❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን #እመቤታችንን_ቅድስት_ድንግል_ማርያምን የከበረ_ሊቀ መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል በአበሠራት መሠረት #ቅዱስ_ደቅስዮስ_በዓል_ላከበረት_ለብሥራት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና የእመቤታችንን ተአምረ ማርያም መጽሐፍ ለጻፈው #ለቅዱስ_ደቅስዮስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ መልአክ ከመላእክት አለቃ #ከቅዱስ_ገብርኤል ከበዓሉ መታሰቢያ ዳህና በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ ከተሠራችበትና ከከበረችበት ተአምራትም ካሳየበትና ከአገር ኤጲስቆስ #አባ_አርኬላዎስ ምስክር ከሆነበት፣ ከእስክድርያ አገር ሠላሳ ስድስተኛ ጳጳስ ከከበረ ከአባት #ከአባ_አንስጣስዮስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የብሥራት መዝሙር፦ "አብሠራ ወይቤላ #ለማርያም_ገብርኤል_አብሠራ_መልአክ። አልቦ ማኅለቅት ለሰላሙ ዲበ መንበረ #ዳዊት_መንግሥቱ ትጸንዕ። ትርጉም፦ #ቅዱስ_ገብርኤል_ማርያምን እንዲህ ብሎ አበሠራት ለሰላሙ ፍጻሜ የለው #በዳዊት_መንግሥት መንበር ላይም መንግሥቱ ስልጣኑ ትጸናለች፡፡
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ደቅስዮስ_በዓለ_ብሥራትን_ማክበሩ፦ በዓልን የማክበሩ ምክንያትም እንዲህ ሆነ ይህ ኤጲስቆጶስ ደቅስዮስ ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ አስቦ በመትጋት የተአምራቷን መጽሐፍ ሰብስቦ አዘጋጀላት። የምእመናን ክብር የሆነች አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ማርያምም ተገለጸችለትና መጽሐፋን በእጅዋ አንሥታ ይዛ "ወዳጄ ደቅስዮስ ሆይ ይህን መጽሐፍ ስለ ጻፍክልኝ ባንተ ደስ አለኝ አመሰገንኩህም" አለችው ከዚህም በኋላ ከእርሱ ተሠወረች። ቅዱስ ደቀስዮስም ይህን ነገር በራይ ባየ ጊዜ ክብርት ድንግል እመቤታችን ማርያምን ከመውደዱ የተነሣ ፈጽሞ ደስ አለው እርሷንም ስለ ወደደ ፍቅርዋ እንደ እሳት አቃጠለው የሷን ክብር አብዝቶ ይጨምር ዘንድ ምን እንደሚያደርግ የሚሠራውን ያስብ ጀመር።
❤ ከዚህም በኋላ በዚያን ጊዜ ጾም ስለነበር ሰዎች አስቀድመው ሊአከብሩት ያልተቻላቸውን የመላእክት አለቃ የከበረ ቅዱስ ገብርኤል ባበሠራት ቀን በዓሏን አከበረ። እርሱም የከበረ የሚሆን የልደትን በዓል ከማክበር አስቀድሞ በስምንት ቀን አደረገ ይኸውም ታኅሣሥ በባተ በሃያ ሁለት ቀን ነው በጵጵስናውም ዘመን ተሠርታ እስከዚች ቀን ጸንታ ትኖራለች። ሰዎችም በዓሉን በአከበሩት ጊዜ ፈጽሞ ደስ አላቸው።
❤ ደግነትን ምሕረትን ቸርነትን የምትወድ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ማርያም በእጅዋ የከበረ ልብስ ይዛ ዳግመኛ ተገለጸችለትና "አገልጋዬ የሆንክ ወዳጄ ደቅስዮስ ሆይ በእውነት አመሰገንኩህ በአንተም ደስ አለኝ ሥራህንም ወደድሁ። በእኔም ደስ እንዳለህና የከበረ መልአክ ገብርኤል እኔን በአበሠረበት ቀን በዓሌን ስለአከበርክ ሰውንም ሁሉ ስለ እኔ ደስ ስለአሰኘህ እኔም ዋጋህን ልሰጥህ አንተ በዚህ ዓለም እንዳከበርከኝም በሰው ሁሉ ፊት አከብርህ ዘንድ እወዳለሁ" አለችው። እሷም "ትለብስ ዘንድ ይችን ልብስ እነሆ አመጣሁልህ በላዩም ትቀመጥ ዘንድ ይህን ወንበር አመጣሁልህ ከሰው ወገን አንድ ስንኳ ይህችን ልብስ ሊለብሳት በዚህም ወንበር ላይ ሊቀመጥ የሚቻለው የለም። ይህን ነገሬን የሚተላለፍ ቢኖር እኔ እበቀለዋለሁ" አለችው ይህንንም ተናግራ ከእርሱ ተሠወረች።
❤ ከዚህም በኋላ ታኅሣሥ22 ቀን በዐረፈ ጊዜ ሌላ ኤጲስቆጶስ ተሾመ ያቺንም ልብስ ለበሳት በወንበሩም ላይ ተቀመጠ ወዲያውኑ ከወንበሩ ላይ ወድቆ ሞተ ይህንንም ያዩ ከእመቤታችን ማርያም ተአምር የተነሣ አደነቁ እጅግም ፈርተው እመቤታችንን አከበሩዋት ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ለእርሱም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ #የቅዱስ_ገብርኤል_የበዓሉ_መታሰቢያ ዳህና በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራችበት ተአምራትም ያሳየበትና በዚች ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ የከበረችበት ነው የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ አርኬላዎስ ምስክር የሆነበት ነው።
❤ ይህም መልአክ ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር የታመነ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተላከ "የደስታ መገኛ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው አንቺም ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ" አላት።
❤ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድም ካህኑን ዘካርያስን ያበሠረው እርሱ ነው ይህ መልአክ እጅግ የከበረ የተመረጠ ገናና የሆነ ነውና ስለ እኛ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ዘንድ ልባችንን አንጽተን ወደዚህ የከበረ መልአክ እየለመንን መታሰቢያውን ልናደርግ ይገባል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱ ረድኤቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ22 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_እብል_ለደስቅዮስ_ባሕርያ። ኤጺስቆጶስ ዘሀገረ ጥልጥልያ። በእንተ ዘጸሐፈ ላቲ ትምእምርተ ዜናሃ ወጸጋ ዕበያ። እንተ ወሀበቶ ወላዲተ አምላክ ማርያ። ልብሰ ሰማያዊት እስከ ዮም ነያ"። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ22።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ማኅሌቱ_ምስባክ፦ "በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ። ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ። ወእገኒ ለስመከ። መዝ 137፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥26-39።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ። ወትሠይም(ሚ)ዮሙ መላእክተ በኵሉ ምድር። ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ"። መዝ 44፥16-17። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 1፥8-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9-18 እና የሐዋ ሥራ 12፥7-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም የብስራት ቅዱስ ገብርኤል በዓል፣ የቅዱስ ደስቅዮስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL