# በሁለቱም ሀገር!!#
ምን ያደርግልኛል ዱነያዊ ኮተቱ
ጀነት አይገዛልኝ ለሚቀር በንቱ
ታዳ ምን ሊፈይድ ዱንያ ፍለጋ
ልቤ ላያርፍበት በከንቱ ላይረጋ
ይህንስ አልሻም ምንዳ የሌለበት
ነገ በአኼራ የምወቀስበት
እ
ው
ነ
ተ
ኛው ወዳጅ
መንገዱ የያዘ በሰለፎች መንሀጅ
ውዴታ እሚያውቅ እውነተኛ ወዳጅ
ሀብታምና ቁንጅና በሱና ፈልጎ
ውስጡ ያሳመረ ነፍሲያው ሸሽጉ
ስንቁን የሚሰንቅ አኼራን አስታዋሽ
ነገ ከነገ ወዲያ እማይል በጭራሽ
የጎደላት አሟይ ለሚስቱ አሳቢ
ያለው ሁሉ ለጋሽ ተንከባካቢ
ከዱንያዊ ኮተት ጀነት ያስቀደመ
በውሂድና ቡሱና ልቦነው ያከመ
በተግባር ታንፆ በኢህላስ ሚሰራ
በሱና ተውቦ አላን ሚፈራ
ላዩ ብቻ ሳይሆን ከስጡም ያጌጠ
ከዱኑያ ፍቅር ጀነት ያስበለጠ
መቼም ማይታክተው በተውሂ የፀና
በሰሀቦች መንገድ በነቢዩ ፋና
በጥሩ የሚያዝ ከመጥፎ ከልክሎ
ለዲኑ ታታሪ ጉበዝ አስተውሎ
በጣም ረጋ ያለ ቤተሰብ አክባሪ
እውቀቱ አካፋይ በተማረው ሰሪ
ጠቃሚው ኢማን ነው በዱንያ ባኼራ
በሁለቱም ሀገር የሌውም ኪሳራ By Sofiya Bint Yassin
ምን ያደርግልኛል ዱነያዊ ኮተቱ
ጀነት አይገዛልኝ ለሚቀር በንቱ
ታዳ ምን ሊፈይድ ዱንያ ፍለጋ
ልቤ ላያርፍበት በከንቱ ላይረጋ
ይህንስ አልሻም ምንዳ የሌለበት
ነገ በአኼራ የምወቀስበት
እ
ው
ነ
ተ
ኛው ወዳጅ
መንገዱ የያዘ በሰለፎች መንሀጅ
ውዴታ እሚያውቅ እውነተኛ ወዳጅ
ሀብታምና ቁንጅና በሱና ፈልጎ
ውስጡ ያሳመረ ነፍሲያው ሸሽጉ
ስንቁን የሚሰንቅ አኼራን አስታዋሽ
ነገ ከነገ ወዲያ እማይል በጭራሽ
የጎደላት አሟይ ለሚስቱ አሳቢ
ያለው ሁሉ ለጋሽ ተንከባካቢ
ከዱንያዊ ኮተት ጀነት ያስቀደመ
በውሂድና ቡሱና ልቦነው ያከመ
በተግባር ታንፆ በኢህላስ ሚሰራ
በሱና ተውቦ አላን ሚፈራ
ላዩ ብቻ ሳይሆን ከስጡም ያጌጠ
ከዱኑያ ፍቅር ጀነት ያስበለጠ
መቼም ማይታክተው በተውሂ የፀና
በሰሀቦች መንገድ በነቢዩ ፋና
በጥሩ የሚያዝ ከመጥፎ ከልክሎ
ለዲኑ ታታሪ ጉበዝ አስተውሎ
በጣም ረጋ ያለ ቤተሰብ አክባሪ
እውቀቱ አካፋይ በተማረው ሰሪ
ጠቃሚው ኢማን ነው በዱንያ ባኼራ
በሁለቱም ሀገር የሌውም ኪሳራ By Sofiya Bint Yassin