ሀዘን!
ወደ ሰፈር ስገባ የሰፈር ሰዎች በደሞና በገሶ የተቆለለውን የአፈር ክምር ይንዳሉ። የተናደውን አፈር በአካፋው የውሃ መውረጃ ቦዩ ላይ በማደበርያ እየጫኑ ይደፍናሉ፤ ጭቃ ቦታው ላይ ደሞ በቆሙበት ቦታ ላይ ሆነው አፈር እየወረወሩ ጭቃውን ያለብሳሉ። ጓደኛዬ ከጠወተ በኋላ ደጀ ሰላም እንድንሄድ ጠርቶኝ ሄጄ፤ ወደ ሰፈር ስመለስ ያልተለመደ እንቅስቃሴ ሰፈር ውስጥ ሳይ ምን ተፈጠረ ብዬ ክው አልኩኝ። ረሃብ እየፈጀኝ እንዳልነበረ፤ የረሃብ ወስፋቴ በአንዴ ተቆለፈ! የውሃ መውረጃው ቦይን በአፈር የሚደፍኑት ልጆች ጋር እያማጥኩ ደርሼ "ምን ተፈጥሮ ነው አልኳቸው"? ልጆቹም በሆነው ነገር ተደነጋግጠዋል! ለእኔ ለመንገር እየተርበተበቱ "ጋሽ! ጋሽ፣ ጋሽ ...... አደላ ሞቱ አሉኝ"። ደነገጥኩኝ። የምለው ጠፋኝ? ሰሞኑን አሟቸው ሀኪም ቤት እየተመላለሱ ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን ባውቅም። ከግቢያቸው ውስጥ "አባቴ፣ አባቴ፣ ወይኔ አባዬ" የሚል የአልቃሽ ድምፅ ይሰማል። ከድንጋጤ ሳልመለስ አፈሩን ንደው የሚያስተካክሉት ልጆች ጋር ደርሼ፤ ሰላም ባልሆነበት ቦታ ሰላምታ አቀረብኩላቸው .....
ሰፈሩ በለቀስተኞች ድምፅ ከደቂቃዎች በኋላ ተሞላ። "ወይኔ አጎቴ, አጎቴ, አጎትዬኤኤ፣ መካሪዬ, መካሪዬ, መካሪዬኤኤኤ፣ ጓዴ, ጓዴ, ጓዴኤኤኤ፣ ጠያቂዬ, ጠያቂዬኤኤ፣ ወንድሜ, ወንድሜኤ..., የእናቴ ልጅ, የእናቴ ልጅእእ፣ ጎረቤቴኤኤ..., ጎረቤቴኤ...፣ አጫዋቼኤኤ, አጫዋቼኤኤኤ...፣ አለሁልሽ ባዬኤ..., አለሁልሽ ባዬኤ..., ሚስጢረኛኤኤ, ሚስጢረኛኤ..." በማለት በነዚህ የሀዘን እንጉርጉሮ ሰፈሩን አደበላለቁት። ጋሽ አደላ ልክ እንዳሏቸው ሰው ነበሩ። ትንሽ ትልቅ ሳይለዩ መካሪ፣ ዘመድ ከባዳ ሳይለዩ ጠያቂ፣ ደምን ሳይለኩ ወንድም፣ ሀብት ንብረት ሳያዩ ደራሽ፣ ዘር እምነት ሳይለዩ ጎረቤት። ልጆቻቸው፣ የልጅ ልጆቻቸው፣ ያሳደጓቸው የሰፈር ልጆች፣ የእህቶቻቸው ልጆች፣ ጎረቤቶች፣ የሰፈር ሰዎች፣ ዕድርተኛ፣ ማህበርተኛ በአጠቃላይ ሁሉም ሰው በበራቸው ደጃፍ ላይ አረገደላቸው። ይገባቸዋልም።
በማግስቱ ግብዓተ አፈራቸው የሚካሄድበት የመቃብር ስፍራ ላይ መሸኛ ሙሾ አወረዱላቸው፣ ደረት ደቁላቸው፣ እንባ አፈሰሱላቸው፣ ፀጉር ነጩላቸው ,..........., እነሱ ግን በተገነዙበት ሰሌን ተጠቅልለው እንዳሉ አፈር አለበስናቸው። ይሄኔ ከዐይኔ እንባ ፈሰሰ፣ ከአንደበቴ ሙሾ ወረደ፣ ደረቴን ደቃው። የሚለብሳቸውን አፈር መሆን ተመኘው፣ የተከፈኑበትን ሰሌን አለመሆኔ ቆጨኝ፣ የተቆፈረላቸውን ጉድጓድ መተናነሴ አናደደኝ። እንዲ አልኩሏቸው ወይኔ ሚስጢሬ, ሚስጢሬ፣ ወይኔ ዕውቀቴ, ዕውቀቴ፣ ወይኔ ትዳሬ, ትዳሬ፣ ወይኔ ........ በማለት ሀዘኔን ለቀኩት!
የያዙትን የአነዋወር ሚስጢር ለማንም ሳያካፍሉ ይዘው በማለፋቸው፣ የያዙትን ትልቅ መድኋኒት የመቀመም ዕውቀት ደብቀው በሞሞታቸው፣ አባት ሆነው በየቤቱ ነጠላውን ጥንድ፣ የተፋቱትን፣ የተኳረፋትን፣ የተጣሉትን አስታርቀው ቤተሰብ የማፅናት ብልዐት ከራሳቸው ጋር ሸጉጠው እንዲሄድ ሳላደረጉ አነባው፣ ደረት ደቃው። ለቀስተኞቹ እነዚህን ነገሮች ይወቁ፣ አይወቁ ባልረዳም!?። ለቀጣይ ትውልድ መተላለፍ ሲኖርባቸው ያልተላለፋትን ጥበቦች በማሰብ በሀዘን ተዋጥኩኝ። ለወራት ማቅ ለብሼ መቃብራቸው ጋር ተመላለስኩ፣ ፊቴ ከሰለ፣ አጥንቴ ወጣ። አንዴ ወደ ወዲያኛው ከነባለቤቱ ሄደዋልና ከማዘን በቀር ምንም ነገር ማምጣት አልቻልኩም። ያን ሰሞን ከዘመድ አዝማድ የበለጠ ሀዘን ገረፈኝ!
#ከምህረትዬ B.
#23,1,2013 አዳማ!
#ማስታወሻነቱ ለጋሼ!