" አለና እግዚአብሄር ከአላህ ለይፈለና"!
መቐለ ከተማ ከሚገነቡት አዳ'ዲስ ሰፈሮች መሃከል አንዱ የነቁሬ ሰፈር ነው። ቤቶቹ በአዳዲስ ዲዛይን አንዳንዶቹ ተሰርተው አልቀዋል፤ አንዳንዶቹ እየተሰሩ ናቸው። እንደ ቤቶቹ አዲስነት ሁሉ ነዋሪዎቹም በሚመሳሰሉት ዓይነት እርስ በራሳቸው አዲስ ጉርብትና በመመስረት ተመዳድበዋል። አብዛኛው ጉርብትናቸውን የቦደኑት በሃይማኖትና በመጡበት አካባቢ መሰረት ነው።
ወደ ሰፈሩ ከሚያስገቡት ሶስት አቅጣጫዎች መሐከል ቁሬ በስተምስራቅ ያለው መንገድ ላይ አንድ ጤና ጣቢያ ጥግ ስር ኬሻ ከልሎ ነው የሚኖረው። ቁሬ በሰፈሩ ሰው ታዋቂ ነው። የሚኖርባትን የኬሻ ዳስ ደጃፍ ላይ በበዙት የሲጋራ ቁሪዎች አማካኝነት ስሙን ከ'መሃሪ' ወደ 'ቁሬ' መለወጣቸው አንዱ ማሳያ ነው። ከዚህ ሌላም የሰፈሩን ሰው ቆሻሻ እሱ ነበር የሚደፋላቸው፤ ቆሻሻ አንሺ ማህበራት ሳይመጡ በፊት። ሁሉም የሚስማሙበት ቁሬን ለየት የሚያደርገው ግን የ'ሱ ብቻ በሆነው ልዪ ሰላምታው ነው።
.
.
.
ክርስቲያን ሆነ ሙስሊም፣ አማኝ ሆነ ኢ-አማኝ፣ ትልቅ ሆነ ትንሽ፣ ሀብታም ሆነ ድሃ፣ ቀይ ሆነ ጥቁር፣ ከዚህ መጣ ከዛ ... ሳይለይ በቀኑ ውስጥ ከብዙ ነዎሪዎች ጋር ሰላምታ ይቀያየራል።
በየቀኑ ቁሬ በሚገኝበት መንገድ የሚያልፉ ሰዎች ሰላምታቸውን እንዲህ በማለት ለቁሬ ያቀርባሉ፤ እሱ በሚመልሰው መልስና እንቅስቃሴ ለመዝናናት "ቁሬ ሰላም ዶ"( ቁሬ እንዴት ነህ) ብለው ሰላምታቸውን ያቀርባሉ። ቁሬ እያጨሰ ያለውን ሲጋራ ከከንፈሮቹ መሃል አንስቶ "አለና! እግዚአብሔር ከአላህ ለይፈለና"('አለን እግዚአብሄር ከአላህ ሳንለይ!'' ይላቸዋል፤ በሲጋራ ምክንያት የዛገ ብረት በመሰለው ጥርሱ ደስታ በተሞላው ፈገግታ እየተቀበላቸው። ለምላሹ ማድመቂያ የቀኝ እጁን በሰላምታ ምልክት እያውለበለበ፤ ከወገቡ ጎንበስ፣ ቀና እያለ። እነሱም በምላሹ እያሳቁ "ንበር ንበር" (ኑር ኑር) ብለውት ሌላ ምላሽ እንደሌለው ሰለሚያውቁ፣ ለቀጣይ ሰላምታ አቅራቢ መንገደኞች ቁሬን ትተው መንገዳቸውን ............!!
እኔ ግን ሁሌ ቁሬ "አለና እግዚአብሄር ከአላህ ለይፈለና" ባለኝ ቁጥር በሃይማኖቴ አሳብቤ የተለያየዋቸው፣ የተለያዩኝ ወዳጆቼ፣ ጓደኟቼ በአጠቃላይ የሰው ዘር ፊቴ ይደቀናል።
እኔ ግን ሁሌ እግዚአብሄር ከአላህ ለይቼ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ ቤተሰብ ለማፍራት የማደርገውን አካሄዴን እንድመረምር ያደርገኛል።
እኔ ግን ሁሌ እግዚአብሄር ከአላህ ለይቼ ለሰዎች ሰላምታ አቀራረቤን ያስታውሰኛል።
እኔ ግን ሁሌ እግዚአብሄር ከአላህ ለይቼ .................... ያስታውሰኛል??
.
.
.
እናንተስ እግዚአብሄርን ከአላህ ለይታቹ ምን አደረጋቹ፣ ምንስ እያደረጋቹ ይሁን .............??
ለማንኛውም ቁሬ ምን ሊለን ይሁን "አለን እግዚአብሄር ከአላህ ሳንለይ" እያለ ለሰላምተኛው ሚመልሰው ወዳጆቼ????
# ከምህረትዬ B.
# 14,2,2014 ዓ.ም
#ማ. ለክብሮም ለገሰ።