Shewa press


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ማንቻውንም አይነት ጥቆማ እና አስተያየቶችን ለማድረስ 👉 @Natuu8

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


13.አርበኛ ሄኖክ አዲሴ ----ምክ/ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ
14.አርበኛ ሞገስ አበራው ----የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
15.አርበኛ አራጋው ያለው-----የስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ
15.1.አርበኛ ፍቅር መንግስቱ----የስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ ምክ/ኃላፊ
16.አርበኛ ሽመልስ ትዛዙ -----የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
16.1.አርበኛ አብደላ አያሌው -----የውጭ ጉዳይ መምሪያ ምክትል ኃላፊ
17. አርበኛ አበበ ቀዬ -----የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
17.1.አርበኛ አሰፋ መሰለ -----የአደረጃጀት መምሪያ ምክትል ኃላፊ
18.አርበኛ አበበ ፈንታው ----የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
18.1.አርበኛ ናትናኤል አክሊሉ ---የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክ/ኃላፊ
18.2.አርበኛ ምኒልክ ፈንታሁን --ሚዲያና ኮሚኒኬሸን ኃላፊ
19.አርበኛ ዚነት አደም-----የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ
19.1.አርበኛ አበበች ሲሳይ---የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ምክ/ኃላፊ
20.አርበኛ ደስታው መለሰ -------የጽ/ቤት ኃላፊ
20.1.አርበኛ አለባቸው ቀስቅሴ --ምክትል የጽ/ቤት ኃላፊ
21.አርበኛ ንጉስ አዳነ ----የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
21.1.አርበኛ አማረ አያሌው --የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ምክ/ኃላፊ
22.አርበኛ ረዳ ውበቱ ----------የሐብት አፈላላጊ መምሪያ ኃላፊ
23.አርበኛ እስራኤል እሸቴ ---የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
23.1.አርበኛ ፍቅሩ ፈንታ---የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ምክ/ኃላፊ
24.አርበኛ አክሎግ ሲሳይ-------የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ ኃላፊ
25.አርበኛ ****-የመረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ
25.1.አርበኛ *****-ምክ/የመረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ መሆናቸውን ለሰራዊታችንና የኅልውና ትግላችንን በስስት ለሚመለከተው በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም ለሚኖረው ሕዝባችን መግለጽ እንወዳለን።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ለትግሉ ደጋፊዎች በሙሉ፣ ለአማራ ሕዝብ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለሥራዓቱ ደጋፊዎች የሚከተለውን መልዕክት ማስተላለፍ እንወዳለን!

1. የበሰበሰውን የብልጽግና ሥርዓት በመደገፍ ወይም የሥርዓቱ አመራር በመሆን እያገለገላችሁ ያላችሁ አካላት፣ በብልጽግና መንግሥት መከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ ተቋማት ያላችሁ መሪዎችና የሰራዊት አዛዦች ብዙ የሥራ ባልደረቦቻችሁ እንዳደረጉት የአማራን ሕዝብ የኅልውና ትግል እንድትቀላቀሉ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) ጥሪ ያቀርብላችኋል፡

2. ውዱ የአማራ ሕዝብ - የሥርዓቱ ሕይወት የሆነውን መንግሥታዊ መዋቅር በማፈራረስ፣ የሥርዓቱ ጠባቂ የሆነውን የብርሃኑ ጁላን ሰራዊት በማግለል ከትጥቅ ትግልህ ጎን ለጎን በሁሉም ከተሞቻችን በሕዝባዊ ማዕበል ስርዓቱን ለመገርሰስ ዝግጁ እንድትሆን እናሳስብሃለን።

3. ውድ ኢትዮጵያዊያን - አብይ አህመድ ሁሉም አባገነኖች እንደሚያልፉት በቅርብ ቀን ያልፋል! የማያልፉት ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያ ናቸው! የአማራን ሕዝብ የኢትዮጵያ አካል ነው ብሎ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ፋሽስቱን አብይ አህመድንና የገማውን ሥርዓቱን እንዲቃወምና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንዲሰለፍ በአማራ ሕዝብ ስም የትግል ጥሪ እናቀርባለን።

4. በውጭው ዓለም የምትኖሩ ወገኖቻችን የሥርዓቱን ሁለንተና ለመገርሰስና ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ አውርዶ ለመጣል የምናደርገውን ትግል በገንዘብ እንድትደግፉ፣ የዘር ጭፍጨፋውን በዲፕሎማሲና በአደባባይ ሰልፎች ለዓለም መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ለዓለም አቀፉ ማህበርሰብ ደጋግማችሁ እንድታጋልጡ እናሳስባለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)
ወሎ፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ፤


ከአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመው ጭፍጨፋ የሕዝባችንን ትግል አይቀለብሰውም!!!
መንግሥት መር ጭፍጨፋው በሕዝባዊ የፋኖ ትግል ይቀለበሳል!!!

ፋሽስቱና ደም የጠማው የጠራራ ጋኒን አብይ አህመድ በሕዝባችን ላይ የከፈተውን መንግሥታዊ ጦርነትና እየፈፀመ ያለውን የዘር ማሳሳት፣ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት የሰማይ አምላክ ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ በተለይ ኢትዮጵያዊያን የተረዱት ጉዳይ ነው ብሎ ማሰብ ያስቸግራል። አምባገነኑ የብልፅግና ቁንጮ፣ የኢትዮጵያዊያን የዘመናችን ታላቁ መርገም አብይ አህመድ ሲፈልግ በምድር ጦር፣ ሲፈልግ በሰማይ ጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ሁለንተናዊ ፍጅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዐይንና ጀሮ ሳይሰጠው እንደቀልድ ሁለት ዓመት እያለፈው ነው።

የአማራ ሕዝብ በታንክና በመድፍ እንዲሁም በጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት የሚጨፈጨፍበት መሠረታዊ ምክንያት የሰው ልጅ በዴሞክራሲያዊው ዓለም ሊከበሩለት የሚፈልጋቸውን ልዩና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም የመንገድና መብራት፣ ፋብሪካና ዘመናዊ ከተሞች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም በምከፍለው ግብር ልክ ልዩ ልዩ የጤናና የትምህርት ተቋማት ይከፈቱልኝ ስላለም አይደለም! የአማራ ሕዝብ የመብትና የኑሮ ማሻሻያ ጥያቄዎችን ይዞ ሳይሆን የወጣው ሰው ተብሎና ሰው ሆኖ መኖር በመከልከሉ የሕጋዊ ሰውነት እውቅናን፣ የሕግዊ ሰውነት ውክልናን እንዲሁም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በኢትዮጵያ ምድር ላይ በሕይወት መኖር መቻልን ለመጠየቅ የወጣ ህዝብ ነው፤ መንግሥታዊ ጦርነት የተከፈተበትም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በሕይወት መኖርን ስለጠየቀ ብቻና ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ውሎች ሁሉንም ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱና በሰውነቱ ልክ ይወቁት፣ ይዳኙት፤ እኔንም ሕጋዊ የዜግነት እውቅናና ሕጋዊ የሕዝብ ውክልና ይስጡኝ፣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋርም እኩል ይዳኙኝ የሚል የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ነው። በሕዝባችን ጥያቄ ውስጥ በሀገራችን መንግስት በዘራችን ምክንያት ማንነታችን ሳይከዳ፣ ማንነታችን ሳይሳሳና ሳይጠፋ በሕግ ታውቆ መኖርን፣ እኩልነትን፣ ዲሞክራሲንና ፍትሕን የምናገኝ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መሠረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ግን ልብ ያሉት አይመስልም።

የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ሕዝብ ጨፍጫፊውና ጦረኛው አብይ አህመድ ግን እነዚህን የከበሩ የሕዝብ ጥያቄዎች የአማራን ሕዝብ በማንበርከክ ጥያቄዎቹን ድጋሜ እንዳይነሱ ማድረግ ካልሆነም የአማራን ሕዝብ ማጥፋትን ዓላማዬ ብሎ መያዙ ገሃድ የወጣ ሐቅ ነው። በአንዳንድ ፀሐፍት አምባገነኑ ሦስተኛው የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ኤዲ አሚን ዳዳ ዘር መርጦ የሰውን ልጅ ስጋና ደም ላልተገባ ተግባር ያውላል ተብሎ እንደተጻፈው ጭራቁ አብይ አህመድን የአማራን ሕዝብ ለማንበርከክ ብሎ በከፈተው ጦርነት የአማራን ልጅ ስጋና ደም እየተመገበ ያለ ሰው በላ መሆኑን ኢትዮጵያውያንም ሆነ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሊገነዘበው የሚገባ እውነት ነው። የአማራ ሕዝብ በማንኛውም የታሪክ አጋጣሚ በሀገሩ መሪና መንግሥት በዚህ ልክ የዘር ጭፍጨፋ ደርሶበት አያውቅም። ፋሽስቱ የጣልያን ወራሪ ክ1928 -33 ዓ.ም ካደረሰው በደል በማይወዳደር መልኩ በሕዝባችን ላይ በዚህ አምሳ ዓመት የደረሰበት በደል የላቀ ሲሆን የሀገር ልጅ በሆነው አብይ አህመድ የደረሰበት በደል ግን የሁሉ ቁንጮ ሆኖ በገሀድ የምናየው ጉዳይ ነው። የአማራን ሕዝብ ባሪያ አደርገዋለሁ ብሎ ቆርጦ የተነሳው አባገነን የገባበት ቅጀት ውስጥ ለመውጣት የሰላም ነጋሪት ቢጎሰምለትም መንቃት የሚፈልግ አይደለም።

ሰሞኑን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)ን የጠቅላላ ጉባዔ ዓመታዊ ስብሰባን አደናቅፋለሁ ብሎ በማሰብ አመራሮቹ በሌሉበት በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በጀትና በድሮን የፈፀመው የንጹሓን ጭፍጨፋ የዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። አማራ መሆናቸውን የማያውቁ ሕጻናት በአብይ አህመድ የግል ንብረት በሆነው አየር ኃይል አማራ ተብለው ተጨፍጭፈዋል።

በእርግጥ የተሸነፈ ስነ ልቦና ባለቤት የሆነውና የስልጣን ጥሙ ከአካሉ የሚገዝፍበት - ከአዕምሮው የሚሰፋበት ይህ የዘመኑ የአፍሪካ አባገነኖች ቀንዲል ከምድር ጦር በዘለለ ሰው አልባ አውሮፕላንና ጀት የሚጠቀመው የሽንፈት ፅዋውን እየተጎነጨ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለው የዘር ጭፍጨፋ ሕዝባዊ ትግላችንን አይቀለብሰውም፤ የተከፈተብን መንግሥት መር ጦርነትም እንደሕዝብ መደራጀታችንን፣ መታጠቃችንን፣ አምባገነናዊ የብልፅግና ሥርዓትን ማስወገዳችንን አያስቀረውም። ሥርዓቱ በሕዝባችን ላይ የሚፈፅመው በደል ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ የሚያበረታን እንጅ ክንዳችንን የሚያዝለው አይሆንም።

ስለሆነም ይህንን የአብይ አህመድን ሰይጣናዊ ተግባር ለመቀልበስ በቤተ አማራ (ወሎ) የምንገኝ ፋኖዎች በቀን 14/05/2017 ዓ.ም ወደ አንድነት መምጣታችን ይታወቃል። በመሆኑም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የመጀመሪያውን የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባውን በማድረግ በስኬት ያጠናቀቀ ሲሆን የማዕከላዊ ምክር ቤትንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውንም አዋቅሯል፤ በሥራ አስፈጻሚና በልዩ ልዩ መምሪያዎች ደረጃ የተመደቡ አመራሮችና ምደባውም የሚከተለውን ይመስላል።

1.ዋርካው ምሬ ወዳጆ --------ሰብሳቢ
2.አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ ------ምክ/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
3.አርበኛ ሀብታሙ ደምሴ -----ምክ/ወታደራዊ አዛዥ
4.ኮሎኔል አባይ ባየው--------ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ
5. አርበኛ በለጠ ሸጋው ------ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
5.1. ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ ----ምክትል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
6.ሺ ዓለቃ ያረጋል አሰፋ-----ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
6.1. አምሳ ዓለቃ ሲሳይ ገላነው---ምክትል ኃላፊ - ለሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ
6.2. ዶ/ር አቡበክር ሰይድ---ምክትል ኃላፊ - ለጤና ጉዳይ
7.መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ---ሎጂስቲክስ መምሪያ ኃላፊ
7.1.አርበኛ ሞላ ሰማው ------ምክትል ኃላፊ - ለስንቅና ትጥቅ ስርጭት
7.2. አርበኛ ኢሳይያስ መልኩ----ምክትል ኃላፊ - ለኦርዲናንስ ክፍል
7.3. አርበኛ ኑረዲን አበበ ----ምክትል ኃላፊ - ለትራንስፖርት ስምሪት
8.መቶ ዓለቃ ዮሴፍ አስማረ ---ወታደራዊ ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
8.1. አርበኛ ጌታቸው ሲሳይ ----ምክትል የሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
9.አርበኛ ** ---ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ኃላፊ
10. አምሳ ዓለቃ አደም አሊ ----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን (ስርጸት) መምሪያ ኃላፊ
10.1.አርበኛ ሙላት አላምረው-----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን መምሪያ ምክ/ኃላፊ
10.2.አርበኛ ተመስገን በቀለ ----የኪነትና መዝናኛ ክፍል ኃላፊ
11.አርበኛ ተሾመ ፈንታዬ -----ልዩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
12.ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ -----ወታደራዊ አማካሪ




«በአሸባሪነት የሚፈልገኝ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ሀገር ቤት እንዳልገባ ከለከለኝ!» ልደቱ አያሌው

ጉዳዩ፦ ወደ አገሬ እንዳልጓዝ መከልከልን ይመለከታል

ወደ ኢትዮዽያ ለመሄድ በኢትዮዽያ አየር መንገድ ትኬት የቆረጥኩት ለዛሬ ስለሆነ ከጧቱ 12 ሰዓት በአትላንታ ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝቸ ነበር። የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈ የኢትዮዽያ ፓስፖርትና የተረጋገጠ የጉዞ ትኬት ይዥ የተገኘሁ ቢሆንም የኢትዮዽያ አየር መንገድ ግን በአሜሪካ የኢትዮዽያ ኤምባሲን አነጋግሬ የተለየ ፈቃድ ካልተሰጠኝ በስተቀር ወደ ኢትዮዽያ መጓዝ እንደማልችል በአትላንታ የኢትዮዽያ አየር መንገድ ሀላፊ በሆኑት በአቶ ተሾመ ገ/ስላሴ ተነግሮኝ ተመልሻለሁ።

በአሸባሪነት ወንጀል ሊከሰኝ እንደሚፈልግና በቁጥጥር ስር እንድውል ከኢንተር-ፖል ጋር ጭምር እየተነጋገረ እንደሆነ ሲገልፅ የነበረው የኢትዮዽያ መንግስት ዛሬ በራሴ ፈቃድ ወደ አገሬ ለመመለስ ስሞክር በእኔ ላይ ህገ-ወጥ ክልከላ ማድረጉ አስገርሞኛል። ምን አልባት እንዲህ አይነቱ ድርጊት በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈፀመ ሊሆን ይችላል። መንግስት እኔን በወንጀለኛነት ከጠረጠረኝ ሊከሰኝና ሊያስረኝ ይችላል እንጅ ወደ አገሬ እንዳልገባ ሊከለክለኝ አይችልም።

አንድን ኢትዮዽያዊ የሆነና የኢትዮዽያ ፓስፖርት የያዘን ዜጋ ወደ አገሩ እንዳይገባ ለመከልከል የሚያስችል ምንም ዓይነት የህግ ማዕቀፍ የለም። ስለሆነም በሌላ አገር አየር መንገድ ትኬት ቆርጨ ሰሞኑን ወደ አገሬ ተመልሸ እንደምሄድ በዚህ አጋጣሚ አሳውቃለሁ።
ከአክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው

@showapress


ከሸዋሮቢት ከተማ ወደ ደብረብርሃን አመራር አጅቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ የአድማ ብተናና መከላከያ ሠራዊት ተደመሠሠ!

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
የካቲት 2/2017 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሃመድ ቢሆነኝ ኮር አስቻለው ደሴ ክፋለጦር 4ኛ ሻለቃ ከሸዋሮቢት ወደ ደብረብርሃን የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮችን አጅቦ ሲንቀሳቀስ በነበረ በጠላት ፓትሮል ላይ የደፈጣ እርምጃ በመውሰድ የጠላት ሀይልን ደምስሶታል። አመራሮቹን በ6 ፓትሮል አጅቦ ዲሽቃና ዙ-23 ያጠመደው የጠላት ሃይል ከሸዋሮቢት ከተማ ሳይርቅ ልዩ ቦታው ፍርፍር በተባለ ቦታ የአርበኛ መከታው ቀኝ እጆች በደፈጣ ጠብቀው አርግፈውታል።

በሌላ ግንባር የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር 7ለ70 ክፍለ ጦር የኦሮሞ ብሄረሰብን ምሽግ አድርጎ ከሚነሳው የጠላት ሀይል ጋር ገጥሞ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል። የጠላት ቡድን ሀይሉን አሰባስቦ ውጊያ ቢክፍትም የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ስር የሚገኘው 7ለ70 ክፍለ ጦር በተለያየ አቅጣጫ የጠላትን ሃይል በመግጠም ከፍተኛ ኪሳራ አድርሶበታል። በዚህ ቀጠና በአውደ ውጊያ የተመታው የብልፅግና ሠራዊት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ውስጥ ከተደበቀው ከሸኔ ጋር በጥምረት ውጊያ የከፈተ ቢሆንም በተባበረ ክንድ በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አናብስቶችና የጦር ጠበብቶች እየተደቆሰ ይገኛል።

ድል ለአማራ ፋኖ
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

@Showapress


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በሸዋ ኤፍራታና ግድም ወረዳ ዘንቦ ቀበሌ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት እናትና ልጅን ጨምሮ አራት ንጹሃን ተገድለዋል። ከፍተኛ የንብረት ውድመትም ደርሷል።

@Showapress


በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ኤፍራታናግድም ወረዳ አገዛዙ በፈፀመው የድሮን ጥቃት የንፁኃኖች ሕይወት አልፏል!

በሁሉም መስክ ኪሳራ አያስተናገደ ያለው አሸባሪው የብልፅግና አገዛዝ በተለያየ ወቅት የሚፈፅማቸው ንፁኃንን ዒላማ ያደረጉ የድሮን ጥቃቶች በርካታ ሲቪሊያን ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ገደማ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የፋኖ አባላትና አመራሮች ይኖሩበታል በሚል የተሳሳተ ግምት በኤፍራታና ግድም ዘንቦ ቀበሌ በሰነዘረው የድሮን ጥቃት የግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ ባደረሰው ጉዳት የንፁኃኖች ህይወት አልፏል።

አገዛዙ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት እናት ከእነ ልጇ ጨምሮ 4 ሲቪሊያን ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከ20 በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳትና ውድመት አድርሷል።

የአብይ አህመድ አማራ ጠል አገዛዝ በጋራ ታግለን ልናስወግደው የሚገባ ከባዕድ ወራሪ ያልተለየ አረመኔና ጨካኝ አገዛዝ በመሆኑ በተባበረ ክንድ ሁሉም አማራ በተሰለፈበት መስክ ስርዓቱን ለመቅበር የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

ክብር ለሰማዕታት
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
የካቲት 1/2017 ዓ.ም

@Showapress


የአማራ ፋኖ በጎጃም የ3ኛ ክፍለ ጦር ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ከስድስት ወራት በላይ ያሰለጠናቸውን የኮማንዶ አባላት አስመርቋል።

@Showapress


ገዳይዋን ተሸክማ ሀኪሟን የምትቀብር ሀገር
ነፍስ ይማር ወንድማችን💔😭

@showapress


የሐዘን መግለጫ
============
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በተወለዱ በ37 አመታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።

ዶ/ር አንዷለም በዩኒቨርሲቲያችን፣ ብሎም በአገራችን አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ ያወግዛል። በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን አጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@Showapress


ዶክተሩ ተገደለ‼️

የጉበት ፣ የቆሽትና የሀሞት ከረጢት ከፍተኛ እስፔሻሊስት ሀኪም ፣ መምህር፣በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በጥበበጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር እና ተመራማሪ የሆነው ዶ/ር አንዷለም ዳኜ በባህርዳር ጥበበ ጊዮን እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሰራ አምሽቶ ወደ ፈለገ ህይወት ሆ/ል ሌላ የሚሰራው ኬዝ ኑሮት እየሄደ ባለበት ሰአት ከምሽቱ 1:00 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ከመኪናው አስወርደው ገድለውታል።

ዶ/ር አንዷለም ዳኜ 37 አመቱ ሲሆን በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ብሎም በአገራችን  አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻች ውስጥ አንዱ ነበሩ።

@Showapress


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
አፄ አምደ ፂዎን ኮር
ራንቦ ክፍለጦር 1ኛ ሞገሴ ሻለቃ!

@showapress


በጥምቀት በዓል በታቦተ ሕጉ ላይ የተሳለቁ በማኅበራዊ ሚዲያ አላስፈላጊ መልእክት ያሠራጩ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሕግ እንደሚጠየቁ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን ግለሰቦችና ቡድኖች ሃይማኖታዊ ቅራኔ እና ጥላቻ ሊፈጥሩ የሚችሉ በቪዲዮ የለቀቁትን አሉታዊ መልእክቶችን እና ተግባራትን በፍጥነት ለማረም በጽሕፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ማብራሪያ ለሚዲያ አካላት ሰጥቷል፡፡

በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራራው ከእምነቱ ሥርዐት ባፈነገጠ መንገድ አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦችና ቡድኖች የሌላውን

* እምነትና ሥርዐት በማንቋሸሽ
* ክብረ ነክ ተግባራትን በመፈጸም
* በተለይም በጥምቀት በዓል ታቦተ ሕጉ ላይ በመሳለቅ

የኢስላማዊ አለባበስ መገለጫ የሆነውን ጀለቢያ በመልበስ ሙስሊሞች በመምሰል የትንኮሳ ስብከቶችና ዝማሬዎች በማቅረብ፣

የትንኮሳ አለባበሶች ጭምር በመጠቀም በማኅበራዊ ድረገጽ የለቀቁት አጫጭር ቪዲዮችዎች የእምነቱ ተከታዮችን ማስቆጣቱን ያብራራል፡፡

ይህ ዓይነቱ ተግባር በሀገራችን ለዘመናት የዘለቀውን የመከባበር፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽር ድርጊት መሆኑን የገለጸው መግለጫው፤ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ የድፍረት ድርጊት በመሆኑ ይህን የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ

መጠየቅም መጀመሩን መግለጫው ያስረዳል፡፡ ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ቡድን ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሌሎችን መብትና ጥቅም በሚጻረር አግባብነት የሌለውና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት የሚፈጽም ማንኛውም ሕገ ወጥ ተግባር በዝምታና ሊታለፍ እንደማይገባው ይገልጻል፡፡

በመጨረሻም ማኅበራዊ ድረገጾችን እና ሚዲያዎችን በመጠቀም የጥላቻ ንግግሮች፣ ትንኮሳዎችና ክብረ ነክ ድርጊቶች የሚፈጽሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፡- ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ከፍትሕ የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ እንደሆነ የወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡ አያይዞም ይህ ዓይነቱን ተግባር ለመከላከል የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሥርዐት ላይ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ ያስረዳል፡፡

Via EOTC TV

@showapress




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
እኛም ከእንግዲህ ህዝባችንም እንዲበጠበጥ፣ ሰላሙም እንዲደፈርስ፣ እኛም እንድንሰዋ አንፈልግም። ይህ የሰራዊቱ ሁሉ ድምፅ ነው ። ቁጭ ብላችሁ ተወያዩ።”

አንድ የመከላከያ አዛዥ የተናገረው…,

@showapress


ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ
ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !!

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ።

የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ እረፍት ከአባልነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ግንባር ቀደም ትግል ሲያደርግ የነበረው ጀግናው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ጥር 12 ቀን ሌሊት ለጥር 13 አጥቢያ ዋሸራ በተባለ ቦታ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተናንቆ የክብር መስዕዋትነትን ተቀብሏል ።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ጎንጅ ወ እንዘግድም በተባለ ቦታ የተወለደ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ከማጠናቀቁ በፊት "በአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ " ከፍተኛ አመራር በመሆን ወቅቱ የጠየቀውን ትግል አድርጓል ።
ከዚያም አብይ አህመድ አማራን መውረሩን ተከትሎ ወደ ትውልድ ቀዬው እንዘግድም በመሔድ ቀደም ሲል የነበረውን " ጎንጅ ወ እንዘግድም ብርጌድን" የአሁኑን "ንስር ብርጌድን" ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በመመስረት አይተኬ የትግል አሻራ ያሳረፈ ጀግና ነበር።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በሞጣ : በአዴት : በምላጭበር : በፈረስ ቤት በቋሪት ከትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን ከባድ ውጊያ ያደረገ ልበ ቆራጥ አርዓያ ፋኖ ነበር።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከተመሰረተ ዕለት ጀምሮ በአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኘነት ሀላፊ በመሆን ሰለቸኝ ታከተኝ ሳይል ያገለገለ ሲሆን ከቅንነት የመነጨ ልበ ቆራጥነትን ያስመሰከረ እና ታታሪነትን እና ለህዝብ ዋጋ መክፈልን መርህ ያደረገ ጀግና የፋኖ አመራር ነበር።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በነበረበት ጊዜ ያለፈውን ፈታኝ ጊዜ በመረዳት የመምራት እና ችግርን የመፍታት ትልቅ አቅሙ ታምኖበት የሁለተኛ ( ተፈራ) ክፍለጦር ሰብሳቢ በመሆን ትልቅ የመንፈስ መነቃቃትን የፈጠረ ታጋያችን ነበር።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ለጥር 13 አጥቢያ ጠላት ወደ ዋሸራ ከተማ ለመግባት በመገስገስ ላይ እያለ ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ አብሪ የጠላት ሐይሎችን በመደምሰስ የክብር መስዕዋትነትን ተቀብሏል ።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ፅናትን : መታመንን : ቁርጠኝነትን እና መስዕዋትነትን ከታላላቅ ሰማዕታት ፋኖዎች በመውረስ ለቀሪው የአማራ ትውልድ ዕውነትን አስተምሮ ያለፈ ጀግና ነው።

ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በጎጃም የፋኖ ዮሐንስ አለማየሁን ክብር የሚመጥን ዝግጅት እንደሚያደርግ እየገለፀ ለትግል ጓዶቹ እና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ይመኛል ።

@showapress




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የትላንቱ የ ቋሪት ጭፍጨፋ😭

@showapress


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ይሄን ሽማግሌ ሊበሉት ነው ፋኖ እንደማይነካው እርግጠኛ ነኝ ነገር ግን እራሳቸው እረሽነው ፋኖ እረሸነው እንደሚሉ አያጠራጥርም ለማንቻውም አርፎ ቢቀመጥ ይሻለው ነበር።

@showapress

Показано 19 последних публикаций.