠ እኮ ነው እያመመው ነው መሰለኝ አለቻት ሰመሃል ፈጠን ብላ ወደ እኔ መጥታ ምነው ናኦድ ደህና አይደለህም እንዴ አለችኝ ቲንሽ ሰመሃልን ሳይ ተረጋጋው ደ..ደና ነኝ አልኩዋት እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ቁና ቁና እየተነፈስኩ ስላም ነው አልኩዋት አቢጊያ ፈገግ እያለች ደህና ነኝ እንዴት ነህ አንተ እየተሸለህ ነው አለችኝ።

እኔ ማመን አልቻልኩም በ ህልሜ በ ህልሜ ነው በውኔ? ምንም ይሁን ምን ከእዚ ህልም መንቃት አልፈለኩም ደህና ነኝ አልኩዋት ዝም አለች እሱዋም ዝም አለች ዝምታው ሲበዛ ኪያር ወንበር
ወደእሱዋ አስጠጋላት ተቀመጭ አላት እሱዋም ወንበሩን ስባ ከአጠገቤ ተቀመጠች ኪያር ከሁዋላዋ ሆኖ ፈገግ እያለ ጠቀሰኝና ሰሙ ነይ ዶክተሩዋን እናናግራት እና እንምጣ ብሎዋት ይዙዋት ሄደ።

ክፍሉ ውስጥ እኔ እና አቢጊያ ብቻ ቀረን ልቤ በጣም ይመታል አይደለም አጠገቤ ሆና ከርቀት ሳያት የምበረግገው አሁን በቅርበት ሆና እያየችኝ ነው ህመሙ ሆኖብኝ ነው እንጂ ጥያት ብሮጥ ምነኛ ደስ ባለኝ ዝም ብዬ በ ሃሳብ መብሰልሰል ቀጠልኩ ዝምታውን ለመስበር ይመስል ወደእኔ ቀና ብላ እያየች ሰመሃል ጥሩ የክላሴ ልጅ ናት ትናት ማታ አግኝታኝ ሁሉንም ነገር ስትነግረኝ ምን… በድነጋጤ አውርታ ሳትጨረስ ነገረችሽ ብዬ ጮክ ብዬ ጠየኩዋት ልቤ ከአፌ ልትወጣ ቲነሽ ቀራት አቢጊያ ደንገጥ እያለች አውው…በጣም ያሳዝናል ህግ ባለበት ሃገር እንደዚ ሲደረግ ያሳዝናል አግባብ አይደለም ምን አይነት ሰውስ ቢሆን ነው እነደዚ አይነት ጨካኝ የሚሆነው ዘመኑ ከፍቱዋል አለችኝ። እፎይ…ይ ተመስገን አልነገረቻተም አልኩ በልቤ ዝም ስል ምነው ዝም አልክ አለችኝ አ..አይ ዝም አላልኩም ቲንሽ ሰው ማናገር ስለሚከብደኝ ነው አልኩዋት እየሳቀች ታፍራለህ እንዴ ስትለኝ ተሽኮረመምኩ ይበለጥ ሳቀች ስትስቅ ደስ ትላለች ጥርሶቹዋ የተፈለቀቀ ጥጥ ነው።

የሚመስሉት ፈጣሪ ጥርሶቹዋን ተጠንቅቆ የደረደራቸው ማራኪ ተፈጥሮ ናቸው በእዚ ቅርበት አይቻት ስለማላውቅ ፍቅሯ በውስጤ ሲጨምር እሱዋነቷ ውበቷ እኔነቴን ሙሉ ለሙሉ ሲቆጣጠረኝ ተሰማኝ ሽቶዋ ደስ የሚል መአዛ አለው በግድ አፍንጫዬን ከፍቶ ልግባ ይላል በቃ ሞኝ ሆንኩ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ በደስታ ይሁን በሃዘን ስሜት አላውቅም ማልቀስ ጀመርኩ ውስጤ ባይፈለገውም መቆጣጠር አልቻልኩም ምነው አለችኝ ድንገት ያለፉትን ሁለት አመታት እንዴት እንዴት ሆኝ እንዳሳለፍኩዋቸው አይኔ ላይ ውል አለ ይበልጥ ተከፋው ኤቢ ከእዚ በላይ አፍኜው መቆየት አልችልም ይበቃኛል ልፈነዳ ነው እኔ ባነቺ ምክንያት ብዙ ተሰቃየው እኔ ካየውሽ ቀን ጀምሮ በጣም ነው የወደድኩሽ አምና መስከረም 24 ቀን እናተ ፍሬሽ ሆናችው ወደ ግቢ ስትመጡ ሻንጣሽን እየጎተትሽ ስትገቢ እኔ ደሞ ስወጣ ነበር ያየውሽ እኔ በቃ አልችለም ከእዚ በላይ በፍቅር መቀጣት አልችልም አልችልም አልችልም ባንቺ ምክንያት ትምህርቴን ተውኩ ጎብዝ ተማሪ ነበርኩ ያውም የባቻችን ሰቃይ አሁን ግን ጀዝባ ነኝ ሞሮ…ጉዋደኞቼ ሸሹኝ ሁሉም እራቁኝ አንቺን እንደምውድሽ ግቢው በሙሉ ያውቃል
አንቺ ግን አይደለም እንደምውድሽ ቀርቶ ምን አይነት ስው እንደሆንኩ እራሱ አታውቂም…በቃ በቃ በቃ ብላ ተቆጣች እኔም መነፋረቄን ለጊዜም ቢሆን
ገታውት ደነገጥኩ እኔ ሙትልኝ ውደደኝ ጀዝባ ሁንልኝ ብዬሃለው እንዴ ምን አይነት ወሬ ነው የምታወራው በእራሰህ ስንፍና እኔን ጥፋተኛ ታረጋኛለህ እንዴ እኔ እና አንተ እኮ አንመጣጠንም ለመሆኑ እራስህን አይተውሃል አለችኝ ቅፍፍ እያልኩዋት ፍቅር ምናምን የሚባለው እንቶ ፈንቶ አይገባኝም እሺ ሃ..ሃ ሃ.ሃ…ሃ ይውጣልህ ብላኝ የምጸት ሳቅ እየሳቀች ከተቀመጠችበት እየተገላመጠች ተነሳች።

እያመመኝ እየንተጠራራው እጇን ያዝኳት አቢጊያ እባክሽ አትሂጂ ስላት
እጀዋን መንጭቃ ሄደች ልከተላት ከአልጋው ላይ እየንተጠራራው ስነሳ ከአልጋው ላይ ወደኩ ይበልጥ አመመኝ ወደኋላ ዞር ብላ አየችኝና ወጣች አቢጊያ እንደዚ አይነት መልስ ትሰጠኛለች ብዬ ነበር እሺ ልትል እንደማትችል ገምቼ ነበር ግን እንደዚ ውጪ ከሰመሃል ጋር ተገጣጠሙ መሰለኝ ወዴት ነው ስትላት ሰማሁኝ አቢጊያ በጣም እየበሸቀች ለእዚ ነው የጠራሽኝ ዘመዴ ነው ምናምን ብለሽ ከዚ ጀዝባ ጋር ልታጣብሺኝ ነበር ያመጣሽኝ በጣም ነው የማዝነው ብላ ስትሄድ የጫማዋ ዳና ተሰማኝ ኪያር ወደ ክፍሉ ሲገባ መሬት ላይ ወድቄ ደም እንባ እያለቀስኩ ነበር ደንግጦ ናዲ…ምነው ብሎ ቀና አደረገኝ ሰመሃልም ስትገባ አየችኝ ጩኀቷን አቀለጠችው ወለሉ በደም እየራሰ ነበር  
 ይቀጥላል
...

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot


Репост из: 🎀 fôř ėvěř 🎀
#ከልቤ

ለምን አትበለኝ ምክንያት የለኝም
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም
ብቻ አፈቅርሀለሁ ማፍቀሬ ጥልቅ ነዉ
ፍቅርህ ለኔነቴ የልቤ ዙፍን ነዉ
ህያዉ የሚሆነዉ አንተን በማፍቀር ነዉ

ጅልነት አይደለም ሁሌ አንተን ማለቴ
ሞኝነት አይሆንም በፍቅርክ መክሳቴ
ዉለታ ፈልጌ ዉደደኝ አላልኩም
ፍቅር ሰጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም
በቃ አፈቅርሀለሁ ማለቴን አልተዉኩም

አዎ እወድሀለሁ አዎ አፈቅርሀለሁ
ፍቅርቅር አድርጌህ ሁሌም እኖራለሁ
አንተን በማፍቀሬ እፎይታ አገኛለሁ
አንተን እያፈቀርኩ በደስታ እኖራለሁ
አንተ ካለህልኝ ሙሉ ሰዉ እሆናለሁ
ከኔ እፎይታ ያንተን ደስታ አስበልጣለሁ
ጉዳትክን ከማይ የኔ ልብ
ይጨነቅ ተወዉ ብዬሀለሁ😢

@saktawocu
@saktawocu

Показано 20 последних публикаций.