SEBIL T UBE 🇵🇸


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


قُل هذِهِ سَبيلى أَدعو إِلَى اللَّهِ عَلى بَصيرَةٍ أَنا وَمَنِ اتَّبَعَني وَسُبحانَ اللَّهِ وَما أَنا مِنَ المُشرِكينَ ﴿١٠٨﴾
"ይህች መንገዴ ናት። ወደ አላህ እጠራለሁ። እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን።ጥራትም ለአላህ ይገባው። እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም"በል።
ቁር 12:108
@muslimman99

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


🌙تسحروا فإن في السحور بركة

💫من السنة تناول السحور

عن أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: تَسَحَّرُوا فَإِنَّ فِي السَّحُورِ بَرَكَةً رواه البخاري (1923)، ومسلم (1095).

ሱሁር አድርግ በሱሁር ውስጥ በረከት አለና።

ሱሑር ማድረጉ ሱና ነው።

አነስ ቢን ማሊክን ረዲያላሁ አንህ እንዳስተላለፈው፡- ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) "ሱሁር አድርጉ ፣ሱህር ውስጥ በረካ አለና "። ቡኻሪ (1923) እና ሙስሊም (1095) ዘግበውታል።

ሀዲሱ ፆመኛ ሱሑርን እንዲመገብ መታዘዙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው ምክንያቱም በውስጡ ብዙ መልካም ነገር እና ትልቅ በረካ እንዳለው በአኪራም ሆነ ከዱንያ ያስገነዝባል።

ጃቢር እንዳስተላለፉት የነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “መፆም የሚፈልግ ሰው በየሆን ነገር ሱህር ያድርግ "።

አህመድ (14533) ሲሆን በ “አል-ሲልሲላህ አል-ሰሂሃህ” (2309) አል-አልባኒ የተረጋገጠ ሃዲስ ነው ብሏል።

ይህ ሐዲሥ የሚያሳየው ሙስታሃብ እንደሆነ (ሱህር) እንጂ ግዴታ አንዳልሆነ ነው ለዚህም ማሳያው ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ና ባልደረቦቻቸው ከሳቸው ጋር ዊሳል አርግቶል፣ ዊሳል ማለት ሁለት ቀንና ከዚያ በላይ መፆም እና ፆሙን ሳያቋርጥ በቀንና በሌሊት መፆም ነው።
💫
@sebil_tube
@sebil_tube💫


#ፍታዋ2

#ጥያቄ:-

#በተራዊህ #ሰላት ውስጥ ኢማሙን ለመከተል በማለት #ማእሙሞች [ከኋላ የሚሰግዱት] #ቁርአን📖 #መያዛቸው እንዴት ይታያል?

#መልስ:-

🔰ለዚህ
#አላማ ብሎ #ቁርአንን📖 #መያዝ ሱናን #መፃረር ነው። ይህም በተለያየ መልኩ ነው፦

1⃣.ኛ በቂያም [ በመቆም ] ላይ ሰውየው
#ቀኝ #እጁን #ግራ #እጁ ላይ ማድረጉ ይቀርበታል።

2⃣.ኛ አስፈላጊ ላልሆነ
#እንቅስቃሴዎች ይዳረጋል። እነርሱም ለምሳሌ #ቁርአንን #መክፈት#መዝጋት#በብብት_ስር ወይም #በኪስ ማድረግና የመሳሰሉት ናቸው።

3⃣.ኛ እንዚህ እንቅስቃሴዎች የሰጋጁን
#ትኩረት ይስባሉ።

4⃣.ኛ ሰጋጁ
#የሱጁድን ቦታ መመልከቱ ያመልጠዋል። አብዛኛዎች #ዑለሞች እንደሚሉት ደግሞ በሰላት ጊዜ የሱጁድን ቦታ መመልከት #በላጭ #ሱና ነው።

5⃣.ኛ ይህን የሚያደርግ [ቁርአን የሚይዝ] ሰው ልቡ ወደ ሌላ ቦታ ካሰበ ሶላት ውስጥ መሆኑንም
#ሊረሳ ይችላል። በአንፃሩ ቀኝ እጁን ግራ እጁ ላይ አድርጎና አንገቱን ሰብሮ ወደ ስጁድ ቦታ እየተመለከተ #በኩሹዕ ከቆመ ግን ልቡን ለመሰብሰብና ከኢማም ኋላ ሆኖ በመስገድ ላይ መሆኑን ለማስታወስ በጣም ቅርብ ነው።

✉️
#ወላሁ_አዕለም

ምንጭ:-
[📚 فتاوا لفضيلت الشيك محمد صالح العثمين📚 ]


۩    ✨•━━━ ✽ • ✽ ━━━•✨   ۩
        【
@sebil_tube
      ╚════•| ✿ |•════╝
  ◢  【
@sebil_tube】  ◤
╚═━━━══•| ✿ |•═━━═══╝


እያሰብኩ ነበር… አላህ ዩሱፍን ከመጀመሪያው መከራ ቢፈርጀው… የግብፅ ንግስና እንዴት ትጠራው ነበር? … በወንድም መከዳት፣ በነጋዴ መሸጥ፣ በአፍቃሪ መሰቃየትና እስር ውስጥ መሰንበት… ተደራርበው ነበር  ንግስናውን የሰጡት… የአንዳንድ መከራዎች መደራረብ… ለውጤቱ ማማር ሰበብም ይሆናሉ… አንዳንዴ

فَصَبْرٌ جَمِيلٌ وَاللّهُ الْمُسْتَعَانُ عَلَى مَا
تَصِفُونَ


"وَلَسَوۡفَ يُعۡطِيكَ رَبُّكَ فَتَرۡضَىٰٓ".


"And surely your Lord will give so much to you that you will be pleased".


ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ ❤️‍🩹


@sebil_tube
@sebil_tube


🌙(ثلاثة لا ترد دعوتهم – ومنهم – الصائم حين يفطر)
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ثلاثة لا تُرَدُّ دَعْوَتُهُمْ الإِمَامُ الْعَادِلُ وَالصَّائِمُ حِينَ يُفْطِرُ وَدَعْوَةُ الْمَظْلُومِ يَرْفَعُهَا فَوْقَ الْغَمَامِ وَتُفَتَّحُ لَهَا أَبْوَابُ السَّمَاءِ وَيَقُولُ الرَّبُّ عَزَّ وَجَلَّ وَعِزَّتِي لأَنْصُرَنَّكِ وَلَوْ بَعْدَ حِينٍ رواه الترمذي (2525)، وصححه الألباني في "صحيح الترمذي" (20 أبي داوود" (2066)

(ሶስቱ ዱዓአቸው የማይመለስ አሉ - ከነሱም - ጾመኛ ፆሙን ሲፈታ)

✨ ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ሶስቱ ዱዓቸው የማይመለስ፡ ፍትሃዊ ኢማም፣ ፆመኛ ፆሞን ሲፈታ እና የተጮቆነ ሰው ዱዓ ከደመና በላይ ከፍ ይደረጋል። የሰማይ በሮች ይከፈትለታል አላህም እንዲህ ይላል፡- “፣ በሀይል (ይሁንብኝ) ከጥቂት ጊዜ በኋላም ቢሆን እረዳሻለሁ።

✨ ይህ ሀዲስ ፆመኛ ፆሙን የሚፈታበትን ጊዜ ተጠቅሞ የወደደውን መልካም ነገር እንዲለምን ምክንያቱም ዱዓው ምላሽ ይሰጠዋልና። ፆሙን ሲፈታ የመጀመሪያው የሚለው አብደላህ ብን ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት መልእክት ነው፡- “ዘሀበቲል ዘመዕ፣ወብተለቲል ኡሩቅ ፣ወሰበተል አጅሩ ኢንሻዓላህ"።

📖 በአቡ ዳውድ (2357) ዘግቦታል።

@sebil_tube 💫
@sebil_tube 💫


#ፈታዋ3

ጥያቄ :-
======

#ምግብ #በመቅመስ #ፆም ይፈርሳልን?

መልስ:-
=====

#ካልዋጠው በስተቀር በመቅመሱ ምክኒያት ብቻ #ፆም #አይፈርስም። ነገር ግን #አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር #አይቅመሰው። መቅመሱ አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝና ሲቀምሰው #ሳያስበው ወደ #ሆዱ #ቢገባ ግን #ፆሙ #አይበላሽም


✉️
#ወላሁ_አዕለም

ምንጭ:-
[📚 فتاوا لفضيلت الشيك محمد صالح العثمين📚 ]


۩    ✨•━━━ ✽ • ✽ ━━━•✨   ۩
        【
@sebil_tube
      ╚════•| ✿ |•════╝
  ◢  【
@sebil_tube】  ◤
╚═━━━══•| ✿ |•═━━═══╝


በፈሳድ ከተዋጠ ጀሰዳችን ላይ የአላህ መሐርታ ባይታከልና በእዝነት ፍስሀው ባያረሰርሰን በየትኛው ውል ሰው እንባል ነበር?

ሐምደን ሊረቢል አለሚን ያ ራህማኑ🤍


ረመዿን 7
🌙  هل تدركه بعد ذلك 🌙

🌟 ከዚህ በኃላ የሚመጣውን ረመዿንን ታገኘዋለህ ወይ? 🌟

🌌 لا ندري هل سنعيش إلى رمضان آخر.
🌌 كم فقدنا من عزيز أو جار أو قريب في رمضان

✨ እስከመጪው ረመዿን ድረስ መኖራችንን አናውቅም በዚሁ ረመዿን ስንትና ስንት ወዳጆችን፣ ጎረቤት እና ቅርብ ሰዎችን አጥተናል!


ይህ የተባረከ ወር በ ዓመት 1 ግዜ ብቻ የሚያልፍ የሆነ ወር ነው ቀጣይ ዓመት ይህን ወር ድጋሚ ማግኘትህን ወይም ደግሞ ከዚያ በፊት መሞትህን አታውቅም ስለዚህ በዚህ ወር ልትጠነክር እና ወደ አላህ የሚያቀርቡህን ነገራቶች በመተግበር ልትፈጥን ይገባል፤ እንዲሁም ከአላህ ቅጣት የሚያድኑህን ሰበቦችን ለመስራት ልትበረታ የአላህ መሃርታን የሚያስገኙ ወንጀልህን ሊያሰርዙ የሚችሉ መልካም ስራዎችን ልትሰራ ይገባል ምክንያቱም ቀጣይ ዓመት ይህን ወር ድጋሚ ማግኘትህን አታውቅም! 🌷

በዚህ ወር ለሙስሊሞች የተወደደ ነው፤ ሌሊቱን በሰላት ሊቆሙ በላጩ ፤11 ረክዓ ሊሰግዱ ሁለት ሁለት እያደረጉ፤ በውስጧም ቁርዓንን አስተካክለው ባማረ መልኩ በኹሹዕ ሊያነቡ ይገባል።🌷

በሰላቱም ሩኩዕ እና ሱጁድ ሲወርዱ በእርጋታ እና በኹሹዕ ሊሆን ይገባል በሰላታቸው አይቻኮሉ ጎንበስ ቀና ብቻ አያድርጉት፤ ዋናው የሚፈለገው ልክ ነብያችን ሲሰግዱ እንደነበረው በኹሹዕ በዕርጋታ እና ልባቸውን ሰጥተው በጥሞና ያማረ አቀራርን እየቀሩ እያስተነተኑ መሆን አለበት እንጂ አንዳንድ ሰዎች በሰላት ተራዊህ እንደሚሰግዱት የችኮላ ጎንበስ ቀና ሰላት መሆን የለበትም፤ ምናልባትም እንዲህ አይነት ሰላት ተቀባይነት የሌላትና የማትበቃ ሰላት ትሆናለችና።
🌷

[ 🔈 💐 የተከበሩ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ቢን ባዝ አላህ ይዘንላቸውና 💐]

@sebil_tube
@sebil_tube


🌙 (من فطر صائما كان له مثل أجره)

✨عَنْ زَيْدِ بْنِ خَالِدٍ الْجُهَنِيِّ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: مَنْ فَطَّرَ صَائِمًا كَانَ لَهُ مِثْلُ أَجْرِهِ غَيْرَ أَنَّهُ لا يَنْقُصُ مِنْ أَجْرِ الصَّائِمِ شَيْئًا رواه الترمذي وقال حديث حسن صحيح.

✨ هذا الحديث دليل على فضل تفطير الصائم، وإن في ذلك أجراً عظيماً، وهو مثل أجر الصائم وهذا والله أعلم؛ لأنه صائم يستحق التعظيم، وإطعامه صدقة، وتعظيم للصوم وصلة بأهل الطاعات. وهذا أمر اعتاده المسلمون لإدراكهم الثواب الجزيل المرتب على ذلك، فإن شهر رمضان شهر يجود الله فيه على عباده بالرحمة والمغفرة والعتق من النار، والله تعالى يرحم من عباده
الرحماء.

🌙(ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው ምንዳው ( ካስፈጠረው ሰው ጋር ተመሳሳይ ነው)

✨በዘይድ ብን ኻሊድ አል-ጁሃኒ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- ፆመኛን የስፈጠረ ሰው (ለአስፈጣሪው ሰው) የፆሚው ምንዳ ያህል ይኖረዋል ከፆመኛው ምንዳው ምንም ሰይቀንስ።

📚ቲርሚዚ ዘግበውታል እና ጥሩና ሳሂህ ሀዲስ ነው ብለዋል።

✨ይህ ሀዲስ ፆመኛን ማስፈጠር ጥቅም እና በዚህ ውስጥ ትልቅ ምንዳ እንዳለ እሱም ልክ እንደ ፆመኛው ምንዳ እንደሆን ያሳያል ምክኒያቱም ጾመኛ ክብር ይገባዋል እርሱን (ፆመኛን)መመገብ ሰደቃ ነውና ።

@sebil_tube
@sebil_tube


ረመዿን 6
🌙  نهار رمضان 🌙

🌟 የረመዿን የቀኑ ክፍል 🌟

ፆመኛ የሆነ ሰው  ፆሙን ለመጠበቅ ሲል በረመዿን የቀኑ ክፍል መስጅድ ውስጥ ሊያሳልፍ ይገባል መስጅድ በመሆኑ ፆሙን ከብዙ ነገሮች ይጠብቃል ለዚህም ነበር ቀደምቶቻችን ይህን የሚያዘወትሩት።

ኢብኑ አብዱልቀዊይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል:- 👇👇

🔹  "ከተገኘህበት መገኛ ሁሉ በላጩና የምታሸበረቅበት ቦታ እና ሁኔታ በመስጅድ ውስጥ አላህን እያወሳህ ስትገኝ ነው ከዚክሮች ሁሉ በላጩ ደግሞ ቁርዓን ነው ይህን ቁርዓን ስትቀራ ሁኔታህ ልክ ፈጣሪህን አረህማንን እያናገርክ  እንደሆነ ነው የሚታሰበው" 🔹

🔺 ለማንኛውም አንድ ዕውቀት ፈላጊም ሆነ በጥቅሉ ሁሉም ሙስሊም በዚህ ወር በይበልጥ ቁርዓንን አብዝተው ሊያነቡ ይገባል በሌላው ወርም እንዲሁ ሌላው  ልናስተውለው የሚገባው ጉዳይ ከእኛ ውስጥ ቁርዓንን ማንበብ ያልገራላቸው ማንበብ የማይችሉ ሙስሊሞች ይኖራሉ መፃፍም ማንበብም የማይችሉ ይኖራሉ የዚህን ጊዜ በቤት ውስጥ ቁርዓን ማንበብ የሚችሉ ልጆች ከወንድም ከሴትም ሞልተዋል ለአላህ ምስጋና ይገባውና ስለዚህ አባት ወይም እናት ልጆቻቸውን እስቲ አንብቡልኝ አንድ አንቀፅ አስተምሩኝ ማለት አለባቸው በያንዳንዱ ቀን አንድ አንቀፅ እየደጋገሙ ቢያነቡ እና ቢማሩ ትልቅ ነገር ነው አላህም በዚህ ላይ ያግዛቸዋል። | 📌

🔺ሌላው ትኩረት የሚያሻው አንድ ቃሪዕ አላህ ቁርዓንን ለማንበብ ያደለው ሰው እራሱን በአግራሞት እንዳይመለከት እና ሌላውን ማንበብ የማይችለውን ሰው የንቀት አስተያየት እንዳይመለከት ነው
ሰዎች በግዜ ከመስጅድ ሲወጡ እሱ በግልምጫ በንቀት ከመመልከት ይጠንቀቅ! በራሱ ከመገረም ይጠንቀቅ!
በራስ መገረም የባለቤቱን መልካም ስራዎች ጥርግርግ አድርጎ ያጠፋል አላህ ይጠብቀንና በጣም ከባድ ነው  በራሱ ስራ የሚደነቅ ሰው ስራውን ሊያበላሽ የቀረበ ሰው ነው። | 📌

🔺 ስንት እና ስንት ሰው አለ በመጀመሪያው የዕድሜ ዘመኑ ጥሩ ስራ ባለመስራቱ ምክንያት የሚፀፀት የሚያዝን የሆነ
በመጀመሪያው የዕድሜ ዘመን ላይ ዕውቀትን ከመውሰድ ይልቅ በኑሮ ውጣ ውረድ ላይ ሆኖ የቆየና አሁን ላይ በዚያ ነገር የሚፀፀት ሰው ቁርዓንን የዚያኔ ባለመማሩ የሚያዝን ሰው ከአንዳንድ ቁርዓንን ከተማሩ ቃሪዕ ከሆኑ ሰዎች የሚሻልበት ሁኔታ አለ ልቡ በማዘኑ!
ለዚህም ነው ቀደምቶች እንዲህ የሚሉት
ስንትና ስንት የተኛ ሰው አለ በመፀፀቱ ምክንያት አላህ ያዘነለት ስንትና ስንት ሰጋጅ አለ በራሱ ስራ በመገረሙ ምክንያት አላህ የነፈገው። | 📌


📚ምንጭ:-👇👇

🔈 [ 📚 ሸይኽ አብዱልከሪም አል-ኹደይር  አላህ ይጠብቃቸውና 📚 ]

@sebil_tube
@sebil_tube


ተሰሀሩ🗣 ፈኢነ ፊሱሁሪ በረካ


በኒያ ጉዳይ መጨናነቅ አያስፈልግም

ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

"ነገ ረመዷን እንደሆነ ያወቀና ሊፆመው የፈለገ ሁሉ ፆሙን ነይቷል።"

[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 25/215]


قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

«ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡

Al-A'raf 7:23

@sebil_tube


#ረመዳ_5 🌙


إِن تُقْرِضُوا اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا يُضَاعِفْهُ لَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ وَاللَّهُ شَكُورٌ حَلِيمٌ
17  التغابن
ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ (ምንዳውን) ለናንተ ይደራርበዋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህም አመስጋኝ ታጋሽ ነው፡፡
(ተጋቡን 17)

🌟                 💫
====================
Sebil_tube
@sebil_tube


ረመዿን 5
🌙 تفطير الصائمين 🌙

🌟 ፆመኞችን ማስፈጠር 🌟

🌺~ ልክ እንደዚሁ (ቀደምቶቻችን) ለረመዿን ከሚዘጋጁበት ነገሮች አንዱ ፆመኛን በማስፈጠር ላይ ነው ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው ምንዳው ያስፈጠረውን ሰው ምንዳ ፤ከእሱ ምንም ሳይቀነስ ማግኘት ነው።
ልክ እንደዚሁ (ቀደምቶቻችን) ራሳቸውን አላህን በማውሳት ላይ ይጠምዱ ነበር
በሌሎች ኢባዳዎች፣ ከነብያችን በተገኙ አዝካሮች ፤የጠዋት እና የማታ ዚክር፣ የመኝታ ዚክርን ይመስል እንዲሁም ከነብያችን በተገኙ በሆኑ ዱዓዎች በዚህ ምርጥ በሆኑ ወቅቶች አላህን ይለምኑት ነበር። በነዚህ ጊዜያቶች አላህ ለባሮቹ ስራቸውን እጥፍ ድርብ የሚያደርግበት ወቅት ስለሆነ ማለት ነው።
~ 🌺

አላህ ስለዚህ ወር ካወራ በኋላ እንዲህ ይላል፦

وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡


🌺~ ይህ ከአላህ የሆነ ቃልኪዳን ነው፤
እሱን ለጠየቀው ፣ለለመነው ባርያው ጥያቄውን ሊቀበለው እና የጠየቀውን እንደሚሰጠው ያረጋገጠበት ነው። ~🌺


📚ምንጭ:-👇👇

🔈 [ 💐 ሸይኽ አብደሏህ ኢብን ጀብሪን አላህ ይዘንላቸውና 💐]

@sebil_tube
@sebil_tube


ተሰሀሩ🗣 ፈኢነ ፊሱሁሪ በረካ


"وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ"

And He(Allah) is with you wherever you are.

እርሱም(አላህ) የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡

@sebil_tube
@sebil_tube


ረመዿን 4

🌙 فتحت أبواب الجنة 🌙

🌟 የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ 🌟

"ይህ የተባረከው ወር የሆነው የረመዿን ወር ከሌሎች ወሮች ልዩ እና በላጭ ከተደረገበት ነገሮች መካከል በዚህ ወር የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ አላህ ሆይ በውስጧ ከሚገቡት ባሮችህ አድርገን 'አሚን🤲'። 🍂

እንዲሁም የዕሳት በሮች ይዘጋሉ
በዚህ ወር መልካም ስራዎች ስለሚበዙ እና መጥፎ ስራዎች ስለሚያንሱ ማለት ነው። 🍂

ወንድሜ ሆይ! በዚህ በተባረከ ወር ላይ መልካምን ስራ አብዝቶ በመስራት ላይ በርታ። 🍂

በሰላት፣ በዚክር፣ በሰደቃ፣ ለሰዎች በጎ በማድረግ በምትችለው ያህል ታገል
የአላህ መልዕክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ቸር ለጋሽ ነበሩ እጅግ በጣም ለጋሽ የሚሆኑት ደግሞ በረመዿን ወር ነበር። 🍂

ለአላህ ባሮች ቸር ሁንላቸው በመልካም ንግግር፣ በጥሩ ፈገግታ፣ እነሱን በማገዝ፣ በገንዘብ ለአላህ ባሮች ቸር የሆነ ሰው የአላህን ቸርነት ለማግኘት ቅርብ እና የተገባው እሱ ራሱ ነው።"
🍂

አላህ ያግራልን!🙏

📚ምንጭ:-👇👇

🔈  ( 💐ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ቢን ባዝ አላህ ይዘንላቸውና 💐)

@sebil_tube
@sebil_tube


ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡

አላህ እንዲህ ይላል፦ የአደም ልጆች ሥራቸው ሁሉ ለራሳቸው ነው። ፃሞ ብቻ ሲቀር ፃም የኔ ነው ምንዳውነም የምከፍለው እኔው ነኝ አለ።


۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡


[ ሱራ አል-ዙመር አንቀፅ 53 ]

ይሄን የቁርአን አንቀፅ እሰኪ ከፋፍለን እንመልከተው:-👇👇

1.ኛ 🌟" ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ "🌟 አላህ እንዲህ ማለቱ:-👇👇

ምንም ያህል የወንጀል ብዛት ቢኖርብን፤ እኔ ወንጀሎቼ ብዙ ናቸው አላህ አይምረኝም ብለን ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብን ያሳያል። 🍂

2.ኛ 🌟 "በእርግጥ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና" 🌟

አንድ ሰው በእውነት ከልቡ ወደ አላህ ከተመለሰ (ተውባ) ካደረገ ወንጀሉ ምንም ያህል የበዛ እና የከፋ (የገዘፈ) ቢሆንም አላህ ወንጀሎቹን ሁሉ (ትንሽም ትልቅም) ይሁን ይምርለታል። 🍂

4.ኛ 🌟 " እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና " 🌟

አላህ መሐርታው የሰፋ እና እዝነቱ ገደብ የሌለው መሆኑን ያሳያል። እናም ያንተ ወንጀል ምንም ያህል የበዛ እና የገዘፈ ቢሆንም ከአላህ ሰፊ መሓርታ እና ገደብ የለሽ እዝነት በፍፁም አይበልጥም።
🍂

📌 | የዚህ የቁርአን አንቀፅ ቱሩፋቶች | 📌

👉 ለእያንዳንዱ ወንጀለኛ ትልቅ ተስፋን ትሰጣለች:- አንድ ሰው ምንም ያህል ወንጀለኛ ቢሆን የአላህ መሐርታና እዝነት ሁሌም ክፍት እንደሆነ ታሳያለች። 🍁

👉 ወደ አላህ እንድንመለስ (ለተውባ) ታነሳሳናለች :- ሰዎች ከሰሩት ወንጀሎች ተቆጥበውና ተፀፅተው ከልባቸው ወደ ጌታቸው እንዲመለሱ ታነሳሳለች። 🍁

👉 አላህ ለባሮቹ የለውን ፍቅርና እዝነት ታሳያለች :- አላህ በዚህ አንቀፅ ውስጥ ኃጢአተኞችን እንኳን ወደ እራሱ አስጠግቶ " ባሮቼ ሆይ!!" ብሎ ነው የጠራቸው ይህም አላህ ለባሮቹ ያለውን ወደር የለሽ ፍቅር እና እዝነት ያሳያል። የባሮቹ ሁኔታ ምንም ቢሆንም። 🍁

👉 የአላህ መሓርታ ገደብየለሽ መሆኑን ያሳያል:- አንድ ሰው ምንም ያህል ወንጀል ሰርቶ ከመሞቱ በፊት ወደ አላህ ከተመለሰ አላህ ወንጀሎቹን ሁሉ እንደሚምረው ታሳያለች። 🍁

👉 ተስፋ ከመቁረት ትጠብቃለች:- አንድ ሰው ምንም ወንጀል ሰርቶ ከወንጀሉ ብዛት ወይም ግዝፈት ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ እንደሌለበት ታስጠነቅቃለች ምክኒያቱም የአላህ እዝነት እና መሓርታ ከሱ ወንጀሎች የሰፉና የገዘፉ በመሆናቸው።
🍁

👉 ከዚህ የቁርአን አንቀፅ የምንማራቸው ነጥቦች :-👇👇

🔺 ከአላህ እዝነት በፍፁም ተስፋ አለመቁረጥ።

🔺 በእውነት ከልባችን ወደ አላህ ስንመለስ አላህ ይምረናል።

🔺 አላህ ወደሱ ከወንጀላቸው ተፀፅተው በእውነት ከልባቸው የተመለሱትን ፀፅት ወይም ንስሓቸውን (ተውባቸውን) ይቀበላል።

🔺 ሸይጣን ወንጀል እንድንሰራ ይጎተጉተናል ከዛም ተፀፅተን ወደ አላህ እንዳንመለስ ቢፈልግም አላህ ግን ሁሌም ተስፋ ሳንቆርጥ ወደ እሱ እንድመለስ (ተውባ) እንድናደርግ ይፈልጋል።

👉 የትኛውም ወንጀል አላህ መሓርታ እና እዝነት አይበልጥም።

ባጠቃላይ ይህ አንቀፅ ቁርአን ውስጥ ካሉ መልክቶች ውስጥ ትልቅ ተስፋን የሚሰት አንቀፅ ነው። ይህ አንቀፅ በሕይወት እስካለን ድረስ ከወንጀላችን ተመልሰን የአላህን መሓርታ ማግኘት እንደምንችል ያሳያል። እናም የአላህ ባሮች ሆይ ይህን ሰፊና ወደርየለሽ የአላህ መሓርታ እና እዝነት ተረድተን ወደ አላህ መመለስ ይኖርብናል። ረመዳን ደግሞ ለዚህ በጣም ምርጥ አጋጣሚ ነው። የረመዳንን ልዩ እድል ተጠቅመን ወደ አላህ መመለስ ይኖርብናል። ረመዳን ከተገኘባቸው ምክኒያቶች ውስጥ ራሱ አንዱ ወንጀላችንን ለማስማር ነው ስለዚህ ይህን ምርጥ አጋጣሚ ተጠቅመን ወንጀላችንን ከማስማር መቦዘን የለብንም።

ማስጠንቀቂያ!!🫵‼️‼️

አላህ መሓሪ ነው እያልን እያወቅን ወንጀል ውስጥ በተደጋጋሚ መዘፈቅ ሌላ ከባድ ወንጀል ከመሆኑም ባለፈ አደብ ማጣትና አላህን መናቅ ነው ስለዚህ በጣም ልንጠነቀቅ ይገባል። አላህ አዛኝ እና መሓሪ እንደሆነው ሁሉ ቅጣተ ብርቱም ነው የአላህ ቅጣት ደግሞ እጅግ በጣም የከፋ ነው። ከማን ጋር እየተሳፈጥን መሆኑንም ልብ ማለት ይገባናል‼️።

አላህ እንዲህ ይላል:-👇👇

۞ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡


وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ الْعَذَابُ الْأَلِيمُ

ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡

[ ሱረቱል ሒጅር አንቀፅ 49 ]

እንዲህም ይላል:-👇👇


فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُ أَحَدٌ

በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡


[ ሱረቱል ፈጅር አንቀፅ 25 ]

አላህ ባነበቡት ከሚጠቀሙት ያድርገን!አሚን!!🤲

ወሰላሙ አለይኩም ወረሀመቱላሂ ወበረካቱህ 👋


@sebil_tube
@sebil_tube

Показано 20 последних публикаций.