Temari Podcast - ተማሪ ፖድካስት


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Образование


የዩቲዩብ ቻናላችን መቀላቀል አትርሱ 👇👇👇
https://youtube.com/@temari_podcast?si=--vADFvenliwbocx

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ላለፉት 10 ቀናት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

በተጨማሪም በምስጉን ዋንጫ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተሸላሚ ሆኗል።

በማጠቃለያ መርሐግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ (ዶ/ር)÷ የውድድሩ ጠቀሜታ የጎላ በመሆኑ ሊቋረጥ እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡

ለውድድሩ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ አካላትም ሚኒስቴር ዴኤታው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአምስት የተለያዩ የውድድር አይነቶች በ49 ዩኒቨርሲቲ መካከል በተካሄደው ውድድር 2 ሺህ 500 ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነውበታል ።

https://t.me/Temari_podcast


ዛሬ መሠጠት የተጀመረውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና በጥብቅ የፈተና ዲሲፕሊን እንዲሰጥ እያደረጉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች ገለፁ።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተፈታኞች ወደፈተና ማዕከላት ይዘው እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮችን ፍተሻ በማድረግ መያዙን ገልጿል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ኩረጃ እና ስርቆት የሚያግዙ ክልክል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዘው የተገኙ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ክፍሎች እንዳይገቡ አድርጓል።

ምስል፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

@Temari_podcast


#EXITEXAM #Note

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከጥር 26 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል።

⚡️በፈተና ወቅት ከተፈታኝ ተማሪዎች ምን ይጠበቃል ?


👉🏾 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

👉🏾 ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

👉🏾 ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

👉🏾 ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

👉🏾 ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 በድጋሚ ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ትኬት (Exit Exam Entry Ticket) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

NB.  ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

⚡️ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ

👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ

🍀 መልካም ፈተና 🍀

@Temari_podcast


Репост из: Freshman Tricks
የ ጤና እና የ ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንቶች ንፅፅር / Health Bs Engineering Departments comparison 👇👇👇

https://youtu.be/JQRlyHMGJpM


#ExitExamSchedule #AAU

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመፈተን የተመዘገባችሁ የፈተናው የመጀመሪያ ሁለት ቀናት መርሐግብር (ጥር 26 እና 27/2017 ዓ.ም) ከላይ ተያይዟል።

@Temari_podcast


#ExitExam

176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ

👉ፈተናው ከጥር 26 እስከ 30 ድረስ ይሰጣል

ጥር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺሕ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና #ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጭምር በዚህ ፕሮግራም ተካታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግል ኮሌጆችን በሚመለከት አሐዱ ላቀረበላቸው ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ኮሌጆች ላይ ገብቶ ለመፈተን የሚያስችል መዋቅር እንደሌለው በማንሳት፤ ነገር ግን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ተቋም በኩል መፈተን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የፈተና ቀኑ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ትምህርት የጀመሩትን ዩኒቨርሲቲዎች ታሳቢ ያደረገና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ መወሰኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረው ጥር 14 እና 15 የነበረ ቢሆንም፤ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እኩል ትምህርት ባለመጀመራቸው ወደ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የፈተና ፕሮግራም ተንቀሻቃሽ ስልክና የወረቀት ፅሁፍ ይዞ መገኘት ፈፅሞ #የተከለከለ መሆኑን የገለጹት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ "ተፈታኞች መታወቂያ መያዝና ከፈተና ፕሮግራሙ 30 ደቂቃ ቀድሞ ቦታው ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ የወጣው ፈተናም ከተማሩት በመሆኑ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዩኒቨርስቲዎች የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት ይሰጥ እንደነበረው ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጥር 26 እስከ 30 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የተማሪዎች ፈተና እንደተጠናቀቀ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 1 ቀን የመምህራንን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ መምህራን ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[ዘገባው የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው]

@Temari_podcast


ዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡

በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው ደብዳቤ፥ "በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ለመሸጋገር የትምህርት ማሻሻያ ስልጠና የሚከታተሉ መምህራን፣ ስልጠና ሳያጠናቅቁ መረጃ እየተሰጠ እንደሆነ" ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለማሻሻል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ መምህራን፣ የማስተማር ሙያ (PGDT) መውሰድና የመውጫ ምዘና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው በመስከረም 2017 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን በደብዳቤው ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ክልሎች ከዚህ በተለየ የማስተማር ሙያ ስልጠናም ሆነ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን፣ የደረጃ ዕድገት እየሰጡ መሆኑናቸውን መረዳቱን አሳውቋል፡፡

ማንኛውም ሠልጣኝ የትምህርት ማስረጃ ማግኘት የሚችለው የትምህርት ምዘና ወስዶ ማለፍ ሲችል መሆኑ እየታወቀ፣ የዲግሪ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በማድረግ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያና የደረጃ ዕድገት የሚሰጡ አንዳንድ ተቋማት መኖራቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ወጪያቸውን በመሸፈን የሚያስተምረው የበቁ መምህራንን ለማፍራት ነው ያሉት ኃላፊው፤ ማንኛውም ተቋም የመውጫ ምዘና ወስደው ላላለፉ ዕጩ መምህራን ምንም ዓይነት ማስረጃ እንዳይሰጥ በደብዳቤ ማሳወቁን አስረድተዋል፡፡ #ሪፖርተር

@Temari_podcast




ማካካሻ_ትምህርት_REMEDIAL_ማስፈፀሚያ_ሰነድ.pdf
4.9Мб
📘የሪሜዲያል ማስፈፀሚያ ሰነድ ለ2016 ዓ.ም
📝ለዘንድሮም አንድ አይነት ሲሆን የተቀየረው የምዘና ሂደቱ ብቻ ነው።

@Temari_podcast


በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ


በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

የዩኒቨርስቲዎች የቀጣይ የሪፎርም መዳረሻ ራስ ገዝ መሆን ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤በትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎቸ መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የትምህርት እና የምርምር ስራዎችን የበለጠ ለማጠናከር ራስ ገዝነት የተሻለ እድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

ሚኒስትሩ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት እና የጎንድር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝተዋል።

ጥራትን መሰረት አድርጎ የትምህርት ተቋማት ሃገር ተረካቢዎችና መሪዎችን በመቅረጽ ዩኒቨርሲቲዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

እስካሁን የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ሆነው በቀጣይ ሊሰሩ የሚገቡት ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዝግጅቶች የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

የጎንድር ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ የራሷ የጤና ባለሙያዎች ያስፈለጓታል ተብሎ በ1942 በተነሳ ሃሳብ መነሻነት በተደረገ ጥረት 1947 ዓ.ም የጤና ባለሙያ ማሰልጠኛ ሆኖ መመስቱ የዩኒቨርስቲው ታሪክ ያሳያል።

https://t.me/Temari_podcast
https://t.me/Temari_podcast


በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ   ለሚገነባው ልዩ አዳሪ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀምጧል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ደ/ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ለሚገነባው ልዩ አደሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅቱ እንዳሉት ብቁ፣ ተወዳዳሪና ለወደፊት ለሀገሪቱ ጠንካራ መሪ ለማውጣት ግብዓት የተሟላላቸው አዳሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

@Temari_podcast


#BongaUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት የካትቲ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ስድስት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@remedial_tricks


በአማራ ክልል ያለው የመምህራን ደመወዝ አለመከፈል መምህራንን የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ማስገደዱ ተገለጸ

በአማራ ክልል ከመስከረም እስከ ታሕሳስ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን፤ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ የጉልበት ሥራ ለመስራት ተገደዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ያሉ መምህራን ለተማሪዎቻቸው ሲሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተቋቁመው እየሰሩ ነበር ያለው ማህበሩ፤ "አሁን ላይ ግን ያለው ሁኔታ ካቅማቸው በላይ እየሆነ ነው" ብሏል፡፡

"ለወራት ደመወዝ ያልተከፈሉ መምህራን ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ ባለመቻላቸው የጉልበት ሥራ የሚሰሩ አሉ" ያሉት፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበበ ናቸው፡፡

"በዚህም ቀጣዩ የመምህራኑ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ አይታወቅም" ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት የትምህርት ሥራውንም ወደ ኋላ ጎትቶታል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ትምህርት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ወደሚሰጥባቸው ቦታዎች ሄደው ለመማር ሲሞክሩ በተፈጠረ የቦታ ጥበት፤ በአንድ ክፍል ውስጥ 90 የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲቀመጡ አስገድዷል ነው የተባለው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያሉ መምህራንን የተመለከቱ ችግሮች በሁሉም አካባቢ አይነት እና መጠናቸውን እየቀያየሩ መቀጠላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

@Temari_podcast


እጃችሁ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም ነገር ካላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መሸጥም ሆነ መግዛት የምትችሉበትን የቴሌግራም ቻናል እናስተዋውቃችሁ 👇👇👇

@Habesha_Gebeya1
@Habesha_Gebeya1


#JimmaUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥር 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በጅማ ግብርና እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ
- የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

@Temari_podcast


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በ2016 ዓ. ም በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተሸላሚዎች

በ2016 ዓ. ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ሽልማት ተበረከተላቸው።

የመጀመርያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት ድርጅት የሽልማት ሥነ ሥርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከናውኗል።

በዚህም ውጤታማ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች እና ሁሉንም ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዮናስ ንጉሴ በ2016 ከተፈተኑ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገሪቱ ከፍተኛውን ማለትም ከ700ው 675 ያመጣና ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው የቃላሚኖ ትምህርት ቤት የተማረ ነው። አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመድቦ የአንደኛ ዓመት ተማሪ ነው።

ትሩፋት መውደድ ከአፋር ክልል 421 በማምጣት የክልሉን ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበች ተማሪ ናት። አሁን በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመድባ የአንደኛ ዓመት ተማሪ ስትሆን ዛሬ ከተሸለሙት መካከል ነች።

ጌታቸው ያየ ሌላኛው ተሸላሚ ተማሪ ሲሆን በአማራ ክልል ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተፈትኖ ከ 600 ው 574 ያመጣ እና አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመድቦ እየተማረ የሚገኝ ነው። #DW

@Temari_podcast


#Update

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከጥር 8-14/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ለመመዝገብ 👉 https://exam.ethernet.edu.et

ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራችሁ ጥያቄ ዘውትር በሥራ ሰዓት በተከታዮቹ አማራጮች ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል፡፡

Email: ngat@ethernet.edu.et
☎️ 0911824528 / 0913678404 / 0913949676 / 0910076453 / 0923106826 / 0913866717 / 0911335683

Note:
➫ የመፈተኛ User Name እና Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ይሆናል።
➫ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም ይኖርባችኋል፡፡
➫ ምዝገባ ማድረግ የሚቻለው በተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ብቻ ነው፡፡

@Temari_podcast



Показано 18 последних публикаций.