🌙 🌙
**,,,,,,****
🌐 🌐
ከረመዳን ቡኋላ ምን,,,,,,,,?
🌷1/ደስተኛ መሆን
ረመዳንን ለማጠናቀቅ ስለተወፈቅን ይህን ታላቅ ፀጋ በማግኘታችንደስተኛ ልንሆን ይገባል።
አላህ سبحان وتعال ክቡር በሆነው ቃሉ እንዲህ አለ : -
"በአላህ ችሮታ(ትሩፋት)ና በእዝ ነቱ ይደሰቱ። በዚህም መክንያት ይደሰቱ ። ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው በላቸው"
አር ረዕድ:58
📗ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
" ለፆመኛ ሁለት ደስታ አለው
አንደኛው ደስታ በሚያፈጥርበት (ፆሙን በሚያጠናቅቅበት) ጊዜ
ሌላኛው ደስታ ከአምላኩ ጋር በሚገናኝበት ጊዜ። "
1/በሚያፈጥርበት ጊዜ ያለው ደስታ
ሀ/ የረመዳንን ፆም የዕለቱን ቀኑን ሙሉ ዒባዳ እና ባጠቃላይ የወሩን ሙሉውን ሳይበላሽበት ወይም ችግር ሳይገጥመው ባግባቡ ሳይጎልበት በማጠናቀቅ ለማፍጠር በመብቃቱ
ለ/(እና) ከተከለከለው ምግብ መጠጥና ,,, ተፈቅዶለት ስለ በላና ስለ ጠጣ ።
🔑 ነፍስያ ከተከለከለችው ነገር ሲፈቀድላት ደስተኛ ትሆናለች
ይህ ደስታ አጅር የሚያስገኘው ፁሞ ለማፍጠር በመጓጓቱ ነው።
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"ሰዎች ፈጡርን እስካቻኮሉና ስሑርን እስካዘገዩ(መጨረሻ ወቅት ላይ ሲበሉ) በመልካሙ ይዘወትራሉ(በኸይር ላይ ሆነው ይቆያሉ) ።"
🔗 በቀኑ ክፍለ ጊዜ የከለከለውን ምሽቱ ክፍለ ጊዜ ተፈቀደለት እንዲያው ም በፍጥነት መፍጠራ ቸውን ወደደላቸው።
🖍ፆመኛ ስው ምግብ መጠጡን ,,,, ,,, የተወው ለአላህ ብሎ እስከሆነና በተመገበ ቁጥር አላህን ካመሰገነ በማፍጠረም አጅር ያገኛል።
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"ባሪያው አንዲትን ጉርሻ ጎርሶ ሲያመሰግነው ፣ አንዲትን ጉንጭ ጠጥቶ ሲያመሰግነው አላህ ይወድለታል።"
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"ተመግቦ አመስጋኝ የፁሞ ታጋሽ (ሰብረኛ) ደረጃ አለው።"
📍በማፍጠሪያው ሰዓት ዱዓው ተቀባይነት አለው።
📗ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"አንድፆመኛ በማፍጠሪያው ወቅት ተመላሽ የማይሆን(ፍፁም ተቀባይየሆነ) ዱዓ አለው።"
🔹በመብላቱ,,, በዒባዳ ላይ ለመጠናከር ብሎ ከሆነ አጅር አለው።
"እኔ ከአልጋዬ ላይ ተኝቼ አጅር የማገኝበት ዒባዳ(አምልኮት) ምንኛ ያማረ የሚያስደስት መገዛት ነው። "
(ሐፍሳ رضي الله عنها)
" ፆመኛ ሰው ዒባዳ ላይ ነው ምንም እንኳ በአልጋው ላይ ቢተኛም። "
( رحمه الله አቡል ዓሊያ)
🔸ይህን የተረዳ በማፍጠሪያው ጊዜ ደስታው ከላይ በተገለፀው መልኩ ሲሆን:የደስታው ምንጭ ከአላህ ችሮታና እዝነት በመሆኑ ነው።
❌ በመፆሙ እየተበሳጨ አያጉተ መተመ በማፍጠሩ የሚደሰት ሰው አጅር የለውም።
2/ከአላህ ጋር ሲገናኝ ያለው ደስታ
✅ ለፆመኞች የተዘጋጀውን ስፍር ቁጥር የሌለውን ታላቅ ምንዳ በሚያገኝ ጊዜ,,, ይደሰታል
✅ፆመኞች እንጂ ሌሎች የማይገቡበትን የረያንን ጀነት በሚገባ ጊዜ ይደሰታል
3/የፆመኞች እርከን (ደረጃዎች)
ሁለት ደረጃዎች ናቸው
✳️ 1ኛውከአላህ ዘንድ ያለውን ታላቅ አጅር ለማግኘት ከምግብ መጠጥና ስሜት ራሳቸውን አቅበው ከርሱ ምንዳን ሸምተው ትርፋማ የሆኑት ሲሆኑ
✳️ ሌሎቹ ፆመኞች በዚህ ዓለም ባዱንያ ላይ ስለ አላህ ብለው በርሱ መንገድ ላይ ሁነው ከሀራም ነገሮች ታቅበው በመፆም የአኼራ ዒድ ሲደርስ በጀነት አላህ سبحان وتعالى ባዘጋጀላቸው ዓይን አይቶ የማያውቀውን ፣ ጆሮም ሰምቶ ያላወቀውንና ከሰው ልቦና ውስጥ ውል ማይለውን ፀጋ በልዩ መስተንግዶ በማፍጠራቸው ይደሰታሉ።
✴️ውድ ወንድሜ
☪ ነገ በአኼራ የማፍጠሪያ ዒዳችን ቋሚና ዘላቂ የሆነ የዘላለም ደስታ ለማግኘት ዛሬ ከስሜት ዝንባሌያችን እንፁም❗️
♦️'ገና ነው ፤ እደርስበታለሁ' የሚለውን ከንቱ ምኞት ከራሳችን እናሽቀንጥር፡፡ ከቀኑ ቀሪው ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሰዓቱ ረፋፍዷል፡፡ ጊዜ የለንም ገና ነው እደርስበታለሁ የሚለውን ከንቱ ምኞት ትተን ከቀኑ የቀረን ጥቂቱን ብቻ መሆኑን እናስታውስ።
⭕️መቼ እንደምንሞት አናውቀውም።
✅ በዚች አላፊ ጠፊና ረጋፊ የዱንያ ህይወታችን ፁመን በነገው ✳️ዘላለማዊ እውነተኛ ህይወት በአኼራው የማፍጠር አውነተኛ መስተንግዶ ደስተኞች እንሁን❗️
አላህ ደስተኛ
ከሚሆኑት ያድርገን❗️
ኣ,,ሚ,,,,,ን
🔸🔹🔶🔷🔹🔸🔻🔸🔷
t.me/tezkiraChannel