Eterⁿal🔥Bläze


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


The blaze ablaze for life,and after life.
:Abracadabra🌪

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


በጠዋቷ ጸሐይ ገና በማለዳ
ፍቅር ሳላቅ ያኔ,በትንሿ ልቤ በልጅነት በአፍላ
አሻግሬ አይቼሽ በ ጨቅላ አይኖቼ
አስብሽ ጀመር በንፁህ አይምሮዬ
ትመታ ጀመር ያች' ትንሽ ልቤ

አይንሽን እያየው መግለጽ በማፈሬ
ወረቀት ላይ ብዕር ፍቅር አስነብቼ
ልብሽን ለመብላት ጥቅሶችን ጠቅሼ
እልክልሽ ነበር ልቤን በደብዳቤ

-'ኤል
@redemption4soul


ንፋሱ ቀላቅሎ:ጠረንሽን አቅፎ
ትዝታ ቀስቅሶ:ሙቀት ውስጤ ፈጥሮ

በርዶኝ ጸጉሬ ቆሞ:ቆዳዬ በድኖ
አፍንጫዬ ቢቀስም አነፍንፎ
ያንቺን መዓዛ:ያንቺን ሽቶ
ላብ ይደፍቀኝ ጀመር....

ይሀው...
ብርዱ,ከውስጤ ሙቀት ጋ' ተጋጭቶ
ነብሴን ይወጋኛል:ልቤ ስር ቀስፎ
-'ኤል
@redemption4soul


ℓιfє нαѕ σиℓу σиє ℓαω
тнє ѕмαℓℓєѕт мιѕтαкє, тнє вιggєѕт ρυиιѕнмєит.


...and,ma 6th sense that traveled with sleepy nights trip, told me that ; In some other life, u are on ma arms movin on and backward.
Whispering for u that music of ur favorite one in this life.
hold beside to ma heart,Ma lips on ur head
Holdin' ur little hand inside ma huge hand.
Maybe in some other life u are ma little baby girl.

@redemption4soul


Maybe in some other life,
We are standing side by side
Your arms on ma shoulder
Ma lips on your lips seeking the love
What I inhale is ur love flavor breath, what u breath is mine.
And our souls comes in one fount.

Thats what ma 7th sense that traveled with meditated trip;told me....


it's the philosophy of Africa.
It has the meaning in swahli that says don't worry ur self.don't worry about what happened,don'tworry about what will happen,andwhat will come. today is your day,ADIOS. ..HAKUNA MATATA.
@redemption4soul


🎶
.
Hakuna matata.
It means no worries
for the rest of ur days
It's our problem-free philosophy.
Hakuna matata.
🎶
@redemption4soul


Oh ma Lord where u are ?am ur creation.we bored and tired, but fire up. ...where are u?we searched in the higher place ,we look on the low too ....but..'where have you been?.🎶...we showered by the rain,we whistle with the winds,we burning through the sun.where you at though?

@redemption4soul


..
በብላቴናነት ጠፍጣፋ መሬት ላይ የሰየምናቸው ጠጠሮቻችንና ጢባጢቤዎቻችን፣'ሳይ፣ባንከረባብት' የተባባልንባቸው ብዮቻችን፤ከየሱቁ ደጅ አጎንብሰን ለቅመን 'ደስቶ ፊንገር' የተጫወትንባቸው የማስቲካ ልጣጮቻችን፤የሽቦ እሽኩሌታዎቻችን፤የበረኪናና የሴሪፋም ካርቱን መኪናዎቻችን፤እልፍ ድርድር ቆርኪ ያጨድንባቸው አኬራም ድንጋዮቻችን፤ዲሞና ቴዘር ያፈጋንባቸው የወተት ላስቲክ ኳሶቻችን፤ተረረም ያደረግናቸው የኮባ ሽጉጦቻችን፤የወረቀት መርከቦቻችንና እሽክርክሮሾቻችን፤የጨሌና የአካት ቀለበቶቻችን ዛሬ በአካል የት ነው ያሉት?...'ሞር' ደፍነን እንደ ፈረስ ባጎነበሱ የጓደኞቻችን ምቹ ጀርባዎች ላይ ተቀምጠን አሻግረን ስናይ የመርሳት ሀገሩ እንዲህ ቅርብ ነበር?ዕቃቃዎቻችን የከበሩት ባዶ ትዝታዎቻችን ውስጥ ብቻ ነው።በእውኑ ዓለም በቅጡ እንኳን አልተሰናበትናቸውም።...

-ከገጾች መሐል[ትዝታሽን ለእኔ፣ትዝታዬ ለአንቺ ]
@redemption4soul


ፍቅር ከ ክብር ጋር ተመሰቃቅሎብሽ
አበባዬን ገፍተሽ፡ጥይቱን መምረጥሽ
የኔን ልብ እረግጠሽ፡ጉልበቱን መሳምሽ
ከእግሩ በታች ወድቀሽ፡ደስታን ማርከፍከፍሽ...
አለሜ ይሄ ለኔ ...
...ከሞት በላይ ያማል።

የኔ ልብ አበባ፡ጥይት አያፈራ
አይምሮዬም ከቶ፡ለጥፋት አይሰራ
እንደ ንቧ መቅሰም፡ትተሽ ውብ አበባ
ከመረጥሽ ቆሻሻ፡የሰው ደም ላይ ማረፍ ሆነሽ እንደ ዝንቧ
ሱፌንም ለብሼ፡አበባዬን ይዤ
እየመጣሁ እሄዳለው,ላንቺ ሞቴን መርጫለሁ
ንብ ሳረግሽ ,ዝምብ የሆንሽው:ልሰዋልሽ እመጣለው።

ደሜ ላንቺ ይፈሳል....
......ፍቅሬም ውስጡ ይኖራል
አበባ ንቀሻል......
እንግዲያው ቅሰሚ፡ከደሜ ጋር-ፍቅር ፈሶልሻል።
-ኤል
@redemption4soul


.
አበባዬን ገፍተሽ፡ጥይቱን መምረጥሽ
የኔን ልብ እረግጠሽ፡ጉልበቱን መሳምሽ
ከእግሩ በታች ወድቀሽ፡ደስታን ማርከፍከፍሽ...
@redemption4soul








On the middle of the day.when the sun burns.givin' high energy.I was there waiting to you on ur door step,your love in ma heart burning all of me,blot out, the sun burning of the city. ☀
Your love is the sun of ma heart.
@redemption4soul


ከ ፍፁም ፀጥታ ወደ ጭንቁ ጨለማ አለም
ብርሀን የመሰለ እሳት ተሸክሜ ከጭኖቼ መሐል
እያለቀስኩ ወጣሁ ብርሃን በሚሉት በር ከሚሰገድለት።
ገና ብዙ ለቅሶ እንዳለኝ ያውቃሉ
እኔ እሪታ ሳቀልጥ እነሱ ያገጣሉ።

ብዙ ቀስቶች ተቀስተው
ጫፋቸውን አሹለው
ጦር ሆነው ታልመው
ብዙ ጊዜ ወግቶኛል
ብዙ ስቶኝ አልፏል
ነካክቶ አቁስሎኛል::
ሆድ ከሀገር ይሰፋል ይላሉ ተራቾች
የኔ አለም ማህጸን ይኸው በግድ ሰፍቶ ሰፍቶ
ሳምባዬ ተጨንቆ ልቤን አቁስሎኛል::
ሴት መሆን ክፋቱ ባለ ስንጥቅ'ኢቱ
ዘመድ ጎረቤቱ የአዳም ዘር በሙሉ
ጭንቅላት እያለው ጭን-ንቅል የሆነው
ቀን በአደባባይ ስቆ,ፍቅር አሳይቶ
በጭኑ ሰገባ ጎራዴውን ከቶ
ሲመሽ ይቀየራል የሰው ጅብ ይሆናል
ካ'መድ ሊንከባለል ቀበቶ ይፈታል::
አንገት ደፊ መስሎ አንገት አስደፍቶ,ቀሚስ አስገልቦ ይጋልባል ፈረስ-የትም 'ማይደርስበት
ይገርፍል ይረግጣል
ማያውቀው ስጋ ውስጥ ነብሱን ያሳድራል::

የፈጠርከኝ አምላክ ቀዳዳ አብጅተህ.....

በቃ ውሰድልኝ ድፍን ይሁን ማህፀኔ
ሽንቴም የዶሮ ይሁን ይበቃኛል ለኔ
በቃ ውሰድልኝ ድፍን ይሁን ማህፀኔ::
-ኤል
@redemption4soul


....
በቃ ውሰድልኝ ድፍን ይሁን ማህፀኔ
ሽንቴም የዶሮ ይሁን ይበቃኛል ለኔ
በቃ ውሰድልኝ ድፍን ይሁን ማህፀኔ...


Defeat, my Defeat, my solitude and my aloofness; You are dearer to me than a thousand triumphs, And sweeter to my heart than all worldglory. Defeat, my Defeat, my self-knowledge and my defiance, Through you I know that I am yet young and swift of foot And not to be trapped by withering laurels. And in you I have found aloneness And the joy of being shunned and scorned. Defeat, my Defeat , my shining sword and shield, In your eyes I have read That to be enthroned is to be enslaved, And to be understood is to be levelled down, And to be grasped is but to reach one's fullness And like a ripe fruit to fall and be consumed. Defeat, my Defeat, my bold companion,You shall hear my songs and my cries and my silences, And none but you shall speak to me of the beating of wings, And urging of seas, And of mountains that burn in the night, And you alone shall climb my steep and rocky soul. Defeat, my Defeat, my deathless courage, You and I shall laugh together with the storm, And together we shall dig graves for all that die in us, And we shall stand in the sun with a will, And we shall be dangerous.
-Khalil Gibran
💫
@redemption4soul


°°ያልተጠለለች ነብስ°°
ሰማዩ ጠቆቁሮ:ደመነው ደማምኖ
ሕዝቤ ይራወጣል:ቀፎው እንደተነካ ንብ,ይተማል ይሮጣል
ሲሸሹት ይመስል:አዝኖ የተከፋ
ሰማዩ ያነባል,መብረቅ ይባርቃል

እዛ ማዶ አንዷ:ቂጧን ጥላ ሮጣ
አንዱ ይከተላታል:ሊያቃብል ይሮጣል(ሊያቀባብል ?)
ባህል ይሆን እኔ አላውቅም:ሁሉም ላለው ያሽቃብጣል

አንዱ ጠባቂ ወጣት:ፍቅሩን ሳያገኛት
ዝናብ እንዳይዛት:ጎርፉ እንዳይወስድበት
ሰግቶ ለንቦጭ ጥሏል
የሚያነሳው ጠፍቷል:እግሮች ይረግጡታል
አልቅሶም ይሆናል:ማን ቀርቦ አይቶታል?
ጸልዮም ይሆናል:የልቡን ማንያውቃል?
ደግምት ተመኝቶ:ከእሷ እስከሱ መንገድ ፀሐይ ይሁን ብሎም ...?

ፊትለፊቴ ደግሞ.....
ሑለት አሮጊቶች:ጉልት ቸርቻሪዎች
ኑሯቸውን ሰብስበው:በዘንቢል ሸክፈው
ጀርባ ሰ'ተው ለኔ:ሱክ ሱክ እያሉ,ሲረግሙ 'ሰማለው
እኔ እስቃለው
(አቦ ግን ሲያምሩ)
ሁሉ' ያማርራል,ሁሉ' ይበሳጫል
ሰማዩ አይሰማም,ዝናቡ አላባራም,መዝነቡን ቀጥሏል ....
-ኤል
@redemption4soul


My happiness arise
before the sun rise.

Ma ear start drumming
After ma 1st blink.

I want to feel the hot
I want to feel the the cold.

Only felt both at once
When me ride on the morn'.

@redemption4soul

Показано 20 последних публикаций.

88

подписчиков
Статистика канала