“ ዝቅተኛ የሆነውን በላጭ በሆነው ነገር መለወጥን ትፈልጋላችሁን “
አል በቀራህ 61
✍ ይህ አንቀፅ በኒ - ኢስራኢሎች ከሰማይ የሚወርድላቸውን ምግብ ሰልችቶናል ብለው ከመሬት ቅጠላ- ቅጠል ፣ ዱባ፣ ምስር ወዘተ እንዲበቅልላቸው በጠየቁ ጊዜ ሙሳ አልይሂስሰላም የሰጧቸው ምላሽ ነበር ።
❇️ የሰይዳችን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ኡመትም ላይ የበኒ- ኢስራኢሎችን ባህሪ የተላበሱ ሙስሊሞች አልጠፋም ፣ እኚህ ሚስኪኖች ህዝበ- ሙስሊሙ በአንድ ድምፅ በዒልምና በተቅዋ የመሰከረላቸውንና ሰለፎች የሆኑትን አራቱን የመዝሀብ መሪዎች ትተው በዘመናችን የሚገኙ ዩቱዩበሮችንን ያለ እውቀት ታዋቂ ሰዎችን የሚከተሉ ወንድሞች ናቸው ።
❇️ ማንኛውም ለራሱና ለዲኑ ክብር ያለው ሙስሊም በላጮቹን እነ ኢማም አቡ- ሀኒፋን ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማም አሽሻፊዒይንና ኢማሙ አህመድን በዝቅተኞች አይቀይርም ።
በአሏህ ፍቃድ እኔ መቼም ቢሆን በላጮችን በዝቅተኞች አልቀይርም እናንተስ ⁉️
https://t.me/sufiyahlesuna