እውነተኛ መረጃዎች ብቻ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ስላም ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ይህ ለናንተ ይሆናሉ ያልኳቸውን ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃዎች የማደርስበት ቻናል ነው።
ማንኛውንም አስተያየት ለመስጠት እና እንዲስተካከል የምትፈልጉት ነገር ሲኖራችሁ @ethiopian_fact_news ላይ ሃሳባችሁን መላክ ትችላላችሁ ።ሰላም ከናንተ ጋር ትሁን።

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: کانال رسمی آیگرام
igram_plusV4.2.1.apk
18.5Мб
2⃣ آیگرام پلاس نسخه 4.2.1

دانلود از کافه بازار:
https://cafebazaar.ir/app/org.telegram.igram.plus/


Репост из: کانال رسمی آیگرام
igram3(V4.2.1).apk
18.5Мб
3⃣ آیگرام سوم نسخه 4.2.1


የዛሬ ሐሙስ ታሕሳስ 9/2012 ዐበይት ዜናዎች

1) የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የወላይታን ክልልነት ጥያቄ ለማፈን የመከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ወደ ዞኑ እየገባ ይገኛል ብሏል ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ፡፡ በዞኑ ግጭት ቢፈጠር ተጠያቂው መንግሥት ይሆናል፡፡ ወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ለደቡብ ክልል ካቀረበ ነገ ዐመት ይሞለዋል፡፡ እናም ሕገ መንግሥቱ ባለመከበሩ መንግሥት ለወላይታ ክልልነት ባስቸኳይ ዕውቅና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ በተያያዘ፣ ዛሬ በሶዶ ከተማ የባጃጅ ሹፌሮች ጥያቄውን በመደገፍ ሰልፍ አድርገዋል፡፡

2) የቻይናዋ ሃንዥ ግዛት ልዑካን ቡድን ወደ መቀሌ እንዳይጎዝ መከልከሉን የትግራይ መገናኛ ብዙኻን ዘግቧል፡፡ ቡድኑ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የተመለሰው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው ተብሏል፡፡ የክልሉ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አብርሃም ተከስተ ወደ አዲስ አበባ ሂደው ከቡድኑ ጋር የማዕድን፣ ቱሪዝምና ግብርና የትብብር ስምምነቶችን ፈርመዋል፡፡ የትኛው የመንግስት አካል እንደከለከለ ግን ገና አለመታወቁን ሃላፊው ተናግረዋል- ብሏል ዘገባው፡፡

3) በዚምባብዌ የኢትዮጵያ ኢምባሲ 19 ኢትዮጽያዊያንን ዛሬ ከዛምቢያ እስር አስፈትቶ ወደ ሀገራቸው እንደሚመልስ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በፌስቡክ ገጹ ካሰራጨው መረጃ ተመልክተናል። እስረኞቹ የሚፈቱት ለዛምቢያ ጭምር የተወከለው የሐራሬው ኢምባሲ ከዛምቢያው ፕሬዝዳንት ጋር ባደረገው ስምምነት ነው። ኢምባሲው ሌሎች 25 እስረኞችን ለማስፈታት ጥረት ላይ ነው ተብሏል፡፡

4) ኢትዮጵያ ነገ የመጀመሪያዋን ሳተላይት ታመጥቃለች፡፡ ሳተላይቷ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማለዳ 12፡21 ላይ ወደ ሕዋ የምትመጥቀው ከቻይና ሳተላይት ጣቢያ መሆኑን የመንግስት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡


ቦይንግ ኩባንያ በመጨረሻ የ 737 MAX አውሮፕላኖችን "ለግዜው" ማምረት አቁሟል!

ቦይንግ ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ባጋጠሙ ሁለት አደጋዎች ከ300 ሰዎች በላይ ህይወት የቀጠፈውን አውሮፕላን በያዝነው የፈረንጆች አመት መጨረሻ ላይ ወደ በረራ ለመመለስ ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ የበረራ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች በፍጥነት በመመለሱ ስላልተስማሙ ኩባንያው ከመጪው ወር ጀምሩ ምርቱን እንደሚያቆም አስታውቋል ።


“መጪው ምርጫ ሁከትን ሊያቀጣጥል ይችላል” - ክራይስስ ግሩፕ #Election2020

ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘንድሮ ይደረጋል የተባለዉ ምርጫ በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየውን ክፍፍል ሊያሰፋው እና ሁከትንም የበለጠ ሊያቀጣጥል እንደሚችል ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተሰኘው ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም አስጠነቀቀ። በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ከተባባሰ የኢትዮጵያ መንግስት መጪውን ምርጫ የሚያካሄድበትን ጊዜ እንዲያዘገይ ተቋሙ መክሯል።

ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ይህን ያለው የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 6 ባወጣው ዳሰሳ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ቀውስ አምጪ ሁነቶችን በመተንተን የሚታወቀው ይሄው ተቋም በኢትዮጵያ በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎችየሚታዩትን ሁከቶች የበለጠ ሊያባብስ እንደሚችል ተንብዩዋል።

(Deutsche Welle)


በሰርጋቸው ድግስ እዳ ጭንቀት የገቡት ሁለት ናይጀርያውያን ጥንዶች እራሳቸውን አጥፍተው ሞቱ ።

ከሁለት ሳምንት በፊት ጋብቻቸውን የፈፀሙት ናይጀርውያን ጥንዶች ለሰርጋቸው ድግስ ብዙ ብር በመበደራቸውና በዚህም ጭንቀት ውስጥ በመግባታቸው ስርጋቸው ባለፈ በሶስተኛ ቀን እራሳቸውን አጥፍተው ሞተው እንደተገኙ በናይጀርያ ተነባቢ የሆነው ቶማስማርሴሎ ብሎግ አስነብቧል።


3 ቢልየን ዶላር የሚያክል ገንዘብ እንዴት ለኢትዮጵያ ተፈቀደ ብዩ ራሴን ስጠይቅ እና ምክንያቱስ ምንድነው ብዩ አስቤ አንዳንድ የዜና ምንጮችን ስመለከት ከስር ያለውን ነገር አነበብኩ.....

✔መንግሥት ከዐለም የገንዘብ ድርጅት 3 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘው የገንዘብ ምንዛሬ ተመኑን በገበያ እንዲወሰን ተስማምቶ እንደሆነ ዋዜማ ሰምታለች፡፡ ሀገር በቀሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሚተገበርባቸው ቀጣዮቹ 3 ዐመታት የጥቁር ገበያ ምንዛሬ አገልግሎት ሕጋዊ ፍቃድ ባላቸው የግል ወኪሎች እንዲከናወን ይደርጋል፡፡ መንግሽት የገበያ አሠራሩንም ይቀይራል፡፡

ይህ ምን ማለት ነው የምትሉ ካላችሁ ....

በኢትዮጵያ የምንዛሬ ተመን በየእለቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በሚያወጣው ዋጋ ግብይት የሚፈጸምበት ሲሆን ፣ ብሄራዊ ባንክ ካወጣው ዋጋ ውጭና ከንግድ ባንኮች ውጭ የሚፈጸመው የውጭ ምንዛሬ ግብይት #ወንጀል ነው።

በቀጣይ ግን የምንዛሬ ዋጋ በገበያ እንዲተመን ፣ #በጥቁር_ገበያ የሚደረገው ግብይት ይፋዊ ሆኖ #ፍቃድ አውጥተው ግብር በሚከፍሉ የምንዛሬ አገልግሎትን ብቻ ለመስጠት በሚከፈቱ ተቋማት ለመተካት ታስቧል ማለት ነው።

በአጭሩ በ3 አመታት ውስጥ #BLACK_MARKET ህጋዊ ይሆናል ነው ቁምነገሩ።

በዚህም አለ በዛ ግን የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ሀይሎች እጁ እየተጠመዘዘ መሆኑ ማሳያ ይመስለኛል!


ዋልታ ቲቪ የዶ/ር ደ/ ፅዮን የውሸት ሞት ዜና ከየትኛው ኮምፒውተር እንደተፃፈ ኢንሳን ምርመራ አድርግልኝ ብሎ ጠይቋል።

ዋልታ ኢንፎርሜሽን የትግራይ ብሄራዊ ክልል መንግስት ም/ርእሰ መሰተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ሂወታቸው አልፏል በሚል waltainfo.com ገፁ ላይ ዛሬ ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም የለቀቀወን ሰው ለማወቅና ለፍርድ ለማቅረብ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) በኮምፒወተሮቹ ላይ ምርመራ እንዲያርግ ጥያቄ አቅርቧል ሲሉ የውስጥ ምንጮቼ ነግረውኛል።
Via tesfaye getnet


የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከልን እንደሚከስ አስታውቋል!



ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር የትግራይ ብሄራዊ ክልል መንግስት ም/ርእሰ መሰተዳደር ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ሂወታቸው አልፈዋል ብሎ በዛሬው እለት ያሰራቸው ነጭ የፈጠራ ወሬ ፈፅሞ ሀሰት መሆኑን ለመላው ህዝባችን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ዋልታ ኢንፎረሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር waltainfo.com በሚል ፌስቡክ ገፁ ላይ ዛሬ ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም ከሰአት በኅላ ያሰራጨው ሀሰተኛ የአሉባልታ ወሬ፣ ይህ የመገናኛ አውታር ባለፉት አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ የብሄር ተኮር ጥቃት እንዲደርስ ስያካሂደው የነበረ ዘመቻ ኣካል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል፡፡

በመጨረሻም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር በህግ የሚጠቅይ መሆኑን ይገልፃል፡፡

የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ
ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም


የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የኖቤል ሽልማት በመጪው እሁድ በብሔራዊ ሙዚየም ይቀመጣል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት በመጪው እሁድ በብሔራዊ ሙዚየም እንደሚቀመጥ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 100ኛውን የዓለም የሰላም ኖቬል ሽልማት አሸንፈው ሰሞኑን ሜዳሊያውንና ዲፕሎማውን መቀበላቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሽልማቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት ይቀመጣል ተብሏል፡


#FederalPolice

- ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ በተወሰነው መሰረት በፌደራል ጥበቃ ስር የማድረጉ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።


ለቸኮለ! የዛሬ ረቡዕ ታሕሳስ 1/2012 የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

1. የዘንድሮው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ በተያዘለት ጊዜ በርግጠኝነት እንደሚካሄድ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ የምርጫ ጣቢያዎችን ወሰን በጂአይኤስ ቴክኖሎጂ የመለየት ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ የጊዜ መጣበብ ግን ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ቦርዱ እስካሁን የምርጫውን ጊዜ ሰሌዳ ያላወጣው የአዲስና ነባር ፓርቲዎች ምዝገባ ባለመጠናቀቁ ነው፡፡

2. ፍርድ ቤት በእነ ክርስቲያን ታደለ እና 10 አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ክስ ላይ ታሕሳስ 21 ብይን ለመስጠት ቀጥሯል፡፡ ዛሬ በ10 አለቃ መሳፍንት የክስ መዝገብ ያሉ 9 ተከሳሾች የክስ መቃወሚያቸውን ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፌስቡክ ገጽ ተመልክተናል፡፡ ዐቃቤ ሕግም መቃወሚያውን እንዲያቀርብ ታዟል፡፡

3. ኖቤል ተሸላሚው ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ ነገ የጀግና አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ ይህን ለፋና ብሮድካስት የተናገሩት የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ናቸው፡፡ አቀባበሉ ነገ ከጧት 12 ጀምሮ ከቦሌ ዐለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ቤተ መንግሥት ይዘልቃል፡፡ በአቀባበሉ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር ይሳተፋሉ፡፡

4. ምርጫ ቦርድ ለ9 ፓርቲዎች ዕውቅና መስጠቱን በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ የአፋር ሕዝባዊ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ሕዝብ ነጻነት ፓርቲ፣ የጋሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ሞቻ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ፣ ወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ፣ ሱማሌ አንድነት ፓርቲ ክልላዊ ሲሆኑ፣ የነጻነት እና ዕኩልነት ፓርቲ ሀገር ዐቀፍ ነው፡፡

5. በያዝነው የፈረንጆች ዐመት ብቻ ኤርትራ 16 ጋዜጠኞችን አስራለች- ብሏል ዐለም ዐቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፡፡ ጋዜጠኞችን በማሰር ቻይና በዐመቱ ግንባር ቀደሙን ደረጃ ይዛለች፡፡ ግብጽ በ3ኛ ደረጃ ትክተላለች፡፡ በኢትዮጵያ አሁን ታስሮ ያለው ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመ ወርቅ ነው፡፡ በኢትዮጵያም የማኅበረሰብ አንቂዎች-ጋዜጠኞች እስር እና እገታ ተገቢውን ሽፋን ባያገኝም አስደንጋጭ ነው ብሏል፡፡

6. ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የሕዳር ወር ዋጋ አጠቃላይ ግሽበት በ20.8 በመቶ መጨመሩን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ የምግብ ዋጋ ግሽበት ብቻውን ከአምናው ሕዳር ዋጋ በ24.5 በመቶ ጨምሯል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጣ ሸቀጦች ደሞ 16.4 በመቶ ጭማሪ ነው ያስመዘገቡት፡፡
[ዋዜማ ራዲዮ]


የበሻሻው ችግኝ የኖብል ሽልማት ተረኛ- ዶክተር አብይ አህመድ አሊ

ቀዝቃዛ በሆነው የኦስሎ መድረክ ብዙዎች ቆመዋል ። ከማርቲን ሉተር ኪንግ አስከ በርትናንድ ረሴል ከኦሳን ሱቺ አስከ ዳይላለማ በኖርዌይ ሮያል ፋሚሊ ታጅበው ላበረከቱት ስራ የአልፍሬድ ኖብልን የሰላም ሽልማት ተቀብለዋል።
ዛሬ ግን የኖብል ሽልማት ሊቀመንበር በርቲ ረሲስ አንደርሰን የጠራችው አንድ ኢትዮጰያዊ ነበር ። በጥቁር ሱፍ ፣በነጭ ሸሚዝና በጥቀር ከረባት ታጅቦ ከጅማ በሻሻ የተገኘው ሰው ከ20 አመት በላይ ተኮራርፈው የነበሩትን ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማስታረቅ በሰራው ስራ ሀገሩን ስም አስጠርቶ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ሆኖ ከ118 አመት ጀመሮ በየመቱ የሚሰጠውን የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀብሏል።
ጉረቤትክ ሰላም ካልሆነ እንተም ሰላም ማግኘት አትችልም በማለት ኤርትራ ጋር የፈፀመው እርቅ ፣ሱዳን፣ኬንያ ፣ደቡብ ሱዳን ፣ሱማልያና ጅቡቲ በማቅናት ጉረቤታሞች ሰላም እንዲሆኑ መጣራቸው ለሰላም ያላቸውን ትጋት ያሳያል።

ምንም እንኳን ለሽልማት ሰውዬው የታጠረበት ችግር ውስብስብ ነው ። የብሄር ግጭት ፣መፈናቀል ፣የሰዎች ግድያ፣ከፍተኛ ስራ አጥነት የዋጋ ንረት ፣ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው
በርቲ ረሲስ ሰውዬውን ከመጥራቷ በፊት እንደተናገረችው ኢትዮጰያና ኤርትራ ሰላም ቢፈጥሩም አሁንም ስምምነቱ በደንብ እንዳልተተገበረ አሁንም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፣ፓለቲካ እና ማህበራዊ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳለ አልሸሸገችም ።
ሆኖም ግን የበሻሻው ችግኝ ከወትድርና ተነሰቶ እራሱን በትምህርት አሳድጎ የሀገር የመሪነት ይዞ ስለሰላም ቆሞ ላገኘው ሽልማት ሊደነቅ ይገባል ።


በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን ዋሽንግተን ገባ!

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሚደረገው ውይይት ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያቀናውና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የልዑካን ቡድን ዛሬ ህዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም ዋሽንግተን ገብቷል።የልዑካን ቡድኑ ዋሽንግተን ዳላስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአምባሳደር ፍጹም አረጋና በኤምባሲው ዲፕሎማቶች አቀባበል ተደርጎለታል።በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሚካሄደው በዚህ ምክክር በቅርቡ በአዲስ አበባ እና በካይሮ ከተደረጉት የግድቡ የውሀ ሙሌትና ሌሎች ባልተቋጩ ነጥቦች ላይ እንደሚያተኩር ይጠበቃል።የአሜሪካ እና የአለም ባንክ ተወካዮች በስብሰባው በታዛቢነት ይሳተፋሉ።

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር


ስላም ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ይህ ለናንተ ይሆናሉ ያልኳቸውን ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃዎች የማደርስበት ቻናል ነው።
ማንኛውንም አስተያየት ለመስጠት እና እንዲስተካከል የምትፈልጉት ነገር ሲኖራችሁ @fact_news_Ethiopia ላይ ሃሳባችሁን መላክ ትችላላችሁ።ሰላም ከናንተ ጋር ትሁን። @seyoumteshome


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


የጀርመኑ ARD TV ጋዜጠኛ ማርከስ ፕሪብ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ቀረፃ እያደረገ ባለበት ወቅት አንድ መኪና አጠገቡ እንደቆመ እና መኪናውን ደግሞ በምሽት እያሽከረከሩ የነበሩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደሆኑ ገልፆ ይህንን ቪድዮ የትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።


በቂሊንጦ ማርሚያ ቤት በታራሚዎች መካከል በተፈጠር እርስ በርስ ግጭት ስድስት ታራሚዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሰባቸው፡፡

ዛሬ ሕዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ በሚገኘው በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በእስረኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት በስድስት ታራሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ታራሚዎችም ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሆስፒታል እንደተወሰዱ የፌደራል ማረምያ ቤቶች የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ዋና አስተዳዳሪ
ኮማንደር ጫላ ጸጋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ግጭቱ በታራሚዎች መካከል ከሆነ ፖሊስ ለምን ብዛት ያለው ጥይት ተኮሰ በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም ፖሊስ ጥይት የተኮሰው እስር ቤቱ ጣራ ላይ የተቀመጡትን ታራሚዎች እንዲወርዱ ለማድረግ በማሰብ ነው ብለውናል ኮማንድር ጫላ፡፡

በግጭቱ ሳብያም እስካሁን የሞተ እንድም ታራሚ አለመኖሩን ኮማንደሩ ነግረውናል፡፡

በጊዜው የደረሰው ግጭት ወዲያውኑ እንደተቆጣጠሩት እና አሁን ላይም ማረሚያ ቤቱ መረጋጋቱን ኮማንደር ጫላ ተናግረዋል፡፡


"የመከላከያ ሰራዊት መለዮውን እየቀየረ ነው። ከዚህ በኋላ የመከላከያ መለዮ ከተቋሙ አባል ውጪ ሊለበስ አይችልም እንዲሁም በምንም ምክንያት ወደ ውጪ አይወጣም።" - የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ


በእኔ ቢጤው ጆኒ ስም የተከፈተው በጎፈንድ ሚ (ሰለ ፈጣሪ ብላችሁ...) አካውንት ውስጥ ከነበረው አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ ሰባ አምስት ሺህ ዶላር ያህል ብቻ የደረሰው ጆኒ "በእኔ ስም የተከፈተው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለእኔው ሊሰጠኝ ይገባል" ሲል በሁለቱ ጥንዶች ላይ የክስ ፋይል ይከፍታል።

ሁኔታው አግራ ሞት እና ጥርጣሬ ያስነሳባቸው የህግ አካላትም ጉዳዩን በቅርበት መከታተል ሲጀምሩ የተባለው ገጠመኝ ሙሉ በሙሉ (የጆኒ ለጋሽነትን ጨምሮ) እውነት ሳይሆን የኬቲሊን እና የወንድ ጓደኛዋ ማርክ አይን ያወጣ ድራማ መሆኑን ይደርሱበታል።

በማምታታት የተካኑት ሁለቱ ጥንዶች ከተከፍተው የጎፈንድ ሚ አካውንት የተገኘው ገንዘብን ወደ ግል አካውንታቸው በማዘወር ከዘመናዊ ቢኤም ደብሊው መኪና አንስቶ እጅግ ውድ የሆኑ ቁሶችን በመሸማመት፣በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በመዘዋወር ቀማር ሲቆምሩ መክረማቸውን ማመናቸውን እና የተራረፈውንም የእርጥባን ገንዘብን ለባለቤቶቹ ለመመለስ መወሰናቸውን ተከትሎ ባለፈው አርብ ኒውጀርሲ ውስጥ የተሰየመው ፍ/ቤት በ39 አመቱ እና ዋንኛ የስርቆቱ ተዋኒው ማርክ ላይ በአንድ ክስ ብቻ የአምስት አመት እስራት ወስኖበታል። የ29 አመቷ ኪቲሌን እንዲሁ ጥፋተኛ መሆኗን በማመን እና የሰረቀችው ገንዘብም እንድትመልስ ተነግሯታል ፣ የአራት አመታት እስራት ለመቀበል ተዘጋጅታለች ሲል ከሳሽ አቃቢ ህግ ለዜና ሰዎች ገልጿል። በግዛት እና በፌደራል ደረጃ ገንዘብ የመዝረፍ፣ህገ ወጥ ገንዘብ የማሸጋገር ክስ የታመሰረተባቸው ጥንዶቹ እስከ ሀያ አመት እስራት እና ከ250ሺህ ዶላር በላይ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

የዚህ ሁሉ የስርቆት ማድመቂያ እና ተባባሪ የሆነው "ለጋሹ " ጆኒም ቀደም ሲል እኩይ ድርጊቱን መፈጸሙን በማመን ወደ ከእጽ ማገገሚያ(drug treatment)ማእከል እንዲገባ፣የበላውንም ገንዘብ እንዲመልስ ይህ ካልሆነ ግን የአምስት አመት እስራትን እንደሚጋፈጥ ተገልጾለታል። ለተቸገሩ ሰዎች ፈጣን የማህበራዊ የመረዳጃ ዘዴ የሆነው "ጕ ፈንድ ሚ" በበኩሉ ከለጋሶች የተዋጣውን እና በአካውንቱ የሚገኘው ቀሪው ገንዘብን ደግ ነገር ለመስራት አስበው በምትኩ በቁጭ በሉዎች ለተሞኙት ለለጋሾቹ እንደሚመልስ አስታውቋል።
(በታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

Показано 20 последних публикаций.

93

подписчиков
Статистика канала