🇪🇹🇷🇺 የካርፒንስኪ የሩሲያ የሥነ-ምድር ምርምር ኢንስቲትዩት የመጀመሪያውን የሳምቦ ማዕከል በአዲስ አበባ ከፈተ
ማዕከሉ የኢትዮጵያ እና ሩሲያን የሁለትዮሽ ግንኙነት በስፖርትና ባህል የማሳደግ አላማ እንዳለው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
አሰልጣኝ እና የሴንት ፒተርስበርግ የጁዶ ፌዴሬሽን ኃላፊ ሚካሄል ራክሊን፤ ሳምቦ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ለማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
🗣 "ግባችን ከሳይንስ እና ከእድገቱ በመጀመር ወዳጃዊ ግንኙነቶችን ማጎልበት ነው። ወዳጅኝነት፣ ሳይንስ እና ስፖርት አንድ እና ጠንካራ እንድንሆን የሚያደርጉን ኃይሎች ናቸው። ጥሩ ልምዶችን እንድንለዋወጥ ያስችሉናል” ብለዋል።
ራክሊን፤ የሳምቦ ማዕከል ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በስፖርት እና ሳይንስ ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያሳድግ እምነታቸውን ገልጸዋል።
ሳምቦ ብሔራዊ የሩሲያ ስፖርት ነው ያሉት የካርፒንስኪ የሩሲያ የሥነ-ምድር ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፓቬል ኪምቼንኮ፤ የተከፈተው ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ አትሌቶችን እና ባለሙያዎችን የማፍራት እቅድ እንዳለው ተናግረዋል።
🗣 "ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች እና ከሩሲያ ባለሙያዎች ጋር እቅድ አውጥተናል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ሻምፒዮና እንዲሳተፉ ማስቻል ቀዳሚ ግባችን ነው። በረጅም ጊዜ ውስጥ አፍሪካውያን አትሌቶች በዓለም ሳምቦ ሻምፒዮና ላይ እንደሚወዳደሩ ተስፋ እናደርጋለን።"
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡-
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia