(ድንገት)
አንዱን ወጣት አየሁት ፤
አይኔ እስኪፈቅድ ተከተልሁት ።
እያየሁት ... እየሄደ ...
እያየሁት ... እየሄደ ...
በሰው ማዕበል ተጋረደ ።
ጠፋ ፥
ተሰወረ ደብዛው ።
እንግዲህ ...
አዕምሯችን ታሪክ ፈጥሮ ካላንዛዛው
ወይ በምናብ ካላወዛው
ሰው መነሻው አይታወቅም
መጨረሻውም እንደዛው ።
By HAB HD
@Samuelalemuu
አንዱን ወጣት አየሁት ፤
አይኔ እስኪፈቅድ ተከተልሁት ።
እያየሁት ... እየሄደ ...
እያየሁት ... እየሄደ ...
በሰው ማዕበል ተጋረደ ።
ጠፋ ፥
ተሰወረ ደብዛው ።
እንግዲህ ...
አዕምሯችን ታሪክ ፈጥሮ ካላንዛዛው
ወይ በምናብ ካላወዛው
ሰው መነሻው አይታወቅም
መጨረሻውም እንደዛው ።
By HAB HD
@Samuelalemuu