ትምህርት በቤቴ®


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Образование


A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...

Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete
📩 For comment- @Tmhert_bebete_info_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


#Update #NGAT

የብሄራዊ ድህረ-ምረቃ (NGAT) መግቢያ ፈተና መጋቢት 5 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የNGAT አመልካቾች ምዘገባ መጠናቀቁን ገልጿን።

ፈተናው የሚሰጠው ዓርብ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ መሆኑንም አሳውቋል።

ተፈታኞች  በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሚመደቡበት የፈተና ማዕከላት እንዲገኙ ብሏል።

➡️ ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል በሚሄዱበት ወቅት ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

➡️ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 3 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት ይጠበቅበታል፡፡

➡️ የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

➡️ የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ይሆናል፡፡

#MoE

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


#ዛሬ ይጀመራል🥳
#ሊጀመር ነው

✨መልካም ዜና ለ2017 አ.ም 12ተኛ ክፍል ተፈታኞች🥳

Day 1 of 90 days challenge


በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው የEntrance prep tutorial *90 days challenge* ዛሬ ሰኞ መጋቢት 1 / 2017 አ.ም ማታ ይጀመራል😍

በነዚህ 90 ቀናት እስከ (ሰኔ 1) ለድፍን 3 ወራት እናንተን ለማትሪክ አዘጋጅተን እናስፈትናለን🤗

✍እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ማትሪክ
በዚህ አመት ከወራት በኋላ ለምትፈተኑ የተፈጥሮም ሆነ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዛሬውኑ ምዝገባ ለማከናወን እንደምትችሉ እናሳውቃለን🙏

💥ክላሳችን 2:30 ላይ ደመቅ ብሎ ይጀመራል 🤝

ለመመዝገብ👇
@Epregisterbot

Join👉 
@Entanceprepare


44A+ እና 40A+ ያሳኩት ተመራቂዎች 👏

ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተመረቁት ተማሪ አስማማው እና ተማሪ ቤዛዊት ከ40 በላይ A+ በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚዎች ሆነዋል።

የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተመራቂው ተማሪ አስማማው ሽፈራው CGPA 4.00 እና 44A+ በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራቂዋ ቤዛዊት ጌቱ CGPA 4.00 እና 40A+ በማምጣት በሁለተኝነት የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

ሁለቱም ተመራቂዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ ለትምህርታቸው ብቻ በመስጠታቸውና ጠንክረው በመስራታቸው ለዚህ ውጤት መብቃታቸውን ገልፀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


ፋይዳ / National_ID

✅ ትክክለኛውን National ID በቀላል መንገድ እንዴት እናገኛለን ?

➡️ ይህንን አገልግሎት ኢትዮ ቴሌኮም በሁሉም ክልሎች እየሰጠ ነው::
➡️ብዙ ሰራተኛ በሚገኝባቸው የመንግስት ተቋማትም ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል

➡️ በቀጥታ በኢትዮ ቴሌኮም በመሄድ የታደሰ ወይም ጊዜ ያላለፈበት መታወቂያ ይዞ በመሄድ fayda ቁጥር መውሰድ ይቻላል::

➡️ ዋናው ጉዳይ ከምዝገባ በኋላ ዋነው /ኦርጅናሉን መታወቂያ እንዴት ማግኘት እንችላለን የሚለው ነው!

➡️ ቴሌብር ላይ በሚሴጅ የሚላክልንን 16 ዲጂት fayda ቁጥር በማስገባት ሶፍት ኮፒ የሆነውን national id ማገኘት እና ኮፒ ማድረግ ይቻላል ነገር ግን ኦርጅናል አይደለምና በተለያዩ ጉዳዮቾ ለverify አስቸጋሪ ነው

✅ ትክክለኛውን /ኦርጅናሉን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://id.gov.et/ በዚህ ሊንክ ገብተን order card print የሚለውን መርጠን የ fayda ቁጥር እናስገባለን

➡️ በመቀጠል normal እና premium የሚል የክፍያ አይነቶች አሉ premium በተወሰነ ጊዜ  ማለትም በ 2-3 ቀን እንዲደርሰን ሲሆን regular ደሞ እራሳቸው ባስቀመጡት ጊዜ የምንወስድበት አሰራር ነው

ዋጋውም:-
🔤 regular service 343 birr

🔤 Premium service 625 birr

✅ስለሆነም በመረጥነው መንገድ በቴሌ ብር ወይም ሲቢኢ ክፍያ በመፈጸም ከተዘረዘሩ ቦታዎች በአቅራቢያችሁ የሚገኘውን ፖስታ ቤት በመምረጥ በሚደርሰን ሚሴጅ በተጠቀሰው ቀን ያለምንም መጉላላት እና ምልልስ ባለንበት ሆነን ከመረጥነው ፖስታ ቤት ኦርጂናል National id ማግኘት እንችላለን❗️

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


ብሔራዊ መታወቂያ ያልያዘ ተማሪ በቀጣይ ትምህርት ቤት አይመዘገብም ተባለ።

ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተማሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ ካልያዙ መመዝገብ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ ከ450 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ብሔራዊ መታወቂያ ለመመዝገብ የአንድ ወር ዘመቻ መጀመሩን ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ የከተማ አስተዳደሩ ለምዝገባው አስፈላጊውን የሰው ኃይል እና የቁሳቁስ ዝግጅት አጠናቅቆ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ ለሚገኙ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ ለማዳረስ ምዝገባው ከትምህርት ቤቶች ባለፈ በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ መዋቅሮች አንደሚካሄድም አስታውቀዋል፡፡

ቤተሰብም በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ እንዳለባቸው አውቆ በተዘረጉት አማራጮች ሁሉ ልጆቹን እንዲያስመዘግብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

©Ethio FM

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


#NGAT

ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ የካቲት 27/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ ይከናወናል፡፡

የመመዝገቢያ ሊንክ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/registration

ከ NGAT ምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በስልክ ቁ. 0920157474 እና 0911335683 ወይም በኢሜይል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et ወይም ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚቻል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የመፈተኛ 'User Name' እና 'Password' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም ይጠበቅባችኋል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


አሜሪካዊቷ ወጣት ማንበብና መፃፍ ሳልችል ከ12ኛ ክፍል ብቁ ነሽ ብሎ አስመርቆኛል በሚል ትምህርት ቤቷን ከሰሰች

የ19 ዓመቷ የኮነቲከት ወጣት በመሠረቱ መሃይም እንደሆንኩኝ እየታወቀ “በክብር” እንድመረቅ በመፍቀዱ ያስተናራትን የሕዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ክስ መስርታለች።ባለፈው ሰኔ፣ አሌይሻ ኦርቲዝ ከሃርትፎርድ የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክብር ተመርቃ የኮሌጅ ስኮላርሺፕ አግኝታለች።

አሁን ላይ ግን የቀድሞ ትምህርት ቤቷን በቸልተኝነት ያለኝን እውቀት ሳይረዳ በማስመረቁ ለስሜታዊ ጭንቀት ተዳርጌያለው ስትል ክስ መስርታለች ነው። የ19 ዓመቷ ወጣት እርሳስ በእጇ መያዝ እንደማትችል እና የማንበብ ችሎታዋ ከአንደኛ ክፍል ተማሪ ጋር እኩል እንደሆነ በመግለጽ የህዝብ ትምህርት ተቋሙን ትምህርቷን ችላ በማለቱ እንደሆነ የክሳ ዝርዝር ያሳያል። በፖርቶ ሪኮ የተወለደችው አሌይሻ ገና በለጋ ዕድሜዋ የመማር ችግር እንዳለባት አሳይታለች።

በ5 ዓመቷ ወደ አሜሪካ ከሄደች በኋላ ትምህርቷን ቀጠለች። ትምህርት ቤቷን እና በጉዳይዋ ላይ የተሾመው ልዩ አስተማሪ ለምረቃ አንድ ወር ሲቀረኝ እንኳን ብዙም እርዳታ እንዳልሰጧት ትናገራለች፣ አሌሻ ኦርቲዝ ማንበብና መፃፍ ሳትችል እንዴት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በክብር ልትመረቅ ቻለች የሚለው ግን አነጋጋሪ ሆኗል። በዚህም ሳያበቃ የኮነቲከት ዩኒቨርሲቲ ስኮላርሺፕ አግኝታለች።

የስማርት ስልክ አፕሊኬሽኖችን ተጠቅማ ጽሁፍ ወደ ንግግር እና ንግግር ወደ ጽሑፍ በመተርጎም የኮሌጁን ማመልከቻ እንኳን ለመሙላትና ለመፃፍ ተጠቅማለች። የኮሌጅ ተማሪ መሆን ግን ፍጹም ከዚህ የተለየ ሁኔታ ነበር። አሌሻ እየተቸገረች መሆኗን አምና በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ ትምህርት መከታተል እንዳቆመች ተናግራለች። ለአእምሮ ጤና ህክምና እረፍት መውሰድ ያቋረጠች ሲሆን በቅርቡ ወደ ክፍል እንደምትመለስ ተስፋ አለኝ ትላለች።


አሌሻ የቀድሞ ትምህርት ቤቷን የከሰሰችው በደረሰባት ችግር የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እንዲጠየቁ ስለፈለገች ነው። “እነሱ የሚያደርጉትን አያውቁም እንዲሁም ግድ የላቸውም” በማለት ሌሎች ወጣቶች  ትምህርታቸውን እንዳይሰረቁ ክሱ እንደሚረዳቸው ተስፋ አድርጋለች።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete




#AAEB

ከ4-8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሂሳብ እና የእንግሊዝኛ ማጠናከሪያ ትምህርት በቴሌቪዥን መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በመተባባር የማጠናከሪያ ትምህርቱን ከዛሬ የካቲት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቴሌቪዥን ስርጭት መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡

የትምህርት ስርጭቱ በ AMN Plus ከሰኞ እስከ አርብ ከ11፡00 እስከ 2፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሑድ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በስርጭቱ የእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርቶች በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ትምህርቱ በ AMN Plus ቻናል እንዲሁም በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይተላለፋል ተብሏል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል!

ብሪቲሽ ካውንስል ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና የካቲት 29/2017 ዓ.ም ይውሰዱ!

ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ፦
☎️ 0923032129

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች ቆጠራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።


በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ሥራ አስፈጽሚ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች ቆጠራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ገልጿል፡፡

የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰራዊት ሃንዲሶ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሥራ ክፍሉ በ2017 ዓ.ም በአቅድ ከያዛቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል አንዱ የምርምር ግብዓቶችንና ፋሲሊቲዎችን በማሻሻል የቤተ-ሙከራ ስታንዳርዳይዜሽንን እና አክሬዲቴሽን ስርዓትን መዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ የኢንዱስትሪ፤ የምርምር እና የላብራቶሪ ኬሚካሎች አያያዝ፤ ክምችትና የማጓጓዝ ሂደትና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ኬሚካሎች የቆጠራ ሥራ ለመሥራት እንዲቻል ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ይህ ሥራ የሚሰራው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ ሳይሆን በአቅራቢያቸው በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስር ባሉ ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙትን ኬሚካሎች ምንጭ፣ አይነት፣ ደረጃ፣ መጠን እና ባህሪይ የማወቅ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራም ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


#MoE

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ ይገባል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።

በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


#AAUCHS

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 179 ተማሪዎች አስመርቋል።

153 ተማሪዎች በሜዲካል ዶክትሬት፣ 21 ተማሪዎች በጥርስ ህክምና እና 23 ተማሪዎች ደግሞ በአኔስቴዥያ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ መካከል 165 ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማስመዘገቡ የተመረቁ መሆናቸው ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


🚀 አዲስ መድረክ፣ አዲስ ዕድሎች!
🚀የአባላታችንን በተሳካ ሁኔታ የተደረጉ ገንዘብ ማውጣቶች እናከብራለን!
አሁን በAllied Gold ይቀላቀሉ – የእርስዎ የስኬት ታሪክ እዚህ ይጀምራል!
💡 በኦንላይን ገቢ መፍጠር ቀላል ነው!
💡 ከብልጽግና ጋር ተባብረው በወርቅ ይድረሱ!
ለምን Allied Gold ን መምረጥ?
✅ 10,000+ በዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች የተረጋገጠ
✅ ደህንነቱ �ስተማማ የወርቅ ኢንቨስትመንት ከ24/7 ግልጽነት
✅ በአንድ ጠቅታ ገንዘብ ማውጣት እና ብቸኛ ድጋፍ
👇👇👇
link:https://alliedgd.cc/?invitation_code=53084

Official Channel:https://t.me/Allied_Gold


የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 7 ተከሳሾች በሙስና ወንጀል ጥፍተኛ ተባሉ

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጫላ ዋታን (ዶ/ር) ጨምሮ ሰባት ተከሳሾች በቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፍተኛ ተባሉ።

ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተከሳሾች በቀረበባቸው ሁለት ከባድ የሙስና ወንጀል ጥፍተኛ የተባሉ ሲሆን÷ 7ኛ ተከሳሽ ደግሞ በቀረበበት አንድ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ መባሉ ተመላክቷል፡፡

ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጫላ ዋታ (ዶ/ር)፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ታምሩ ኦኖሌ (ዶ/ር)፣ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ሮባ ደንቢ (ዶ/ር)፣ የቢዝነስና ተቋማዊ ልማት ም/ፕሬዚዳንት አብርሐም ባያብል (ኢ/ር)፣ የግዢ ዳይሬክተር አቶ ሊበይ ገልገሎ፣ የፋይናንስ ዳይሬክተር አቶ ቦሩ ህርቦዬ፣ የዩኒቨርሲቲው መምህርና የቢኤች ዩ አማካሪ ለታ ድሪባን ናቸው፡፡

በዚህም ከ1ኛ እስከ 6ኛ ተራ ቁጥር ያሉት ተከሳሾች የዩኒቨርሲቲው አመራርና የማኔጅመንት አባል በመሆን ሲሰሩ የመንግስት ግዢ አዋጅን በመተላለፍ በ2012 ዓ.ም በያዙት ቃለ ጉባዔ መሰረት ሕግን ባልተከተለ መልኩ ያለአግባብ ቢኤች ዩ ለተባለ አማካሪ ግዢው በቀጥታ እንዲፈጸም በማኔጅመንት ውሳኔ ማስተላለፋቸው ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ውል ሲዋዋል ዩኒቨርሲቲውን በመወከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት 1ኛ ተከሳሽ ውል ሰጪ ሆነው 7ኛ ተከሳሽ ውሉን በመፈረም በ5ኛ ተከሳሽ ትዕዛዝ መሰረት በ1ኛ ተከሳሽ ስም ለተመዘገበው አማካሪ ድርጅት ያለአግባብ ክፍያ እንዲፈጸም ማድረጉን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሷል።

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በመንግስት ላይ ከ196 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ከባድ የሙስና ክስ ቀርቦባቸው ነበር፡፡

በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ከሕግ ውጭ በሚሊየን በሚቆጠር ከደረሰው ጉዳት ውስጥ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው ተመላክቷል፡፡

2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በተመሳሳይ ከ500 ሺህ ብር በላይ ለግል ጥቅም ማዋላቸው የተመላከተ ሲሆን÷ 4ኛ ተከሳሽ  ከ2 ሚሊየን ብር በላይ፣ 5ኛ ተከሳሽ ከ99 ሺህ ብር በላይ፣  6ኛ ተከሳሽ ከ400 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ በአጠቃላይ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በክሱ ተብራርቷል።

ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከራቸው ዐቃቤ ሕግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተከሳሾች በሁለት ክሶች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በተጨማሪም 7ኛ ተከሳሽ በአንድ ክስ ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን÷ ፍርድ ቤቱ ከ8ኛ እስከ 17ኛ ያሉ ተከሳሾች ላይ ደግሞ በሌሉበት የጥፋተኝነት ውሳኔ በማስተላለፍ የቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለመጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


ኢንስታግራም በቲክቶክ ላይ የበላይነት ለመዉሰድ የተለየ የሪልስ መተግበሪያን ሊጀምር መሆኑ ተሰማ

ኢንስታግራም በቻይና ባለቤትነት የተያዘው የቲክ ቶክ የወደፊት ዕጣ በአሜሪካ ውስጥ እርግጠኛ ስላልሆነ ሬልስ የተሰኘውን አጭር የቪዲዮ ባህሪን አንድ የተለየ መተግበሪያ ለማስጀመር እያሰበ ነው ተብሏል።

በቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ የቢዝነስ ህትመት ዘ ኢንፎርሜሽን እንደዘገበው የማህበራዊ ሚዲያው ዋና አስተዳዳሪ አደም ሞሴሪ በዚህ ሳምንት ሊኖር ስለሚችለው እርምጃ ለሰራተኞቹ ተናግረዋል።

የኢንስታግራም የወላጅ ኩባንያ ሜታ በሪፖርቱ ዙሪያ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።

በጥር ወር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክ ቶክን የ75 ቀናት ማራዘሚያ በመስጠት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተፈረመውን ቲክቶክን መሸጥ ወይም ማገድን የሚጠይቀዉን ህግን ለማክበር መገደዳቸዉ ይታወሰል።

በወቅቱ "በዩናይትድ ስቴትስ" እና በቻይናው ባለቤቱ ባይትዳንስ መካከል የ 50 በ50 ሽርክና እንደሚፈልግ በመግለጽ ኩባንያውን የሚመራ የጋራ ኩባንያ ሊኖር እንደሚችል ተመላክቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete

Показано 16 последних публикаций.