ጤንነት ፀጋ ነው አመስጋኝ ባርያ ሁን!
ቀደም ሲል ከነበሩ ሰዎች አንዱ ፀጉር ያልነበረው (የተመለጠ) ሰውነቱ በለምጥ የተሸፈነ ሁለቱም አይኖቹ የማያዩ እንዲሁም ሁለቱም እጆቹና እግሮቺ የማይንቀሳቀሱ ነበር። ምንም እንኳ በዚህ መሰል ከባድ ፈተና ቢፈተንም ሲበዛ አላህን አመስጋኝ ባርያ ነበር።
ታድያ አንድ ቀን:—
"ብዙ ሰዎችን ከተፈተኑበት ፈተና ለጠበቀኝና ከበርካቶች የተሻልኩ ላደረገኝ ጌታ ምስጋና ይድረሰው" ሲል አጠገቡ የነበረ አንድ ሰው ይሰማውና :—
" መላጣ ፣ በለምፅ የተሸፈንክ ፣ አይነ ስውር፣ ሁለት እጅ እና እግርህ ሽባ ሆኖ ሳለ ከማን ነው ተሽለህ ነው ከብዙ ሰዎች የተሻልኩ የምትለው!?" ሲል ይጠይቀዋል።
አመስጋኙ ባሪያም:—
"አንተ ሰው ሆይ! ወየውልህ አላህ እርሱን የምታወሳ ምላስ፣ አመስጋኝ ልብና በደረሰበት ፈተና ታጋሽ ሰውነትንስ ሰጥቶኝ የለምን!?" ሲል መለሰለት ይባላል።
ሱብሀነላህ!
قل الحمد لله.