telebirr


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Технологии


The first mobile money platform in Ethiopia

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций


እነሆ #5G ለሆሳዕና!

የሆሳዕና ከተማን የ #5G ሞባይል አገልግሎት ጅማሮ በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች ለነዋሪዎች አብስረናል!

የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጅማሮ ለማብሰር ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ ኃላፊዎች የተገኙበት እንዲሁም በከተማዋ ህዝብ አብሮነት የደመቀ የመንገድ ላይ ትርኢት እና ተያያዥ መርሐ ግብሮች አከናውነናል፡፡

የሆሳዕና ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እና ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#5G_ለሆሳዕና
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #Hosaena #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF


5ጂ በአርባ ምንጭ በይፋ ማስጀመራችንን ተከትሎ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡክ የአርባምንጭ ከተማን በስማርት ሲቲ እና ዲጂታል ሶሉሽኖች ያለመ ውይይት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ ከከተማዋ አስተዳዳር ከንቲባ እና የሥራ ኃላፊዎች ጋር አደረገ።

የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት የደረሰበት ደረጃ የቀረበ ሲሆን ከተማዋን ለነዋሪዎቿ፣ ለጎብኚዎች እና ለኢንቨስትመንት በሴፍ ሲቲ ሶሉሽን ምቹ እና ደህንነቷ የተጠበቀ ለማድረግ የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል፡፡

ውይይቱ ኩባንያችን የዘረጋውን ግዙፍ መሰረተ ልማት በመጠቀም የመስተዳድሩን መሬት አስተዳደር ጨምሮ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብር፣ ቱሪዝም ያሉ ቁልፍ አገልግሎቶችን በዲጂታል ሶሉሽኖች ማዘመንን ያካተተ ነው፡፡

ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን መሆን መደላድል የሆነውን የዲጂታል መታወቂያ ለዜጎች ለማዳረስ ኩባንያችን ለሚያደርገው ጥረት የትብብር ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህም ኩባንያችን ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝም ተብራርቷል፡፡

የከተማዋ የኮሪደር ልማት ከመስተዳድሩ ጋር በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑ የተወደሰ ሲሆን ይህም አገልግሎት እንዳይቋረጥ እና ሀብት እንዳይባክን ሚና መጫወቱ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም ኩባንያችን በዲጂታል ላይብረሪ፣ በችግኝ ተከላ እና ለዝቅተኛ ገቢ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያ በመለገስ ላከናወነው አርአያነት ያለው ተግባር ምስጋና ቀርቧል።

ለተደረገልን አቀባበል እና ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

11k 0 5 48 97





🌟 ገንዘብዎን በምቾትና በቅልጥፍና ይቀበሉ፤ ተጨማሪ 8% የገንዘብ ስጦታ ያግኙ!!

✅ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በቪዛ የተላከልዎን ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ በአቢሲኒያ ባንክ ዕለታዊ ተመን
✅ በዌስተር ዩኒየን (Western Union)፣ ኦንአፍሪክ (onafriq) እንዲሁም ቱንስ (Thunes) የተላከልዎን ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን ይደርስዎታል፡፡

💁‍♂️ በተጨማሪም 8% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia


መልካም የሥራ ሳምንት !

#Monday #MondayMotivation
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia


በኩባንያችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡካን ቡድን የዲጂታል ሶሉሽኖች እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ለማስፋፋት የሚያስችል ውይይት ከሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የሆሳዕና ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ጋር አደረጉ።

በዚህም ወቅት የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጨምሮ የአገልግሎት ክፍያዎች፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብር፣ ቱሪዝም የመሳሰሉ ዘርፎችን በዲጂታል በማዘመን የሆሳዕና ከተማን ለነዋሪዎች፣ ለኢንቨስትመንት እና ጎብኝዎች ምቹ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ኩባንያችን በከተማዋ መልሶ ማልማት ከመስተዳድሩ ጋር በቅንጅት በመስራት የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን ከማዘዋወር ባሻገር ቀጣይ የከተማዋን እድገት መሰረት ያደረገ ማስፋፊያ እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በማህበራዊ ኃላፊነት ረገድም በአረንጓዴ አሻራ እና አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው ተማሪዎች የደብተር ልገሳ በማከናወን አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸመ በመሆኑ ምስጋና ቀርቧል፡፡

የሆሳዕና ከተማ ህዝብ፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር ላደረጉልን የሞቀ አቀባበል እንዲሁም ለነበረን ስኬታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#Hosaena #SmartCity #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU

16k 0 7 58 109


Показано 8 последних публикаций.