ስለ ሰሞኑን ከባድ ብርድ እስልምና ምን ይላል?
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ
ኢስላም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሀይለኛ ሙቀት እና በሀይለኛ ብርድ ሰው ተቸግሯል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ለአላህ ካጠፋነው ጥፋቶች ንሰሀ ከመግባት ይልቅ በየዜና አውታሩ “የአለም በረዶ ስለቀለጠ ነው፣ ዛፎች በመቆረጣቸው ነው፣ ኦዞን በመሳሳቱ ነው…..” እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች ናቸው እየተባለ ይለፈፋል፡፡
እስቲ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን እንደሚሉ እንይ
አቡ ሁረይራ (ረድየላሁ አንሁ) ባስተላለፉት፣ ኡማሙ አል-ቡኻሪ በዘገቡት ትክክለኛ ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ጀሀነም (እሳት) ወደ ጌታዋ ስሞታ አቀረበች፡፡ ከፊሌ ከፊሌን በላው አለች፡፡ አላህ ሁለት ጊዜ እስትንፋስን ፈቀደላት፡፡ አንደኛው በቀዝቃዜ ወራት ሌላኛው ጊዜ በሙቀት ወራት፡፡ በሙቀት ጊዜ የምታገኙት ከባድ ሙቀት እና በቅዝቃዜ ጊዜ የምታገኙት ከባድ ውርጭ (ቅዝቃዜ፣ ቀቅ) (ናቸው)፡፡”
حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنِ الزُّهْرِيِّ، قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو سَلَمَةَ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ، أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا، فَقَالَتْ رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا، فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ، فَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ فِي الْحَرِّ، وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ ".
ልብ እንበል ከባዱም ሙቀት እና ከባዱም ብርድ የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የአላህን ፈሪዎች ሁሉ ፈሪ፣ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ እንደነገሩን የጀሃነም እሳት የምትተነፍሰው ሁለት ትንፋሽ ምክንያት ነው፡፡
ሌላው መገንዘብ ያለብን ነገር እስልምና ሙሉ መሆኑን ለማንኛውም አለም ላይ ላለ ክስተት በል እንዲያውም ለሚቀጥለው አለም ጉዳዩች፣ የሚቀጥለው አለም ላይ ምን እንደሚከሰት በዝርዝር እና በጥቅል የተናገር ዉድ፣ ልዩ፣ የማይበረዝ፣ የማይሰረዝ፣ የማይደለዝ፣ ዘመን የማያልፍበት ሀይማኖት ነውና አጥብቀን እንያዘው፡፡ ይሀው ተመልከቱ አለም “Econmic Crisese” ኢኮኖሚክ ክራይስስ ብለው ሲያወሩ አላህ ጥንትም የወለድ መጨረሻው ይህ መሆኑን ነግሮን ነበር፡፡
ትዳር እንዲመሰረት እና ከዝሙት እንድንታቀብ ከጥንትም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት መክሮ ነበር፡፡ ግን ይህን አልሰማ ብለው አሁን አለም ላለችበት ከባባድ በሽታዎች ተዳርገዋል፡፡
በሁሉም የህይወት ዘርፍ ላይ የጥንት የጠዋቱ ኢስላም (ሰለፍያ) በሄደበት መንገድ መሄድ ብቻና ብቻ ነው ዋስትናው፡፡ ሁለት ሃቅ የለም፡፡ ሁሉም ሙስሊም ከጥመት ቡድኖች እርቆ ወደ ብቸኛዋ አማራጭ እና ሁለተኛ ወደሌላት ሃቅ ጎዳና፣ ሰለፉነ ሷሊሂን የተጓዙባት ጎዳና መመለስ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ በሙስሊሙ አለም ላይ እንዳየነው አሁንም ከባድ ኪሳራ ይከሰታል፡፡
ታድያ ምን ይበጀን?
አማኞች ወደ ጌታቸው በንሰሃ ሊመለሱ፣ ያችን “ጭማሪ አለን?” ብላ የምትጠይቀውን ጀሀነም ከሷ ጌታችን እንዲጠብቀን እሱን ዘውትር መለመን ግድ ይለናል፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ፡፡ አላህ እነዚህን ሁሉ ተዓምራት የሚያሳየን በሰጠን አእምሮ የሱን ጌትነት፣ በቸኛ ተመላኪነት አውቀን ወደሱ እንድንመለስ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሁሌ ወዳንተ በጸጸት ከሚመለሱት አድርገን፡፡
Via SadatKemalAbuMeryem