ሰሌዳ | Seleda


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ @Contact_officework ያናግሩን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


☄️"የፈጠራ ክስ ቀርቦብኛል"- ኤርትራ❗️


ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ገብተው ጥቃት እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ያቀረበባትን ክስ ኤርትራ አስተባበለች።


የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገ/መስቀል በx ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አውሮፓ ህብረት እና ተመድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ተመሳሳይ እና የፈጠራ ክስ በኤርትራ ላይ መስርቷል ሲሉ ገልፀዋል።


በጄኔቫው ስብሰባ ላይ ኤርትራ በትግራይ ክልል ወረዳዎች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀመች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡


ይሁንና ኤርትራ ክሱን የፈጠራ ክስ ነው ስትል አስተባብላለች።

@seledadotio
@seledadotio


☄️ኢትዮጵያና ሶማሊያ የባህር በር ውዝግብን በሰላም ለመፍታት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሶማሊላንድ ወደብ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸውን አስታዉቀዋል።


የሁለቱ አገራት መሪዎች በቱርክ አደራዳሪነት ባደረጉት ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሉዓላዊነት ውስጥ በመሆን የባህር በር ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ተጠቃሚነት ያለው የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማምተዋል።


ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሞቃዲሾን ጎብኝተው ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጋር ተወያይተዋል።

በስብሰባው አጀንዳ ቀዳሚው የዓፍሪካ ቀንድ ደህንነት እንዲሁም ባለፈው ታኅሣሥ በአንካራ እንደተስማሙት የኢትዮጵያ ወደብ ተደራሽነት የቴክኒክ ድርድር መጀመር እንደነበር ተጠቁሟል።


የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ዑመር አሊ እንዳስታወቁት፣ ድርድሩ ቀጥሏል፤ ግቡም እስከ ሰኔ ወር ድረስ የአሠራር ማዕቀፍ ላይ መድረስ ነው።


ይህ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ የምትጠቀምበትን ወደብ፣ የሚገኝበትን ቦታና ወጪውን ይወስናል።


ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን በሰላማዊ መንገድ እንድታሳካ ትልቅ እድል የሚፈጥር ነው።


ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ በኩል የባህር በር ለመጠቀም ያደረገችው ጥረት ውዝግብ አስነስቶ ነበር።


አሁን ግን ሁለቱ አገራት በመደራደርና በመስማማት የጋራ ጥቅምን ለማስጠበቅ ቁርጠኝነታቸውን ማሳየታቸውን ዘ ማሪታይም ኤክስኪዩቲቭ ዘግቧል ።


ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ የባህር በር አልባ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የራሷን የባህር በር ለመገንባት ጥረት ስታደርግ ቆይታለች።

ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያግዝና በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@seledadotio
@seledadotio


❗️ብሄራዊ ባንክ አዲስ ህግ አጸደቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አነስተኛና አዲስ የተቋቋሙ የፋይናንስ ድርጅቶች በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ቅርንጫፍ እንዳይሠሩ የሚያግድ ረቂቅ መመሪያ አወጣ።

ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ውሳኔ በባንኮች መካከል ውህደትን ለማበረታታት ሰፊ ስትራቴጂ አካል ነው

@seledadotio
@seledadotio


⚡️የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ያበሻቀጡት የአሜሪካው ም/ፕሬዚደንት ጄዲ ቫንስ ቤተሰብ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩክሬን ደጋፊ ተቃዋሚዎች የቬርሞንት የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያውን ካጨናነቁ በኋላ ወደ 'ያልታወቀ ቦታ' ተዛውረዋል።

JD Vance family moved to ‘undisclosed location’ after hundreds of pro-Ukraine protesters swarm Vermont vacation resort

@seledadotio
@seledadotio


❗ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እኔን መተካት ከባድ ነው አሉ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሀገራቸው የኔቶ አባል ከሆነች በምትኩ ስልጣን እንደሚለቁ ተናግረዋል

የአሜሪካ ፖለቲከኞች ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለቦታው አይመጥኑም የሚል ሀሳቦችን እያንሸራሸሩ ይገኛሉ

@seledadotio
@seledadotio


ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ ይጠበቅባቸዋል ተባለ

ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉም ተነግሯል

የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክስዮን ማህበር ከዛሬ የካቲት 24 ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ወይዘሮ እስራኤል ወልደመስቀል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የመንገደኞችን እንግልት ለመቀነስና ለጋራ ደህንነት መንገደኞች ከዛሬ ጀምሮ የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በመቁረጥ አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል።

ማህበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ዲጂታላይዝድ ማድረጉን የገለጹት ባለሙያዋ፤ ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉም ተናግረዋል።

ይህንንም ለደንበኞች የማሳወቅ ሥራው ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ሲሰራ እንደነበርና ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር መታወቂያውን እንዲያገኙት እየተደረገ እንደነበር አስታውሰዋል።

የብሔራዊ መታወቂያ ተግባራዊነቱ ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ብቻ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ተጠቃሚዎች ፓስፖርታቸውን በመጠቀም ትኬት ማግኘት እንደሚችሉ ወይዘሮ እስራኤል ገልጸዋል።

በኦንላይን ትኬት የመቁረጥ አገልግሎት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል።


ፒያሳ❗️ፒያሳ❗️ፒያሳ❗️ፒያሳ
   ጊወርጊስ አደባባይ ፊትለፊት

#ቴምር ሪልስቴት(የንግድ ሱቅ)
4,235ካሬ ላይ ያረፈ ግዙፍ የገበያ ማዕከል በ18ወር የሚረከቡት ከ20ካሬ ጀምሮ የንግድ ሱቆች በሽያጭ ላይ ነን

የ20ካሬ ሱቅ ጠቅላላ ዋጋ👇👇👇
🏪4th & 5th floor=3,900,000ብር
  ቅድመ ክፍያ=900,000ብር
🏪3rd Floor=4,200,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=1,200,000ብር
🏪2nd Floor=4,800,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=1,500,000ብር
🏪1st Floor=5,500,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=2,000,000ብር
🏪Ground Floor=7,000,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=2,800,000ብር

#ቴምር ሪልስቴት(አፓርታማ)
🎅ፒያሳ ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ፊትለፊት(ሊሴ ት/ቤት ጀርባ) አፓርታማ ሽያጭ

🧲66ካሬ-142ካሬ(1መኝታ-3መኝታ) 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪ ክፍያ በ18ግዜ ዙር በ3አመት ተከፍሎ ይጠናቀቃል

👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል!!
❗️በኢትዮጵያ ብር ብቻ የሚዋዋሉት!!!
    
    ፈጥነው ይደውሉ
   📞+251926172402 / +251951513585

#temerrealestate #apartment #AddisAbabaApartments #realestateinethiopia


⚡️አውሮፓ የሩሲያን ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ 1000 የኑክሌር አረሮች ያስፈልጓታል ተባለ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ለአውሮፓ የሰጡትን የደህነት ዋስትና ያነሳሉ የሚለው ስጋት አውሮፓውያን ከአሜሪካ ነጻ ሆነው ራሳቸውን የሚከላከሉበትን ለመቀየስ እየወያዩ ይገኛሉ።
@seledadotio
@seledadotio


ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት ያስተላለፈው መልዕክት።

@seledadotio
@seledadotio


❗️የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለእስራኤል የ4 ቢሊዮን ወታደራዊ እርዳታ በአስቸኳይ እንዲደርሳት ማዘዛቸውን ገለጹ

የትራምፕ አስተዳደር በቅርብ ሳምንታት ውስጥ መሳሪያዎችን በፍጥነት ለእስራኤል ለመሸጥ የአስቸኳይ ጊዜ ስልጣን ሲጠቀም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል።

@seledadotio
@seledadotio


⚡️ በአዲግራት የመሬት መንቀጥቀጥ


ከአዲግራት ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ ርዕደ መሬት ተከሰተ

ዛሬ እሁድ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ላይ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ።


ርዕደ መሬቱ የተከሰተው ከቀኑ 5 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ላይ መሆኑንም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአፋር ክልል ባሉ አካባቢዎች ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰትም፤ በትግራይ ክልል ከተሞች አቅራቢያ ርዕደ መሬት ሲመዘገብ ግን በዚህ ዓመት የመጀመሪያው ነው።

የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ቀጠና የተከሰተ መሆኑን የጠቆመው የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC)፤ መጠኑም በሬክተር ስኬል 5.3 የተለካ እንደሆነ አስታውቋል።

በኤርትራ ከአንድ ሳምንት በፊት የደረሰ ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 4.6 ሆኖ ተመዝግቧል። የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በቀይ ባህር ሰሜናዊ አቅጣጫ ከአስመራ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ አካባቢ ነበር።

በሀገሪቱ ባለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽም እንዲሁ ተመሳሳይ ርዕደ መሬት ተመዝግቧል።

በሐምሌ 2015 ዓ.ም. በኤርትራ ባህር ዳርቻ ዳህላክ ደሴት አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተደጋጋሚ ንዝረቶች አስከትሎ እንደነበር ይታወሳል።

ንዝረቱን በሽሬ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም እና መቐለ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች መስማታቸውን በወቅቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸው ነበር::

@seledadotio
@seledadotio


📣‹‹ጣሊያን በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ!››


ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፣ ባሕር ተሻግሮ ድንበር አቋርጦ የመጣውን ወራሪውን የጣሊያን ሠራዊት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በዓድዋ ጦርነት ድል ማድረጋቸውን አስመልክቶ በወሩ መጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን ከጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ የተገኘ ኃይለ ቃል ነው፡፡

ከ129 ዓመታት በፊት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም.፣ (በአውሮፓዎቹ ቀመር ማርች 1 ቀን 1896) ኢትዮጵያ የነጩን ዓለም ያናወጠ፣ ለጥቁር ሕዝቦች ሞገስ የሆነውን የዓድዋ ጦርነት በጣሊያን ወራሪ ሠራዊት በድል የተወጣችበት ዕለት ነበር፡፡



ይህንን የ19ኛው ምዕት ዓመት ታሪካዊ ገድል ነበር ጆርጅ በርክሌ በመጣጥፉ ያንፀባረቀውና “አጤ ምኒልክ” ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ ያሠፈረው፡፡



ይኸው የዓድዋ ጦርነት ድል 129ኛ ዓመት እንደወትሮው በብሔራዊ በዓልነት ዛሬ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ከዓድዋ እስከ አዲስ አበባ አገሪቱን አቅፎ እየተከበረ ይገኛል፡፡

@seledadotio
@seledadotio


⚡️"የገሃነም በሮች የሚከፈቱበት ጊዜ አሁን ነው

መብራት እና ውሃ ማቋረጥ፣ ወደ ጦርነት መመለስ - "

የእስራኤል የቀድሞ ባለስልጣን ቤን ጊቪር ወደ ጋዛ ከበባ ፈጣን እና ጭካኔ የተሞላበት መመለስን ደግፈው ተናገረዋል።


Time to open up GATES OF HELL, cut off electricity and water, return to WAR — Israeli ex-official Ben Gvir advocating a swift and brutal return to Gaza siege

@seledadotio
@seledadotio


ፒያሳ❗️ፒያሳ❗️ፒያሳ❗️ፒያሳ
   ጊወርጊስ አደባባይ ፊትለፊት

#ቴምር ሪልስቴት(የንግድ ሱቅ)
4,235ካሬ ላይ ያረፈ ግዙፍ የገበያ ማዕከል በ18ወር የሚረከቡት ከ20ካሬ ጀምሮ የንግድ ሱቆች በሽያጭ ላይ ነን

የ20ካሬ ሱቅ ጠቅላላ ዋጋ👇👇👇
🏪4th & 5th floor=3,900,000ብር
  ቅድመ ክፍያ=900,000ብር
🏪3rd Floor=4,200,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=1,200,000ብር
🏪2nd Floor=4,800,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=1,500,000ብር
🏪1st Floor=5,500,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=2,000,000ብር
🏪Ground Floor=7,000,000ብር
   ቅድመ ክፍያ=2,800,000ብር

#ቴምር ሪልስቴት(አፓርታማ)
🎅ፒያሳ ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ፊትለፊት(ሊሴ ት/ቤት ጀርባ) አፓርታማ ሽያጭ

🧲66ካሬ-142ካሬ(1መኝታ-3መኝታ) 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪ ክፍያ በ18ግዜ ዙር በ3አመት ተከፍሎ ይጠናቀቃል

👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል!!
❗️በኢትዮጵያ ብር ብቻ የሚዋዋሉት!!!
    
    ፈጥነው ይደውሉ
   📞+251926172402 / +251951513585

#temerrealestate #apartment #AddisAbabaApartments #realestateinethiopia


❗የውጭ ዜጋ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ሕግ እየተዘጋጀ ነው

የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የገንዘብ እርዳታ ካቆመ ወዲህ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች መካከል 85 በመቶዎቹ ሥራቸውን ማቆማቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

በተለይ በሰብዓዊ መብቶች፣ በሰላም፣ በጤና እና ልማት ዘርፎች የሚሠሩ ድርጅቶች ይበልጥ ተጎጂ እንደኾኑ የጠቀሰው ዘገባው፣ በትግራይ ለ100 ሺሕ የጦርነት ተፈናቃዮች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያቀርብ የነበረ መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅትም ሥራ ማቆሙን አመልክቷል።

መንግሥትም፣ የውጭ ዜጋ የሆኑ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ሕግ እያዘጋጀ መኾኑን ምንጮች መናገራቸውን የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል።

@seledadotio
@seledadotio


ዓድዋ‼️

"ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!"
እንኳን ለ129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ -አደረሰን!

@seledadotio
@seledadotio


❗ግብፅ ኢትዮጵያ የባህር ሃይል እንድታቋቁም አልፈቅድም አለች

ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር የራሷን ወደብ ለማግኘት እና የባህር ሀይል ለመቋቋም እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል።

ግብጽ የቀይ ባህር አካል ያልሆነ ማንኛውም ሀገር በባህሩ ዙሪያ የሚያደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የባህር ሀይል ለማቋቋም የሚደረግ ጥረት እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡

ይህ የተባለው በግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዳላቲ የተመራ ልዑክ በኤርትራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት የቀይ ባህርን ጨምሮ የጋራ በሚያደርጓቸው ቀጠናዊ እና በተለያዩ መስኮች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ተስማተዋል፡፡

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር “የቀይ ባህር ደህንነት በተዋሳኝ ሀገራቱ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው ፤ምንም አይነት ወታደራዊም ሆነ የባህር ሃይል በአካባቢው መገኘትን አንፈቅድም” ብለዋል።

አክለውም “ወደብ አልባ ሀገራት በቀይ ባህር ዙሪያ የባህር ሀይል ማቋቋም የቀጠናውን እና የባህሩን ደህንነት ለመጠበቅ የተደረሰውን ስምምነት ክፉኛ የሚጎዳ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ እንዳስታወቀው አብዳላቲ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በአህጉራዊ የጋራ ጉዳዮች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምና ደህንነትን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፣ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እና ሉዓላዊነቷን በሁሉም ግዛቶቿ ላይ ለማስረፅ የሚያስችል የሃሳብ ልውውጥ ተካሂዷል።

ስብሰባው በሊቢያ እና በአፍሪካ ሳህል
አካባቢ ስላለው ሁኔታ እንዲሁም በቀይ ባህር ውስጥ ያሉ ለውጦች እና ማንኛውም ቀይ ባህር አካል ያልሆነ መንግስት በፀጥታ እና በአስተዳደር ውስጥ ተሳትፎን ውድቅ በማድረግ ላይ ትኩረቱን አድርጓል ።

በተጨማሪም በጥቅምት 2024 በኤርትራ ከተካሄደው የመጀመሪያው የመሪዎች ጉባኤ በኋላ ተመሳሳይ የሚኒስትሮች ስብሰባዎችን በሞቃዲሾ እና በአስመራ ለማካሄድ እና በቅርቡ ለሁለተኛው የፕሬዝዳንት ጉባኤ ለመዘጋጀት መምከራቸውን አብዳላቲ ጠቁመዋል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በበኩሉ ትላንት ምሽት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዳላቲ ከተመራ ልዑካን ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይቶች ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡

በሱዳን ሶማሊያ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በቀይ ባህር አካባቢዎች የሰላም እና የደህንነት ፈተናዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት መካሄዱንም መግለጫው አክሏል፡፡

@seledadotio
@seledadotio


⚡️ኢለን መስክ ለ14ኛ ጊዜ የልጅ አባት

የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኢለን መስክ ሰዎች ብዙ ልጆችን እንዲወልዱ በማበረታታት ይታወቃል

ባለጸጋው ከአራት ሴቶች የተወለዱ የ14 ልጆች አባት ነው ተብሏል

@seledadotio
@seledadotio


❗ዘሌንስኪ “በዋይት ኃውስ ቆይታ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ምንም ስህተት አልሰራንም” አሉ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከዶናልድ ትምፕ ጋርሀይለ ቃል የተቀላቀለበት ክርክር ከተለዋወጡ በኋላ ውይይቱ ተቋርጡ ከዋይት ኃውስ ሲወጡ ታይተዋል።

ከውይየቱ በኋላ ከፎክስ ኒውስ ጋር ቆይታ ያደረጉት ዘሌንስኪ ትምፕን ይቅርታ ይጠይቃሉ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ትራምፕን የምጠይቀው ይቅርታ የለም” ብለዋል።

“ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ለአሜሪካ ህዝብ ክብር አለኝ” ያሉት ዘሌንስኪ፤ ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ግን በጣም እዚህ ጋር በጣም ግልጽ እና ሐቀኛ መሆን ያለብን ይመስለኛል፣ ይቅርታ ሊያስጠይቅ የሚደረስ ምንም መጥፎ ነገር ያደረግን አይመስለኝም” ብለዋል

@seledadotio
@seledadotio


⚡️የአማራ ክልል የ102 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ያስፈልጋል

የአማራ ክልላዊ መንግሥት፣ በአውሮፓዊያኑ 2025 ለሰብዓዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች 102 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ትናንት ከዓለማቀፍ አጋሮች ጋር በተደረገ የምክክር መድረክ ላይ መግለጡን ዶቸቨለ ዘግቧል።


ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁንም በሚካሄደው ጦርነት ሳቢያ 6 ሺሕ154 ትምህርት ቤቶች እንደወደሙ የክልሉ መንግሥት በመድረኩ ላይ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።


የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ በክልሉ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዕርዳታ ፈላጊ ሕዝብ እንደሚገኝም በመድረኩ ላይ ገልጧል ተብሏል።

ከአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት ሰብዓዊ ዕርዳታ ያገኙ የነበሩት ዋግኽምራ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ባኹኑ ወቅት ዕርዳታው እንደተቋረጠባቸው ኮሚሽኑ ማስታወቁንም የዜና ምንጩ ዘገባ አመልክቷል።

@seledadotio
@seledadotio

Показано 20 последних публикаций.